Sunday, December 8, 2013

የቀድሞ የደህንነት ሀላፊ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ልማታዊ ሙስኛ ሚሊኒየር


ኢትዮጵያ ብዙ ሚሊዮኖች ድሆች ጥቂት የተመረጠው ዘር ሚሊኒየሮች
  
ባለፈውሳምንት ኢትዮጵያ  ከአፍሪካ አገራት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ባለ ብዙ ሚሊዮን ብራሞች በማስቆጠር ዳሚነቱን እንደያዘች የተለያዩ የዜና አውታሮች  ሲግቡ ሰንብተዋል፡ 108 ከመቶ እድገት በአንድ ዓመት ብቻ በማስመዝገብ። አጃኢብ አይደል ኢትዮጵያ ቀን ወጣላት። አለፈልን ስማችን በድህነት ከመነሳት አልፎ ለዚህ ላበቃን ህውሃት እና የተከበሩ ልማታዊ ሙሰኛ አባላቱ ምስጋና ይግባቸው   እንደ አውሮፓውያኑ ቀመር 2007 ዓም ኢትዮጵያ 1300 ባለብዙ ሚሊዮን ብሮች የነበሯት ሲሆን በዚህ ዓመት ግን ቁጥራቸው ወደ ወደ 2700 አሻቅቧል የቀድሞው የደህንነት ሃላፊ አቶ ወልደሚካኤል፡ቤተሰቦቻቸው ዘመዶቻቸው፡ዘርማንዘራቸው፡ ጓደኞቻቸው፡ እነ /ሮ አዜብ መስፍን ስዩምመስፍንን፡ አቦይ ስብሃትን፡ እንዲሁም ሌሎች በአንድ ሌሊት አዳር የተተኮሱ የህውሃት አባላትን፡ደጋፊዎቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ጨምሮ። ምን ይሳነዋል ለህውሃት። ዛሬ ፋና ሬዲዮ የዘገበው ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት በ1000 ብር ደሞዝ ባለ4 ደረጃ ህንጻ ማሰራት እንደሚቻል በ 500 ብር የወር ደሞዝ   በተለያዩ ባንኮች እሰከ ሚሊዮን ብር ማስቀመጥ እንደሚቻል እና ከስምንተኛ ክፍል ያቋረጡ ስራ ዓጥ እና ምንም ገቢ የሌላቸው የህውሃት ዓባላት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እስከ 8 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በባንክ በማስቀመጥ በአገራችን ለዘመናት ተለጥፎ የነበረውን የድህነት ምሳሌ ተረት ተረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ምን ይሳነዋል ለህውሃት? ሚሊዮኖች ጠኔ ይዟቸው በሚንጠራወዙባት ኢትዮጵያ በመቶዎች የሚቆጠሩ እንደእነ  አቶ ወልደስላሴ እና አጋሮቾቻቸው አልጠግብ ብለው ሲተፉ ያድራሉ። እስኪ ፋና ወደ አሰናዳው ዝርዝር ዜና ልመልሳችሁ።   

መጽሃፌን አሳትሙ/ግዙ በግዳጅ  
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኛ የነበሩት አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ከሁለት ቤተሰቦቻቸው ጋር በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ተጨማሪ ክስ ተመሰረተባቸው።
ተከሳሾቹ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል፣ የመከላከያ ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩት ወንድማቸው ዘርአይ ወልደሚካኤል፣ እህታቸው ወይዘሪት ትርሃስ ወልደሚካኤልና የቅርብ ጓደኛቸው ዶሪ ከበደ ናቸው ።
ተከሳሹ በ 2002 ."ቴረሪዝም ኢን ኢትዮዽያ ኤንድ ዘ ሆርን ኦፍ አፍሪካ" የተሰኘ መጽሃፍ ያሳተሙ ሲሆን ፥ ይህንን መጽሃፋቸውን በስፖንሰር ለማሳተም ባደረጉት እንቅስቃሴም የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ በየነ ገ/መስቀል የነበራቸውን ቀና አስተሳሰብ ተጠቅመው ያለአግባብ በልጽገዋል ነው የሚለው የክስ መዝገቡ።
መጽሃፉ በመስሪያቤታቸው ስም እንደተዘጋጀ በሚያስመስል ሁኔታ አቶ በየነ የሚመሯቸው የቦሌ፣ የብርሃንና ሰላምና የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ሃላፊዎች በጋራ የአቶ ወልደስላሴን 3 ሺህ መጻህፍት124 ሺህ ብር እንዲያሳትሙ ተደርጓል ነው የሚለው ክሱ።
ማተሚያ ቤቶቹ በርካሽ ያሳተሙት አቶ ወልደስላሴ ከነበራቸው ተሰሚነትና ስልጣን መነሻነት መሆኑንና ይህንን መጽሃፍ ኢትዮ ቴሌኮም ምንም በማይመለከተው 10 ሺህ መጻህፍት የሚታተሙበትን የ385 ሺህ ብር ክፍያ ለአቶ ወልደስላሴ እንዲከፍልም መደረጉንም ነው የክስ መዝገቡ የሚያስረዳው።
አቶ ወልደስላሴ የሙገር ሲሚንቶ ኢንተርፕራይዝና የአትክልትና ፍራፍሬ ገበያ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ በነበሩበት ጊዜ ሃላፊነታቸውነ ተጠቅመው ፥ ሁለቱ ድርጅቶች 310 ኮፒዎችን በግድ እንዲገዙ መደረጉም ተመልክቷል።
26 የሚሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶችም እያንዳንዳቸው ከ 25 እስከ 1ሺህ 500 ፥በጥቅሉ 73 ሺህ የሚልቁ ኪፒዎችን ሳይወዱ በግድ እንዲገዙ መደረጉ ፣ ይሄ ሁሉ ሲደረግ ተቋማቱ ለመጻህፍቱ ገንዘብ ከፍለው መጻህፍቱን አለመረከባቸውም ጭምር ነው በክስ መዝገቡ የተዘረዘረው።

ቤቴን ስሩ በግዳጅ
ተከሳሹ አቶ ወልደስላሴ ባልደረባቸወ የሆኑ አንዲት ሴት ጋር በነበራቸው መቀራረብ የመስሪያቤቱን መኪና በህገ ወጥ መንገድ ነዳጅ እያስሞሉ ግለሰቧ እንደልባቸው በአዲስ አበበባና ከከተማ ውጪ እንዲጠቀሙበት አስደርገዋል የሚለውም ተጠቅሶባቸዋል።
ተከሳሹ ከ2003 እስከ 2004 .ም አቶ ሳቢር አርጋው የተሰኙ ነጋዴን ለምሰራው ቤት ሴራሚክ ስለጎደለኝ የጣሊያን ስሪት ገዝተህ ስጠኝ በማለት ፥ በስልጣናቸው አስፈራርተዋቸው 65 ሺህ ብር ሴራሚክ ተቀብለዋል ፣ ከ 2001 እስከ 2005 ባሉት የግብር አመታት አሳትሞ ከሸጣቸው መጻህፍት ካገኘው ገቢ ላይ መክፈል የነበረበትን ከ496 ሺህ ብር በላይ ለመንግስት አስታውቆ አለመክፈሉም ተጠቅሷል።
ተከሳሹ ባለ4 ፎቅ የግል ቤቱን ወንድሙ ለሆነው ሁለተኛ ተከሳሽ ዘርአይ ወልደስላሴ ውክልና ሰጥቶና ከመኖሪያ ቤት ውጭ ለሆነ አገልግሎት እንዲውል አድርጎ በ14 ወራት ውስጥ 790 ሺህ ብር ገቢ አግኝቷል ፤ ከገቢው 126 ሺህ ብር የሚሆነው የመንግስት ግብርን ለግብር አስገቢው መስሪያቤት ሃሰተኛ መግለጫ በማቅረብ ሳይከፍል መቅረቱም በክሱ ተመልክቷል።
ከዚሁ ቤት ኪራይ መንግስት ከተርን ኦቨር ታክስ ማግኘት የነበረበትን ከ119 ሺህ ብር በላይ ገቢ ሳያገኝ መቅረቱና ተከሳሹ በህገ ወጥ መነገድ ያገኘውን ገንዘብ ማንም እንዳያውቅበት ለማድረግ በሰኔ 28 1998 .ም ለሁለተኛው ተከሳሽ (ወንድም) ዘርአይ ወልደሚካኤል ሙሉ ውክልና መስጠቱ ተዘርዝሯል።
እንዲሁም ምንም አይነት የገንዘብ ልውውጥ ሳያደርጉ ከ3ኛዋ ተከሳሽ እህቱ ትርሃስ ጋር መጋቢት 242005 .ም የብድር ውል ማድረጋቸውም ተጠቅሷል።
በተጨማሪም ተከሳሹ ከእህቱና ወንድሙ ጋር ያለአግባብ አፈሯቸው የተባሉ የገንዘብና የአይነት ሃብቶች በክስ መዝገቡ ተጠቅሰዋል።
ስራ ዓጥ ባለብዙ ሚሊዮን ብሮች ልማታዊ ባለሃብት
1ኛው ተከሳሽ ወልደስላሴ ወደሚካአል 1983 እስከ የካቲት 2005 . የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የውስጥ ሰራተኛ ሆኖ ሲሰራ ፥ ወርሀዊ ደመወዙ ከ 1,600 እስከ 6,000 ብር የነበር ሲሆን ፥ ነገር ግን ስልጣኑን እና የነበረውን ተሰሚነት በመጠቀም በፈጸመው የሙስና ወንጀል ከባለ4 ደረጃ ህንጻ ውጪ ፣ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በተለያዩ የግልና የመንግስት ባንኮች ተቀማጭ ማድረጉም ተመልክቷል።
2ኛ ተከሳሽ አቶ ዘርአይ ወልደስላሴ ከመከላከያ ሚኒስቴር በጡረታ እስከሚገለል ድረስ ወርሀዊ ደመወዙ 532 ብር የነበር ሲሆን ፥ በክስ መዝገቡ ተከሳሹ በተለያዩ ባንኮች 5 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ማስቀመጡ ፣ በአዲስ አበባ ቤቴል ቁጥር 3 በተባለ አካባቢ
74 ካሬ ሜትር ይዞታ ላይ መሰረት የተጀመረበት ቦታ ፣ በአፋር ክልል ከ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሁለት የእርሻ ኢንቨስትመንቶችና 2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ሁለት ሎደር ማሽነሪዎችም በስሙ መኖራቸው ተመዝግቧል ።
3ኛዋ ተከሳሽ የአቶ ወልደስላሴ እህት 8ኛ ክፍል ተማሪ ስትሆንምንም አይነት የገቢ ምንጭ የሌላት እንደሆነች ነው በክስ መዝገቡ የተገለጸው።
ግለሰቧ በ 81 ሺ ዩሮ የተገዛ አንድ ስካቫተር አውቶሞቢል መኪናበአዲስ አበባ ቦሌና የካ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በለገጣፎ ፣ በመቀሌና አክሱም ከተሞች 3 ሺህ 266 ካሬ ሜትር ቦታዎች በስሟ ተመዝግቧልበተለያዩ ባንኮችም ከ 8 ሚሊየን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብም እንዲሁ ተመዝግቧል።
የአቶ ወልደስላሴ የረዥም ጊዜ ጓደኛ እንደሆነ የሚነገርለት 4ኛው ተከሳሽ ዶሪ ከበደ አቶ ወልደስላሴ በቤተሰቦቹ ስም በሚስጥር የያዘውን ከፍተኛ ሃብት ይዞ በማቆየት የወንጀል ተሳትፎ አድርጓል ነው የሚለው ክሱ።
በአጠቃላይ ተከሳሾቹ ንብረትና ገንዘብ ለማፍራት የሚያስችል ምንም አይነት አቅም ሳይኖራቸው በፈጸሙት ምንጩ ያልታወቀ ንብረትና ገንዘብ ይዞ በመገኘት የሙስና ወንጀል ተከሰዋል።
ከአቶ ወልደስላሴ እና ከወንድማቸው በስተቀር ወይዘሪት ትርሃስ እና አቶ ዶሪ የዋስትና መብት ጥያቄ አቀርበው ፥ ከሳሽ አቃቤሀግ የተመሰረተባቸው ክሰ ከ10 አመት በላይ የሚያስቀጣ በመሆኑ በህጉ መሰረት የዋስትና መብት ሊፈቀድላቸው አይገባም ሲል ቅዋሜ አቅርቧል።
ግራ ቀኙን የመረመረው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት በተከሳሽ ጠበቆች የቀረበውን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግና ጉዳያቸውን ማረሚያ ሆነወው እንዲከታተሉ በመወሰን ፤ የክስ መቃወሚያቸውን ለመስማት ለታህሳስ 7 2006 .ም ተለዋጨ ቀጠሮ ይዟል።



No comments:

Post a Comment