Friday, December 13, 2013

ጉዳዬ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይታይልኝ ፡ በሙስና ተጠርጣሪው አቶ መላኩ ፈንታ

እንደ ኢሳት ዘገባ ሕገመንግስት የትርጉም ጥያቄ ያስነሳው የአቶ መላኩ ጉዳይ ዛሬም አልተቋጨም።ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም :- የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ክሳቸው በየትኛው ፍርድ ቤት ይታይ በሚለው ጉዳይ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የመጨረሻ ውሳኔውን እንዲያሳውቅ ሲል የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት  ፲፭ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ትእዛዝ በመስጠት ለታህሳስ ፳፪ ቀን ፳፻፮ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።ፍ/ቤቱ ቀደም ሲል በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ጉዳዩን የመረመረው የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የውሳኔ ኀሳቡን ዛሬ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል።ሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩት አቶ መላኩ ፈንታ የተሾምኩትና ስሰራ የቆየሁት በሚኒስትር ማዕረግ ነው፣የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል ነበርኩኝ ፤ስለዚህም በፍርድ ቤቶች መቋቋሚያ አዋጅ ፳፭/፹፰ መሰረት እኔ በሚኒስትር ማእረግ የተሾምኩ ስለሆንኩኝ የቀረበብኝ ክስ መታየት ያለበት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሳይሆን በጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው በማለት ያቀረቡትን መከራከሪያ ፍ/ቤቱ በማጤን ጉዳዩ የህገመንግስት ትርጉም ያስፈልገዋል በሚል ለሕገመንግስት አጣሪ ጉባዔ እንዲመራ ህዳር ፲፩ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም በዋለው ችሎት መወሰኑ ይታወሳል።የኮሚሽኑ አቃቤ ህግ በበኩሉ አቶ መላኩ በሚኒስትር ማዕረግ መሾማቸው ጥቅማ ጥቅማጥቅሞችን በሚኒስትር ደረጃ እንዲያገኙ እንጂ ሚኒስትር ስለነበሩ አይደለም ሲል የአቶ መላኩን መከራከሪያ ተቃውሞ እንደነበር ይታወሳል፡፡በአቶ ካሳ ተ/ብርሃን የሚመራው የፌዴሬሽን ም/ቤት ከሕገመንግስት አጣሪ ጉባዔ የደረሰውን የውሳኔ ሃሳቡ በ፴ ቀናት ውስጥ ምላሽ መስጠት እንዳለበት በሕግ የተደነገገ ቢሆንም፥ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት የሚገኙ መሆናቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት ምክር ቤቱ በቀጣይ ፩፰ ቀናት ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔውን እንዲያሳውቅ ሲል ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

No comments:

Post a Comment