Showing posts with label Kenya. Show all posts
Showing posts with label Kenya. Show all posts

Tuesday, October 14, 2014

የማራኪ መጽሄት ባለቤት ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ በስደት በሚኖርበት ናይሮቢ ኬንያ ህይወቱ አለፈ

በስደት ላይ ሞት እንዴት ያሳዝናል።  አገሩም ላይ ሳይደላው፡ በስደት ላይ እንደወጣ ለቀረው የሙያ አጋራችን ነፍስህ በሰላም ትረፍ።  የህውሃትን ወከባ እና አፈና አመለጥኩ ሲል በዚህ መልኩ መሞት ግን ህይወት አንዳንዴ ለምን በጣም ብዙ ጊዜ በየዋሃን ላይ እንደምትጨክን ያሳያል። የሚሊዮን ሞት ለቤተሰቡ እና ለሙያ አጋሮቹ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ከራሴ ልምድ አውቀዋለሁ። ወይ ነዶ ስደት ለወሬ አይመችም። ለሚሊዮን ቤተሰቦች፡ወዳጆች እና የሙያ ባልደረቦች መጽናናቱን ይሰጣችሁ ዘንድ ምኞቴን እየገለጽኩ ይህ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ወይ ልብ ይስጠው ወይ ደግሞ መጨረሻውን ያቅርበው፡ አሜን።
ከሞቱ አሟሟቱ ካገሩ በወጣ በወር ከአስር ቀኑ በሞት ያጣነው ጋዜጠኛ ሚሊየን ሹርቤ የመጨረሳዎቹ ቀናት
ጋዜጠኛ ሚሊዮን በመጨረሻዎቹ ሰዓታት…
.
የሚሊዮን አሟሟት እንዳስረዳችሁ ለጠየቃችሁኝ …

ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ከ
12 አመት በላይ የሰራ ወጣት ጋዜጠኛ “ነበር”፡፡ በነሃሴ ወር ውስጥ በመንግስት ወከባ ህይወቱን ከእስር ለማትረፍ ተሰዶ ወደሀገሩ በሳጥን ለመመለስ እየጠበቀ ያለ ወጣት ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ…ሚሊዮን፡፡ ተስፋ የነበረው ስደተኛ ጋዜጠኛ የመልካም ባህሪ እና ስብእና ባለቤት የነበረው ሚሊዮን፣ ስለሀገሩ ፍቅር ብዙ መሰናክሎችን ሊጋፈጥ ስደትን መርጦ ባሰበበት ሳይሆን በታሰበለት ሊኖር የተገደደው ሚሊ እንደወጣ በሰው ሀገር ልጄን እህቶቼን ቤተሰቦቼን ሃገሬን እንዳለ በድንገት

Thursday, April 24, 2014

ህይወታችን በፍርሃትና በስጋት የተሞላ ነው፡ በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች

ኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ችግር እየተባባሰ መሄዱን እዚያ የሚገኙ ስደተኞች አስታወቁ ። የኬንያ መንግሥት ስደተኞች በሙሉ በሃገሪቱ ወደሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች እንዲገቡ ካዘዘ ወዲህ በተለይ በከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የፍርሃትና የስጋት ህይወት እንደሚገፉ ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ።
Kenia Dadaab, Somalische Flüchtlinge በኬንያ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ቢሮ በበኩሉ በከተሞች ኑሮአቸውን ሲገፉ የቆዩት ስደተኞች ጉዳይ መፍትሄ እንዲፈለግለት ለኬንያ መንግሥት ማሰሰቡን መቀጠሉን አስታውቋል።ድርጅቱ ችግሩ መፍትሄ ያገኛል ብሎ ተስፋ እንደሚያደርግም ተናግሯል ።ኬንያ ከ3 ሳምንት በፊት ያወጀችው አዲሱ ህግ በሃገሪቱ የሚገኙ ስደተኞች በሙሉ በሁለቱ የስደተኞች መጠለያዎች ማለትም በምሥራቅ ኬንያው የዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ወይም ደግሞ በሰሜን ምዕራቡ በከካኩማ መጠለያ እንዲገቡ ያዛል ። ይህ ህግ ከታወጀ አንስቶ በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን «ዩኤንኤችሲአር»እውቅና የሰጣቸውም ሆነ ገና እውቅና ያላገኙት ስደተኞች መብታቸው መጣሱና መንገላታታቸውም መባባሱን ኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ።የኬንያ መንግሥት ስደተኞች በሙሉ ወደ መጠለያ ጣቢያዎች እንዲገቡ ቢያዝም ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞችም እንደሚሉት