Showing posts with label Big Brother Africa 2013. Show all posts
Showing posts with label Big Brother Africa 2013. Show all posts

Saturday, June 22, 2013

ቢግብራዘርአፍሪካ፡ቤቲ፡እና እኛ

ዛሬ ይለያል ጉዱ 
እስቲ በትልቁ ወንድም አፍሪካ በእንግሊዘኛው አጠራር ቢግብራዘርአፍሪካ ልጀምር። ይህ በጂዮርጅ ኦርዌል ልብወለድ መጽሃፍ ላይ ከሚገኝ አንድ አምባገነን ገጸባህሪ ስሙን በውሰት በመውሰድ በሆላንድ አገር  እንደ አውሮፓውያኑ ቀመር በ1990 መጨረሻ ላይ የተጀመረ Reality Show የቴሌቪዥን የመዝናኛ ይቅርታ የመጃጃያ ዝግጅት አገር፡ድንበር እና ባህር በማቋረጥ በመላው ዓለም ታዋቂነትን በማግኘት ወደ አፍሪካ በመዝለቅ ከደቡብ አፍሪካ ለአፍሪካውያውን አድናቂዎች ዝግጅቱን ማሰራጨት ከጀመረ እነሆ አንድ አስርት ዓመት ሆኖታል። እኔ በበኩሌ ይህንን ዝግጅት ተከታትዬው የማላቅ ሲሆን ዛሬ ይሄን ጦማር እንድጦምር ያነሳሳኝ ግን ባለፉት ሳምንታት ኢትዮጵያ ውስጥ እና በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፍተኛ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከሆኑት ጉዳዮች አንዷ