Sunday, January 13, 2013

በስዊድን የሚገኘው የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ድረገጽ ሃክ ተደረገ


ተቀማጭነቱ በስዊድን አገር የሆነው የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ድረገጽ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በህውሃት መንግስት ሃክ ተደረገ/ተጠቃ (እባካችሁ ሃክ የሚለውን የእንግሊዘኛ ቃል ሊተካ የሚችል የአማርኛ ቃል የምታውቁ ካላችሁ ተባበሩኝ) ። ድረገጹ በሞሮኮ መንግስት ሃክ እንደተደረገ/እንደተጠቃ በእንግሊዘኛ የተጻፈ ጽሁፍና እንዲሁም በአረብኛ ቋንቋ የተደገፈ የጥቂት ሰከንዶች መልእክት የተቀመጠ ሲሆን የሞሮኮ መንግስት ድረገጹን ሃክ ለማድረግ/ለማጥቃት ያነሳሳው ምክንያት
መንግስታችሁ (የኢትዮጵያ መሆኑን አይገልጽም) የምዕራብ ሰሃራን ከሞሮኮ ለመገንጠል የሚታገለውን የፖሊሳሪዮ ግንባር የሚደግፍ በመሆኑ እኛም ይህንን የሞሮኮን ህልውና የሚጻረረውን ድርጅት የሚደግፈው መንግስታችሁ ድጋፉን እስካላቆመ ድረስ በድረገጻችሁ ላይ የምናደርገውን ጥቃት እንቀጥላለን” ይላል። ጉዳዩን ለማጣራት የስደተኛ ማህበሩ ሊቀመንበር የድረገጹን ምህዋር የሰጠውን ድርጅት ጠይቆ ያገኘው የኢሜይል ምላሽ ***(ዋናውን ከዚህ መልእክት በስዊድንኝ በታች ያገኙታል) የሚያስረዳው ከድርጅቱ የኤፍቲፒ (ፋይል ትራንስፈር ፕሮቶኮል) መረጃ እንደሚያሳየው ድረገጹን በተለያየ ጊዜ ለማጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን በመጠቆም ድርጅቱ ካለው ልምድ በመነሳት ድረገጹ ሊጠቃ የሚችለው በኢትዮጵያ መንግስት አልያም ከማህበሩ ጋር ተጻራሪ ዓላማ ባላቸው ቡድኖች ሊሆን እንደሚችል ደምድሟል። በዚህ አጋጣሚ እንዲህ ዓይነቱ ጥቃት ሊካሄድ የሚችለው በህውሃት መንግስት ወይም ውጭ አገር በተለይም እዚህ ስዊድን አገር በሚገኙ ደጋፊዎቹ/ሰላዮች እንጂ ከዚህ የስደተኞች ማህበር ጋር ምንም ዓይነት የዓላማም ሆነ የርዕዮት ዓለም ተቃርኖ በሌለው የሞሮኮ መንግስት ሊሆን እንደማይችል ከማንም የተደበቀ አይደለም። እንደሚታወቀው በስዊድን አገር የሚገኙት የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው በስልጣን ላይ የሚገኘውን መንግስት የሚቃወሙ ሰላማዊሰልፎችን እዚህ ስቶክሆልም በሚገኘው የህውሃት ቆንስላ ፊትለፊትና በሌሎችም የከተማው አካባቢዎች በማካሄድ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚካሄደው የሰብዓዊ መብት ጥሰት፡የህግ የበላይነት እጦት በማጋለጥ እንዲሁም በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት እንዲፈቱ የሚያደርገው ጥረት በገዢው ፓርቲና ደጋፊዎቹ ጥርስ ውስጥ እንዲገባ እንዳደረገው መገመት አያዳግትም። በተለይም ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ድረገጹ በይዘትና በቅርጽ እንዲሻሻል ተደርጎ በየጊዜው ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ወቅታዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በድረገጹ ላይ እንዲወጡ በማድረጉ የጎብኚዎቹ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነበር። የስደተኛ ማህበሩ በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መባቻ ላይ ለ14 ወራት በቃሊቲ እስር ቤት እንዲማቅቁ ከተደረጉ በኋላ የተፈቱትን ሁለት ስዊድናዊ ጋዜጠኞች በመሸለም እንዲሁም በእስር ቆይታቸው ወቅት ስለደረሰባቸው እንግልት ለዓለም ህብረተሰብ እንዲያጋልጡ ያደረገው አስተዋጽኦ የህዋሃት መንግስትንም ሆነ ደጋፊዎቹ በከፍተኛ ደረጃ እንዳስቆጣ ለማንም ግልጽ ነው።የገዢው ፓርቲ ከቻይና መንግስት በሚደረግለት ሙያዊም ሆነ ቁሳዊ ድጋፍ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖረው ህዝብ በአገር ደህንነት ስም መረጃ እንዳያገኝ በውጭ አገር የሚገኙ የተለያዩ ድረገጾችና ጦማሮችን እንደሚያፍን ዶ/ደብረጽዮን የተባለው የቴሌ ባለስልጣን ዘመን ለሚባለው የመንግስት ልሳን መጽሄት በቅርቡ የገለጸ ሲሆን የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ድረገጽም የዚህ የተቀነባበር ዘመቻ አንዱ ሰለባ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። በድረገጽ አዘጋጅነት በሰራሁባቸው ጊዚያት የተለያዩ ማንነታቸው የማይታወቁ ግለሰቦች በህገወጥ መንገድ ድረገጹ ውስጥ ለመግባት እና የድረገጹን ይዘት እና መረጃዎችን ለማበላሸት ያደረጉትን ሙከራ የተከላከልኩ ሲሆን እነዚሁ ግለሰቦች በመጨረሻ ሙከራቸው ተሳክቶላቸው ድረገጹን ለማጥቃት ችለዋል።


***Hej Assefa,

även svårt att veta exakt Vem som gjort men via FTP vi se någon försökte flera gånger olika metod också tidigare
Vi rekommenderas från vår erfarenhet hela tiden hände antingen regeringen eller personen motsatte din målgrupp.

Återkom gärna om ni har några frågor eller funderingar.

Var god bevara historiken om du svarar på det här meddelandet.
--
Med vänlig hälsning
Fredric S
Second Line, Loopia AB
Tfn: +46 (0)21 12 82 22 - Fax: +46 (0)21 12 82 33 -http://www.loopia.se/


No comments:

Post a Comment