Monday, July 14, 2014

ከ ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ጠበቃ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

Defendants’ lawyer Ato Amaha briefing the  crowd ‹‹ከቅዳሜ አራት ሰዓት ጀምሮ ደምበኞቼ በህገ ወጥ መንገድ መታሰራቸው መታወቅ አለበት ››
‹‹የአካል ነጻነታቸው እንዲከበርም ክስ እንመሰርታለን››
የአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለመጨረሻ ጊዜ ከሚል ማስጠንቀቂያ ጋር ለፖሊስ የሰጠው የ28 ቀን ቀጠሮ ቅዳሜ የሚያበቃበት በመሆኑ የዞን ዘጠኞችና የጋዜጠኞቹን ጉዳይ ሲከታተሉ የቆዩ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና ጋዜጠኞች ቀደም ብለው ፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ደርሰዋል፡፡ምን ይወሰን ይሆን? በሁሉም ልብ የሚመላለስ ጥያቄም ነበር፡፡ከዘጠኙ ታሳሪዎች መካከል ስምንቱን በፍርድ ቤት ሲወክሉ የቆዩት ጠበቃ አምሀም ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ቀደም ብለው ቅጥር ግቢው ተገኝተዋል፡፡
አራት ሰዓት እንደሚጀመር የተገመተው ችሉቱ እስከ አምስት ከሩብ ድረስ በሌሎች ጉዳዩች ተወጥሮ ቆይቷል፡፡ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ነፍጥ ባነገቱ ወታደሮች ታጅበው መምጣት የነበረባቸው ኪቦርድ አንጋቾች እስራት ያልበገረውን ተስፋቸውን እየዘሩ ሊመጡ አልቻሉም፡፡ሁኔታው አግራሞት የፈጠረባቸው የተወሰኑ ጋዜጠኞች ወደ መዝገብ ቤት በማምራት መረጃ ጠየቁ፡፡የተሰማው በግቢው ውስጥ የነበሩትን ጠበቃ አምሀ መኮንንን ጨምሮ ያስገረመ፣ ያሳዘነና ያሳፈረ ነበር፡፡ከጠበቃው ጋር ዳዊት ሰለሞን ያደረገው አጠር ያለ ቃለ ምልልስ እንደወረደ እነሆ፡፡
ጥያቄ---ወደ ፍርድ ቤቱ ሲመጡ በአእምሮዎ ያመላልሱት የነበረው ነገር ምንድን ነው?
ጠበቃ አምሀ---ምናልባት ምርመራ ባለመጨረሳችን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠን ይላሉ እያልኩ ነበር፡፡ይህንን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ በምን አይነት መንገድ እንደሚመልስ ለማወቅም ፈልጌ ነበር፡፡የሆነው ግን በፍጹም ያልጠበቅነው ነገር ነው፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ያመሩ ጋዜጠኞች ‹‹የልጆቹ መርማሪ ነኝ ያለ ሰው ምርመራዬን በመጨረሴ ለአቃቤ ህግ አስተላልፊያለሁ›› በማለቱ መዝገቡ እንደተዘጋ እንደተነገራቸው እንደነገሩኝ እውነት መሆኑን አጣርቻለሁ፡፡
ጥያቄ --- ሁኔታውን እንደሰሙ ምን አደረጉ?
ጠበቃ አምሀ -- እኛ ከቀጠሮው ሰዓት ቀደም ብለን ግቢው ውስጥ ተገኝተን መርማሪው እንዲህ ዓይነት ነገር ሲያቀርብ መስማት ነበረብን፡፡ በፍጹም እንዲህ አይነት መደረግ እንደሌለበት ቅሬታ እንደተሰማንና የተፈጸመው ነገር ህገ ወጥ መሆኑን ለዳኛው ተናግረናል፡፡
ጥያቄ -- ህገ ወጥ የሆነው ምንድን ነው?
ጠበቃ አምሀ --ለፖሊስ ልጆቹን ለተጨማሪ 28 ቀናት እንዲያስር ፈቅዶለት የነበረው ፍርድ ቤቱ ነው፡፡እስካሁን ድረስ ደምበኞቼ የታሰሩት በፍርድ ቤት እውቅና ነው፡፡ከዛሬ አራት ሰዓት ጀምሮ ግን ደምበኞቼ የታሰሩት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመሆኑ እስራታቸው ህገ ወጥ ነው፡፡ፖሊስ ልጆቹን ፍርድ ቤት አቅርቦ ምርመራውን መጨረሱን ማስረዳትና ክስ የሚመሰርት ከሆነም ማሳወቅ ይገባው ነበር፡፡የሚመሰርተው ክስ ዋስትና የሚያስከለክልና የማያስከለክል መሆኑን መወሰን የነበረበት ፍርድ ቤቱ ነው፡፡ይህ ሳይደረግ መዝገቡ ተዘግቷል መባሉ ህገ ወጥ ነው፡፡
ጥያቄ -- ከአሁን በኋላ ለደምበኞችዎ ሊያደርጉ የሚችሉት ነገር ምንድን ነው?
ጠበቃ አምሀ -- ሰኞ ወይም ማክሰኞ የደምበኞቼ የአካል ነጻነት እንዲከበር ክስ እመሰርታለሁ፡፡ሰኞን የምንጠብቀው እንደተናገሩት ክስ የሚመሰርቱ ከሆነና የት እንደሚመሰርቱ ለማጣራት ነው፡፡
ጥያቄ --በ‹‹ሃብየስ ኮርፐስ›› ደምበኞችዎ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ክስ የምትመሰርቱት በየትኛው ፍርድ ቤት ነው?
ጠበቃ አምሀ --ክሱን የምንመሰርተው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው፡፡
ጥያቄ --ደምበኞችዎን በማዕከላዊ በወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲጎበኙ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ነገር ግን እስካሁን ድረስ አቤል ዋበላን ሰዎች ማግኘት እንዳልቻሉ እየተናገሩ ነው ምክንያቱን ለማጣራት ሙከራ አድርጋችኋል?

Cases of Zone9 Bloggers & Journalists referred to the Court in the Absence of both the Defendants & their Lawyer

The first instance court of Arada bench was expected to wrap up the pre-trial ‘hearing’ which took more than 70 days and yet the bloggers were not even brought before the judge. Mr.Amaha Mekonnen, a lawyer defending the bloggers & journalists who are detained on unclear but shaping up to be on terrorism charges expected the first instance court at Arada bench to rest the pre-trial procedure last Saturday. The court had set the 12th July hearing for closing arguments but with an extraordinary move the police referred the case to the Federal High Court without even the presence of neither the defendants nor their defense lawyer himself. The shift overlooked the court and contravenes even the standard procedure of the biased justice system. The lawyer speaks to Dawit Solomon, a journalist based in Addis Ababa about the issue. Here are the translated excerpts from the interview.
DAWIT: What were your thoughts on your way to the court for Saturday’s procedure?
Defendants’ lawyer Ato Amaha briefing the  crowd
Amaha Mekonen Defense Lawyer of Zone 9 bloggers & Journalists
AMAHA: I expected the police might demand for more time to wrap up their interrogation as usual. I also sought to see how the court would reply to this repeated claim of the police. Nevertheless, to the shock of me and all people who were here what unfolded was really baffling. Since the detainees were not brought to the court some journalists went straight to the court’s registrar to ask about the case. Then a person who claimed himself as “the detective” of the case told the journalists since he is done with the interrogation he submitted the case for a prosecutor. He further claimed that the case is closed. This was what I was told by the journalists then I also went in to verify which I found it true. They closed the case without the presence of neither my clients nor me who is representing them.
DAWIT: What action have you taken after you heard?
AMAHA: We have been to court’s compound way earlier than the scheduled time of the hearing. When the detectives/police officers presented their arguments it should be in our presence. I have tried to explain our disappointment to the judge. This is basically a grave breach of law.
DAWIT: So what is the encroachment? Where is the breach of the law?

Sunday, July 13, 2014

የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ሶስቱ ጋዜጠኞች በሌሉበት መዝገባቸው ተዘጋ

ሁለት ወር ከሃይ ቀናት በእስር ያሳለፉት ስድስቱ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች በሶስት የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ፡በሰንበት ሲመላለሱ ከርመው ትናንት ቅዳሜ በሌሉበት መዝገቡ ለዓቃቤ ህግ መተላለፉን በቦታው ተገኝታ የነበረችው ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ዘገበች። ሃምሌ ዓምስት ተቀጥረው የነበሩት ጋዜጠኞች ተስፋለም፡ወልደየስ፡ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፡ኤዶም፡ካሳዬ እና የህግ መምህር እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ዘልዓለም ክብረት፡ እንዲሁም የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃነ፡በአጠቃላይ ስድስቱ ተጠርጣሪዎች ፍርድቤት ይቀርባሉ ተብሎ እስከ ጠዋቱ አምስት ሰዓት ተኩል ድረስ ሲጠብቅ የነበረው ችሎት ተከታታይ በመጨረሻም ችሎቱ ማብቃቱ ተነግሮታል። ቆይታው ግራ ያጋባቸው፡ጠበቃው አቶ አመሃ መኮንን ሁኔታውን ለማጣራት ችሎት፡ገብተው ሲጠይቁ፡ "ውይ አለቀኮ"፡ የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። "እዚህ ውጭ ቁጭ ብለን እየጠበቅን እንዴት ነው አለቀ የሚባለው"፡ ብለው ላነሱት ጥያቄም "ስንጠራችሁ፡ አልሰማችሁም፡ የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል"። "ግቢ፡ውስጥ ከሶስት መቶ ሰው በላይ ተቀምጦ የእነርሱን ጉዳይ እየጠበቀ፡ጠበቃቸው እዚህ እያለ እንዴት፡አልሰማችሁም ይባላል" ብለው ቢጠይቁም ጠበቃ አይስፈልጋችውም ነበር። የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። "ተጠርጣሪዎቹስ መች ቀረቡ?" ብለው ሲጠይቁም "እነርሱ አይስፈልጉም ነበር፡ ፖሊስ ይህን መዝገብ ዘግቼ፡ጉዳዩን ለዓቃቤ ህግ፡ አስተላልፊያለሁ አለ። በዛ መሰረት መዝገቡ ተዘጋ" በማለት ምላሽ ሰጡት። 
ምንጭ: ኢካድፍ
የጦማሪው ማስታወሻ ለ78 ቀናት እና ማእልታት ምንም ዓይነት ክስ ሳይመሰርትባቸው የጓንታናሞ ታናሽ በሆነው ማእከላዊ እስርቤት የሚንገላቱት የኢትዮጵያ ተስፋዎች፡ ህይወት ላይ የምትጫወቱ ዳኛ፡ፓሊስና አቃቤህግ ተብዬዎች፡ታሪክ ፍርዱን ይሰጣችኋልትናንትው የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ጉዳይ የፍርድቤት ውሎ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ የሚባለው የህግ ስርዓት፡ ለእነማን እና በእነማን ጠለላ ስር እንድሆነ ለ101ኛ ጊዜ ፍንትው ብሎ ያሳያል። እነ ጠቅላይ ምኒስትር  ደሳላኝ ሃይለማርያም  አለ የሚሉን ህግ ተርጓሚ እና አስፈጻሚ ሚና እንዲህ ተደበላልቆ ትርጉም ያጣበት ጊዜ ላይ መድረሳችን፡ የዚህ አገር እጣ ፈንታ ከድጡ ወደማጡ   እያዘገመ  መሆኑን :ጥሩ አመላካች ነው።

Friday, July 11, 2014

ባለፈው ሚያዚያ የተቀሰቀሰውን የተማሪዎች ዓመጽ ተከትሎ መንግስት ሃያ ጠባብ ዓመለካት አላቸው ያላቸውን የኦሮሚያ ቲቪ ጋዘጠኞችን ከስራ አባረረ፡ ሲፒጄ

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ወይም ሲፒጄ በሚል የምጽሃረ ቃል የሚጠራው ዓለምዓቀፉ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ   ተሟጋች ቡድን ትናንትናው እለት በድረገጹ  ላይ እንዳስታወቀው፡ እነዚህ ሃያ የሚሆኑ በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚተዳደረው የኦሮሚያ ቴሌቪዥን ባልደረቦች ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከስራ ገበታቸው የተሰናበቱ ሲሆን በዓሁኑ ሰዓት መንግስት በሰበብ   አስባብ እንዳያስራቸው በመስጋት ተደብቀው እንደሚገኙ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ጋዜጠኛ ለሲፒጄ ከሰጠው ቃለመጠይቅ ለመረዳት ተችሏል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጁን 25 እነዚሁ ሰራተኞች ወደ ቴሌቪዥን ጣቢያው መግባት እንደማይችሉ በስራ ሃላፊዎቻቸው እንደተነገራቸው ገልጸው፡ በምን ምክንያት ውሳኔው ሊተላለፍባቸው እንደተቻለ ምንም የተገለጸላቸው ነገር አለመኖሩን ለሲፒጄ አስታውቀዋል። 
People demonstrate in Addis Ababa on May 24 against security forces who shot at students at a peaceful rally weeks eearlier in Oromia state. (Reuters/Tiksa Negeri)እንደሚታወቀው ባለፈው ሚያዚያ መንግስት ሊያጸድቅ ያቀደው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በዋና ከተማ ዙሪያ አካባቢዎች ላይ የሰፈሩ ገበሬዎችን ያፈናቀላል በሚል በተለያዩ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ከፍተኛ የተቋውሞ ሰልፍ አስነስተው በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ከፍተኛ አደጋ ደርሶ ነበር። የኦሮሚያ ቲቪ ጋዜጠኞች ይህንን ፖሊሲ የሚተች ነው ያሉትን ዘገባ እና የገዥው ፓርቲ ባለስልጣናት የተሳተፉበትን ስብሰባ ከተቃውሞ ሰልፉ አንድ ቀን ቀደም ብለው ማቅረባቸው ከስራ ለመባረራቸው መነሾ ሊሆን እንደሚችል አክለው ገልጸዋል። ይህ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገው ጋዜጠኛ ለሲፒጄ በሚከተለው መልኩ ገልጾታል።
"መንግስት እሱ በሚፈልገው/በሚመርጠው አስተሳሰብ ሊያጠምቅህ ካልቻለ፡ ከስራ ገበታህ ያፈናቅልሃል"
የጋዜጠኞቹን መባረር ተከትሎ አቶ በረከት ስምኦን እና የፋና ብርድካስት በአዳማ ከተማ ባዘጋጁት ግምገማ የኦሮሚያ ጋዜጠኞች እንዲሳተፉ የተደረጉ ሲሆን፡ ዓላማው የጋዜጠኛውን ክህሎት እና የስራ ብቃት ለማጎልበት ሳይሆን የጋዜጠኞቹን የፖለቲካ አቋም ለመሰል የተሸረበ ሴራ እንደነበረ፡ በዚሁ ግምገማ ላይ የተሳተፉ ጋዜጠኞች ተናግረዋል። ግምገማውን ያዘጋጁት አንዳንድ ካድሬዎች ለጋዜጠኞቹ እንዳሰረዱት፡ የተቋውሞ ሰልፉን በተመለከት የኦሮሚያ ቲቪ ሲያቀርቡት በነበረው ዘገባ ላይ መንግስት ደስተኛ እንዳልነበር ነው። 
እንደሲፒጄ ዘገባ፡ እነዚህ ከስራ የተባረሩት ጋዜጠኞች ከአምስት ዓመት በላይ የስራ ልምድ እንዳላቸው ለመረዳት ተችሏል።
ምንጭ ሲፒጄ   

Ethiopian Heart Patients are dying due to the imprisonment of A Renown Ethio-Swedish Cardiologist for 13 months

A prominent Ethio-Swedish cardiologist from Sweden changed the course of medicine and saved many lives in Ethiopia, but now Dr.Fikru Maru is wrongfully imprisoned since May, 2013. Ethiopian officials accused him of having a secret contact with a former chief of Ethiopian custom's authority, who has been also charged with suspicion of corruption and in jail since last year.
Right now, Dr. Fikru is placed in " Kilinto Prison which has
  • 3 different zones, and Dr. Fikru belongs to zone 2,
  • 7 different rooms, each room carries around 90 prisoners,
  • is located in one of the hottest areas of Ethiopia (an average temperature between 35-40 degree Celsius),
  • water is very scarce, malaria is rampant and sanitation at its worst.
It's not only sad but inhumane for a very well known cardiologist to be treated like petty criminals for the crimes he neither committed nor charged with. He is sleeping on the floor on the flea and mice infested cell, thousands Kilometers away from his closest family who live in Sweden. According to his first ever interview he made since his arrest last year with the Swedish National Television on July 10th 2014, what saddens him most at the moment is some of his cardiac patients are dying since he is the only person who could change cardiac defibrillators implanted in their body. His Swedish colleagues who used to go and treat patients at Addis Cardiac Hospital, are not going there for fear of being detained by the Ethiopian officials.
As a family member said some days ago,

Thursday, July 10, 2014

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የልብ ህክምና ሆስፒታል መስራች ኢትዮስዊዲሽ የልብ ሃኪም ለ13ወራት ያለምንም ክስ እና ፍርድ ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ ይገኛሉ


Fikru Maru. Privat ኢትዮጵያ አገሬ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ
የስዊድን ቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ ጠዋት እንደዘገበው የ63 ዓመት እድሜ ያላቸው ዶክተር ፍቅሩ ማሩ  በትውልድ ኢትዮጵያዊ  በዜግነት ስዊድናዊ ሲሆኑ፡ እዚህ ስዊድን አገር ውስጥ አሉ ከሚባሉ በጣት የሚቆጠሩ የልብ ሃኪሞች በግምባር  ቀደምትነት ይጠቀሳሉ። ጣቢያው ዶ/ሩ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ  ለመጀመሪያ ጊዜ በልጃቸው አማካኝነት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ መረዳት እንደሚቻለው፡ እኝህ አገር ወዳድ እና በጎ አድራጊ የልብ ህክምና ባለሙያ እንደተራ ወንጀለኛ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቂሊንጦ እስርቤት ከዘመድ፡ከወዳጅ፡ እንዲሁም ከሚወዱት ሙያቸው ተገልለው ሳይማር ያስተማረኝን ወገኔን ልጥቀም ባሉ፡ በእርጅና ዘመናቸው፡ እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ። በትናንትናው  እለት በዋለው ችሎት ላይ  ተገኝተው የነበሩት የዶ/ሩ ልጅ ኤሚ ፍቅሩ ለቴሌቪዥን ጣብያው እንዳስረዱት፡ አባታቸውን ላለፉት ሶስት  ወራት ለመጎብኘት እንዳልቻሉ ነው። በዋና ከተማዋ የሚገኘውን እና ብቸኛ   የሆነውን አዲስ  ልዩ የልብ ህክምና ሆስፒታል  ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ከአምስት ዓመታት በፊት ያቋቋሙት እኝህ አንጋፋ    የህክምና ባለሙያ፡ እሳቸው ብቻ ሊቀይሩት የሚችሉት ካሪዲያክ ደፊብሪለተር cardiac defibrillator የተባለ ወሳኝ ህይወት አድን መሳሪያ የተገጠመላቸው የልብ ህመምተኞች በእሳቸው መታሰር ምክንያት በመሞት ላይ እንደሚገኙ እጅጉን እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል። ዶ/ር ፍቅሩ ተከሰው የታሰሩት በሙስና  ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩት ከቀድሞው የጉምሩክ ሃላፊ ጋር  ምስጢራዊ ግንኙነት አላቸው በሚል ቢሆንም፡ እስካሁን ድረስ ለቀረበባቸው  ክስ፡ ፓሊስ ምንም ዓይነት ተጨባጭ ማስረጃ ሳያቀርብ ላለፉት  አስራ ሶስት ወራት በከፍተኛ እንግልት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።  እጅግ የሚያሳዝነው የሙያ አጋራቸው የሆኑት የቀድሞው የጤና ጥበቃ ምኒስትር እና በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር በመሆን በማገልገል  ላይ የሚገኙ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ይህ ኢሰብዓዊ እና ኢፍትሃዊ ድርጊት እልባት አግኝቶ ዶ/ር ፍቅሩ በሙያቸው በሺሆች   የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የልብ ህምተኞችን ህይወት እንዲታደጉ ምንም ጥረት አለማድረጋቸው አንድ ቀን በታሪክ ፊት ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።
ምንጭ፡ የስዊድሽ ቴሌቪዥን

Wednesday, July 9, 2014

የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ የነበሩት እና በየመን መንግስት ባለስልጣናት ተላልፈው የተሰጡት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢቴቪ ላይ ቀረቡ

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ለማምራት ባለፈው ሳምንት ሰንዓ ዓየር ማረፊያ ላይ አውሮፕላን ለመቀየር ሲሉ በየመናውያን የጽጥታ ሃይሎች ከተያዙ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የተላለፉ የሚታወስ ሲሆን፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ እይታ የቀረቡት መንግስት በሚቆጣጠረው የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው። ዜና አቅራቢው ተመስገን በየነ ከወትሮው ለየት ባለ ንቃት እና ፈገግታ በመታጀብ አያቱ ሊሆኑ የሚችሉትን ግለሰብ አንተ እያለ በመዘርጠጥ ዜናው ሲያስደምጥ ነበር። አቶ አንዳርጋቸው በዚሁ ተቀናብሮ (ደበበ እሸቱ፡ ብርቱካን ሚዴቅሳ፡ ስዊድናውያን ጋዜጠኞቹን እና ሌሎችም በመቶ የሚቆጠሩ የቀድሞ እስረኞች ልብ ይሏል) በተሰጣቸው የንስሃ በሚመስል ቃለ ምልልስ ላይ፡ በእስር ላይ መዋላቸውን በጸጋነት እንደሚቀበሉት ሲናገሩ ተደምጠዋል። አጃኢብ ነው፡ ውድ የኢትዮጵያ ልጅ ስማ፣ ላልሰማ አሰማ ኢትዮጵያ ውስጥ ማእከላዊ የሚባል እስርቤት ሰላምህን የሚሰጥ ስለሆነ፡ ቦታ እንዳያመልጥህ ተሽቀዳደም። እቺ የተቀነባበረች ዜና የቀረበችው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሌሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የአቶ አንዳርጋቸው ደህንነት እንዳሳሰባቸው በመግለጽ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ዓለምዓቀፍ ዘመቻ በጀመሩበት ሰዓት መሆኑ እነሱም ድራማ መስራት አይሰለቻቸው እኛም መመልከት ያሰኛል። የብሄራዊ ደህንነት ድርጅቱ በተጨማሪ ለተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎች እና ደጋፊዎች፡ ለጋዜጠኞች እና ጦማሪያን እንዲሁም በዞን ዘጠኝ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ በሙሉ በጸረሽብሩ "ህጋችን" ለእስር ከመዳረግ እንደማንድን በገደምዳሜ ተነግሮናል። ለማንኛውም ተመስገንን እንዲህ ያስፈነደቀው ዜና ከዚህ በታች በሚገኘው ቪድዮ ላይ መመልከት ይችላሉ። 

Saturday, July 5, 2014

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የማዕከላዊ ፖሊሶች የእምነት ክህደት ቃል በኃይል አስፈርመውናል ይላሉ

ወከባው ቀጥሏል

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በስድስቱ ጦማሪያንና በሦስቱን ጋዜጠኞች ላይ የፌደራል ፖሊስ የተለያየ ምክንያት እየሰጠ ቀጠሮ የሚያራዝመውን ሁለት መዝገብ አንዴ ሲያቀራርበው መልሶ ደግሞ ሲያራርቀው ቆይቶ አሁን ደግሞ መዝገቦቹን መልሶ አቀራርቧቸዋል።   
ችሎቱን በፍርድቤቱ በመገኘት የዘገበችው ጽዮን ግርማ ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረገጽ ከላከችው ዘገባ ለመረዳት እንደሚቻለው እስረኞቹ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉበት ኹኔታ ፖሊስ ያረቀቀውን የእምነት ክህደት ቃል ተገደው እንዲፈርሙ አድርጓቸዋል። የሦስቱ ብሎገሮች አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን ቀጠሮ ሰኔ 22 ቀን 2006 ዓ.ም እንዲቀርቡ የሚል የነበረ ሲኾን ከጠዋት ጀምሮ ችሎቱን ለመታደም የመጣውን ቤተሰብ፣ ጓደኞቻቸው፣ ጋዜጠኞች፣ ዲፕሎማቶችና የወጣቶች ደጋፊዎች በአጠቃላይ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጋ ሰው ከችሎት ውስጥ የሚሰማውን አዲስ ነገር ለመጠበቅ በግቢው ውስጥ ቆመው ነበር። ከጠዋቱ አራት ሰዓት አካባቢ