Thursday, May 31, 2012

ለታደሰ ሙሉነህና የእሁድ ጠዋት ፕሮግራም መታሰቢያ

ኧቤት የዚህን ተወዳጅ ፕሮግራም መግቢያ ሙዚቃና የታደሰ ሙሉነህ ማራኪ ድምጽ በስንት ዘመኔ ስሰማው የተሰማኝ የደስታና የሃዘን ቅልቅል ነው፦( ታደሰ ነፍስህ በሰላም ትረፍ።  በኢትዮጵያ ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥንና ሌሎች ሚዲያዎች ከ40 ዓመታት በላይ ያገለገለው ጋዜጠኛ ታደሰ ሙሉነህ ቀብር ባለፈው ዓርብ ግንቦት 16 2004 ዓ᎐ም᎐ በገነተ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ የ 64 ዓመቱ ጋዜጠኛ ታደሰ ሙሉነህ በኢትዮጵያ ሬዲዮ ከዜና አንባቢነት እስከ ዜና ዋና አዘጋጅነትና በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ከማገልገሉም በላይ፣ ከ1970ዎቹ መጀመርያ ጀምሮ ተወዳጅ የነበረው ‹‹የእሑድ ጧት ፕሮግራም›› መሥራችና ዋና አዘጋጅ ነበረ፡፡ 
አቶ ታደሰ ጡረታ ከወጣም በኋላ ከሙያው ሳይለይ የራሱን ማስታወቂያ ድርጅት በማቋቋም የማስታወቂያ ሥራዎችን ከማከናወኑ ባሻገር፣ በሸገር ኤፍኤም የ‹‹እሑድ እንደገና›› ፕሮግራም አዘጋጅና የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የራዲዮ ፕሮግራም ይመራ ነበር፡፡ በሙያው ካገኛቸው በርካታ ሽልማቶች መካከል ከኢትዮጵያ የሥነ ጥበባትና መገናኛ ብዙኀን ሽልማት ድርጅት ያገኘው በዋናነት ይጠቀሳል፡፡
ታደሰ ሙሉነህ እና ባልደረቦቹ (ባልሳሳት የአሜሪካን ድምጽ አማርኛ ክፍል ባልደረባ አዲሱ አበበ አንዱ ነበር)  በኢትዮጵያ የመዝናኛ ሬዲዮ ፕሮግራም ዘርፍ

Tuesday, May 22, 2012

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በጣም አዝነናል


እንዴት ከረማችሁ?
ያለፈው ሳምንት እንዴት ነበር የእናንተን እንጃ የኔ ግን ለየት ያለ ነበር? ከባድ ሃዘን ላይ ነኝ መቼም በተከበሩ ጠቅላይ ምንስትራችን ላይ የወረደውን መከራ ያየ አገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ በሙሉ (ይሄ እነዚህ በአውሮፖ እና አሜሪካ የጠቅላይ ምኒስትራችንን እግር እየተከተሉ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉ ጸረ ልማት እና ዲሞክራሲ ተቃዋሚዎችን አይመለከትም) ቢያንስ ቢያንስ ሰባት ቀን እንዳገራችን ባህል ፍራሽ መሬት አውርዶ በመተኛት፡ከል በመልበስ የአገራችንን በምግብ ራሳችንን የመቻል ስኬት ልምድ ለመጋራት በሄዱበት ወቅት ክብርና ዝናቸው በአንድ አሸባሪ ጋዜጠኛ አማሪካን አገር ውስጥ መገፈፉን በመቃወም ልማታዊ ሃዘኑን መግለጽ አለበት። 
ታሪኩ እጅግ አሳዛኝ ስለሆነ ጽሁፉን ማንበብ ከመጀመራችሁ በፊት  ባጠገባችሁ የጨርቅ ወይም ወረቀት እንባ ማበሻ ብታዘጋጁ የሚመረጥ ሲሆን አኬልዳማ ድራማን እንዲያዩ ያልተፈቀደላቸው ህጻናትም ባካባቢው ባይኖሩ ተመራጭ ነው። በሉ እንግዲህ ተዘጋጁ። በመጀመሪያ ከዚህ በታች ያለውን ጥቅስ ልተርጉምና ወደ ዝርዝሩ የሃዘን ዜና እገባለሁ። የሚከተለውን ጥቅስ የተወሰደው አምባገነኖችን ማሸነፍ፦በአፍሪካና በመላው የሚገኙ አምባገነኖችን መታገያ ከተባለው በእውቁ የጋና ኢኮኖሚስት ፕሮፌሰር ጂዮርጅ አዬቴ ከተጻፈው መጽሃፍ ሲሆን ጥሬ ትርጉሙም እንደሚከተለው ነው። እጅግ የተከበረ አምባገነን መሪ የለም፧ ጥሩ አምባገነን መሪ የሞተው ብቻ ነው። There is no benevolent dictator. The only good dictator is a dead dictator”.*
Prof. George Ayittey (America-based Ghanaian Economist). ይቅርታ አማርኛው ጥሩ ባይሆንም ትርጉሙ ከእንግሊዘኛው ይዘት ጋር ተቀራራቢ ያለው ይመስለኛል። በተረፈ በትርጉም ስራ ላይ እውቀት ያላችሁ ልታርሙኝ ትችላላችሁ።  እንግዲህ ተዘጋጁ ይሄን አስከፊ ትዕይንት ለመመልከት። 

Saturday, May 19, 2012

Ethiopian Tyrant Discredited at G-8 Summit


There is no benevolent dictator. The only good dictator is a dead dictator”.*
Prof. George Ayittey (America based Ghanaian Economist). 

First of all, 99 percent of us, Ethiopian people living at home and abroad, were sad and angry when we heard the news about the invitation of our benevolent leader to the G-8 summit by the Obama administration. We changed our minds after seeing what happened on Friday, May 18th 2012. We owe the American president Barack Obama for inviting and hosting our "leader" in Washington DC to discuss the world’s "food security" not because we agree with the premise of this invitation, but because a young exiled Ethiopian journalist, Abebe Gellaw, who is charged with terrorism/treason charges in absentia, gave your Ethiopian ally aka Meles Zenawi the taste of his medicine - humiliation. We, 99 percent of Ethiopians all over the world, indebted to those 20 seconds which allowed us to watch/witness your ally being shocked/humiliated/embarrassed in front of the whole world; had it not been for your gracious invitation, we might never ever have seen

Wednesday, May 16, 2012

ነብይ በአገሩ አይከበርም


መቼም በልባችሁ ዛሬስ ደግሞ ሰበካ ጀመረ ሳትል አትቀሩም። ኧረ ከየት ብዬ፡በየትኛው እውቀቴ። የዚህ ጹህፍ ዓላማ ከሰበካ ጋር በጭራሽ ግንኙነት የለውም፡ጥቅሱን የተጠቀምኩበት ባለፈው አስራምስት ቀን ታስቦ የዋለውን የዓለምዓቀፉን የፕሬስ ነጻነት ቀንን ከተሸላሚዎቹ "አሸባሪ" ጋዜጠኞቻችን ጋር ለማነጻጸር ያህል ብቻ ነው የተጠቀምኩበት። ያው እንደምታውቁት የዓለምዓቀፉ የፕሬስ ነጻነት ቀን በፈረንጆቹ ግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ በመላው ዓለም ታስቦ የዋለ ሲሆን ኢትዮጵያን የመሳሰሉ በዴሞክራሲያዊነት በጋዜጠኞች አያያዝ እጅግም የማይታሙ አገሮችም ቀኑን በተለያዩ መንገድ አክብረውታል፡አጃኢብ አለ ማን ነበር እሱ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ በእስር ላይ የሚገኙት አሸባሪ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ማለትም እስክንድር ነጋና ርዕዮት አለሙ ከሁለት የተለያዩ በአሜሪካ የሚገኙ የፕሬስ ነጻነት ተሟጋቾች ለሽልማት አጭተዋቸዋል። ፔን አሜሪካን ማዕከል ጋዜጠኛ/ብሎገር እስክንድር ነጋን የዚህ ዓመት (2012 ዓ᎐ም᎐) የፔን/ባርብራ ጎልድስሚትዝ የመጻፍ ነጻነት አሸናፊ ብሎ የሰየመው ሲሆን፡ ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል ለባለቤቷ የተበረከተውን ሽልማት ሜይ 1/2012 ዓ᎐ም᎐ ኑውዮርክ ከተማ በመገኘት ተቀብላለች። እንደሚታወቀው ሰርካለም የ 1997  ዓ᎐ምን  ምርጫ ተከትሎ በተከሰተው ብጥብጥ ምክንያት ከባለቤቷ ጋር ለ17 ወራት በታሰረችበት ወቅት ልጃችውን ናፍቆት እስክንድርን እንደተገላገለች የምንዘነጋው አይደለም። በጣም የሚገርመው ግን ሰርካለም እንደባለቤቷ ጋዜጠኛ ብቻ ሳትሆን የ 2007ቱ የዓለምዓቀፉ የሴት ጋዜጠኞች ተቋም ጀግና ጋዜጠኛ ተሸላሚ ነች። መቼም ምንይልክ ቤተመንግስት ውስጥ የሚኖሩ መሪዎቻችን እነዚህ አሜሪካኖች አበዱ ወይ ሳይሉ አይቀሩም።
ኧረ ገና ምን ታይቶ፡የእስክንድር ነጋ ሲገርማቸው ይባስ ብለው

Saturday, May 12, 2012

I accuse Tribunal 12

I came home on Saturday night (May 12th) very exhausted, hungry and sad after "attending" the so-called "We accuse Europe" meeting organised by Tribunal 12 at Kulturhuset in Stockholm. First, they or their partners posted a wrong programme schedule, which said that there would be a MANIFESTATION between 10-11:30 AM at Sergelstorg, but when my compatriots from the Ethiopian Refugees Association and I arrived at the scene, it was, to our dismay, completely empty, except for the huge screen on which a live-stream about the event was being broadcasted. By the way, I heard the same disappointments from many participants of the meeting and onlookers, who were deceived by this huge PR stunt, but found it to be not at all close to their expectations on the ground.   
We waited until 11 o'clock and then we decided to ask the person who e-mailed me that we are welcome to the event, but she was nowhere to be seen. No one could tell us why; it was so disorganised that we had to sit for nearly four hours before somebody explained to us that the protest would actually be held at 2 o'clock in the afternoon. And after a while, we watched people enter showing tickets, and we were wondering whether one had to pay in order to attend a meeting? So, I went there and asked the women who was standing at the entrance, and they told me yes. I asked how much the fee was, and they said 100 Swedish kronor per session or 350 Swedish kronor per day. Hmm, we never heard people actually pay to attend a meeting; in our country it was the other way around . So, I told the receptionists that we're refugees and we don't have that kind of money. And one of the organisers told us

Wednesday, May 9, 2012

Spoilt Freedom in the Name of Arts



I hope everybody read/watched/heard about the outcry over CakeGate in Sweden. I have been/am one of art-illiterates who were revolted, insulted by such a crude, racist and so called art installation held at Moderna Museet in Stockholm on April 15th, 2012 to raise 'awareness' about the female genital mutilation (FGM). Hmm, some of you may wonder where the hell I have been all these days since this issue has been in the spotlight for the past few weeks. Well, I just wanted to strip-off my racial, emotional baggage against this 'provocative art', compose myself and take my time to think reasonably and logically to comprehend the intent of this installation before I jump into any 'shallow' interpretation. Sorry, it didn't work folks, and it will never work no matter how much I attempt to detach my racial and emotional background from this sensitive subject. For me, this situation looked like sadomasochistic, cannibalistic fetish staged at the expense of one of the most painful and horrific practices in which millions of girls/women had/have to go through in some parts of Africa and some Middle-Eastern countries.
I relate myself on different levels to this practice.

Monday, May 7, 2012

በስዊድን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቋውሞ ሰልፍ በሜይዴይ

ሚያዚያ ፳፫/፳፻፬ ዓ/ም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በስዊድን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በየዓመቱ በሚከበረው የሜይዴይ በዓል ላይ በመገኘት የህውሃት መንግስት በኢትዮጵያ እያካሄደ ያለውን በኒዮኮሎኒያሊዝም እና በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ዜጎችን ከሚኖሩበት የማፈናቀል ዘመቻ፡የመሬት ቅርጫ፡ እንዲያቆም እንዲሁም ያለአግባብ የታሰሩ ጋዜጠኞችንና የፖለቲካ እስረኞችን ባስቸኳይ እንዲፈታ የተቋውሞ ሰልፍ በማድረግ ጠየቁ። ከዚህ በተጨማሪም የዓለም መንግስታት በከፍተኛ ሁኔታ በህውሃት መንግስት በጭቆና ቀምበር ለሚሰቃየው የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል አጋርነቱ እንዲያሳይና አምባገነን ለሆነው መለሰ ዜናዊ  የሚሰጠውን ማንኛውንም እርዳታና ትብብር እንዲያቋርጥ በተቋውሞ ሰልፉ ላይ ጠይቀዋል።

Saturday, May 5, 2012

የጠቅላይ ምኒስትራችን ህልውና ሌላ የእኛ ህልውና ሌላ


ICT helps ensure our survival” Meles Zenawi 5th International on ICT for Development, Education and Training March 19, 2008
ከዚህ በላይ የተመለከተው ጥቅስ የተወሰደው የተከበሩት ጠቅላይ ምኒስትራችን በ 5ኛው ዓለምዓቀፍ የመረጃ ከምፒውተር እና ቴክኖሎጂ ስብሰባ ላይ እ᎐አ᎐አ᎐ በ2008 ዓ᎐ም᎐ ከተናገሩት የተወሰደ ሲሆን ግርድፍ ትርጉሙም እንደሚከተለው ነው "የመረጃና ከምፒውተር ቴክኖሎጂ ህልውናችንን እንድናረጋግጥ ይረዳናል"። ድንቅ አባባል ናት አይደል፦በዛን ዓመት "ህልውናችንን" ሲሉ የሰማ ኢቺ ውስጠ ወይራ ያልገባ ቋንቋ ያልገባው ሁሉ አቤት በቃ በአጭር ጊዜ ውስጥ እኝህ ምንም የማይሳናቸው መሪያችን ከዓለም ተርታ በ1ኛ ደረጃ አሰልፈውን  ህነትን፤ በሽታን፡ድንቁርናን፡ረሃብን፡ደህና ሰንብት ብለን የመኖር ዋስትናችንን የምናረጋግጥበት ዘመን እሩቅ እንደማይሆን ቢያልም አይፈረድበትም "ህልውናችንን ሲባል እነማንን እንደሚያመለክት ዛሬ ዛሬ ገሃድ እየሆነ መጥቷል። ለዚህም ይመስላል የተከበሩና የተወደዱ ጠቅላይ ምኒስትራችንና የስራ ባልደረቦቻቸው በከፍተኛ ደረጃ ከወጭ የሚያገኙትን ብድር/እርዳታ እና ከሃገር ውስጥ ከግብር ከፋዩ የሚሰበስቡትን በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ዜጎችን በተለያየ መንገድ