Wednesday, December 4, 2013

ህውሃት ሰማያዊ ፓርቲ የዳግማዊ አጼ ምንይልክን መቶኛ ዓመት ሙት፡ዓመት እንዳያከብር አገደ

የሰማያዊ ፓርቲ የአፄ ምኒልክ ኛ እረፍት አመትን በተለያዩ ዝግጅቶች አስቦ ለመዋል በጃንሜዳ የመሰብሰብ ፍቃድ እንዲሰጠው ጥያቄ አቅርቦ ነበር፣ ይሁንና መንግስት ጥያቄውን ተልካሻ ምክንያቶችን በመደርደር ውድቅ ማድረጉን የሚገልጽ ደብዳቤ ለሰማያዊ ፓርቲ እንደደረሰው በመግለጫው አመልክቷል። የፊታችን ታህሳስ የእምዬ ምኒልክን  ኛ እረፍት በሰማያዊ ፓርቲ አዘጋጅነት እንደሚዘክር የታወቀ ነዉ፡፡ በፕሮግራሙ ላይም በርካታ ከሀገር ዉስጥና ከዉጪ ሀገር ምሁራን ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ይገኛሉ ተብሉ ይጠበቃል፡፡ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ሰማያዊ ፓርቲ ለዝግጅቱ በሚያስፈልጉ ጉዳዩች ላይ ስራ እየሰራ ይገኛል። በስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ አዋጅ መሰረትም ስብሰባ እንደሚያደርግ ለስብሰባና ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ደብዳቤ በትናንትናዉ እለት ያስገባ ሲሆን ዛሬ በደብዳቤ የተመለሰዉ መልስ እጅጉን አስቂኝና አጠያያቂ ሆኖ እንዳገኙት ብርሃኑ ተክለያሬድ የተባሉት የፓርቲው አባል  ይናገራሉ፡፡ በደብዳቤዉ ላይ ለምታደርጉት ስብሰባ እዉቅና ልንሳጣችሁ አንችልም ምክንያቱም የፖሊስ ጥበቃ መመደብ አንችልም የሚል ነዉ፡፡ የፅፈት ቤቱ ሀላፊ ተብዬዉ አቶ አሰግድ በንቀት ደግሞ ማናችሁና ምኒልክ ምናምን የምትሉት ደግሞ ምኒልክ ማነዉ በሚል በእብሪት የመለሰዉ መልስ አቶ ብርሃኑን በእጅጉ እንዳስገረማቸው አክለዋል፡፡ እንኳን ድንኳን ጥሎ ለመሰብሰብ ይቅርና ጎዳና ሙሉ ህዝብ በመላበት የሩጫ የሰልፍ መሰል የገዢዉ ፓርቲ መልካም ፈቃድ ያገኙ ፕሮግራሞች ከህዝቡ እኩል ፌደራል ፖሊስ ለጥበቃ እንደሚታዘዝላቸዉ እየታወቀ ፤ በሌላ መልኩም በድፍረት እንወጣለን ብለን በተለያየ ምክንያት በተጠሩ ሰልፎች ላይ ለድብደባ የሚላከው ቁጥር ስፍር የሌለዉ የፀጥታ ሀይል አሁን ምን ቢውጠው ነዉ የጥበቃ የሚሆን የሰዉ ሀይል ልናስተባብር አንችልም ስለዚህ ዝግጅታችሁን እዉቅና አንሰጠዉም መባሉ??? ይህ ከእብሪት በላይ ምን ሊሆን ይችላል!!!? አቶ ብርሃኑ ዝግጅቱ በታቀደለት ልኩ እንደሚፈፀም ተለመደ ፓርቲቸዉ ቁርጠኝነት ዋል፡፡ ሲፈልጉ ለጥበቃ የከለከሉትን ሀይል ለድብደባ ይላኩት!!! እኛ የምንዘክራቸዉ ፍርሃት ካልፈጠረባቸዉ ሞተዉም መንፈሳቸዉ ካልተለየን እምቢ ባይ አባቶቻችን ተወልደናል፡፡

ድል ለኢትየጵያ ህዝብ!!!


No comments:

Post a Comment