Wednesday, January 15, 2014

ባድመ የኤርትራ መሆኗን ኢትዮጵያውያን መቀበል ይኖርባቸዋል ዴቪድ ሺን በኢትዮጵያ የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር

ዛሬ ማምሻውን  የጀርመን ድምጽ ባሰራጨው ዘገባ በኢትዮጵያ የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ዴቪድ ሺን ኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነታቸውን ወደ ሰላማዊ መንገድ ለመመለስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊወያዩ ይገባል ሲሉ አሳሰቡ። አምባሳደሩ ፣ ከዚህ ቀደም በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት በተደረገ ድርድር ውጤት ባድመ የኤርትራ መሆኗን እትዮጵያውያን መቀበል ይኖርባቸዋል ብለዋል። ኤርትራ በበኩሏ ፣ አምባሳደሩ እንዳሉት ፤ ኢትዮጵያ በአሰብ ወደብ እንድትጠቀም ልትፈቅድ ይገባል። አምባሳደር ዴቪድ ሺን ፤ አሰብ የኢትዮጵያ ናት የሚለው እሳቤ ጊዜው ያለፈበት ነው ማለታቸውም ተጠቅሷል። እቺ ዛቻ መሰል ማስጠንቀቂያ በርቀት መቆጣጠሪያ የመተላለፏ አንድምታ ምንን ለማመላከት ነው። ለማንኛውም ዘገባውን አምባሳደሩ  አሜሪካን አገር ለሚገኘው የጀርመን ድምጽ ባልደረባ የሰጡት ቃለምልልስ እዚህ ጋር በመጫን ያዳምጡ። ህምምም ነገሩ  የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ወይስ ሌላ ድብቅ ዓላማ???

No comments:

Post a Comment