Friday, November 29, 2013

ከሳዉዲ ለመመለስ የተዘጋጁ ወገኖች አቤቱታ

በጅዳ ውስጥ ሸረፍያ በሚባል አካባቢ ወደሃገራችን እንግባ በሚሉ ኢትዮጵያዉያን እና በጸጥታ አስከባሪዎች መካከል ግጭት መፈጠሩ ተገለጸ። ለቀናት በጅዳ ቆንስላ መስሪያ ቤት ተጠልለው ከነበሩበት ቦታ ወደተጠቀሰዉ አካባቢ መጠለያ የተወሰዱ እነዚህ ወገኖች ላለፉት ሶስት ቀናት ወደ መጠለያው መግባት አልቻልንም ሲሉ በምሬት ይናገራሉ። ከሽሜሲ ጊዜያዊ ማቆያ ግቢ ውጭ አውቶቡስ ዉስጥ ያለ ምግብና ዉሃ መቆየታቸዉን የሚገልፁት እነዚሁ ወገኖች ሕጻናትና ነፍሰ ጡሮችና፤ እንዲሁም አቅመ ደካሞች ለከፋ አደጋ መጋለጣቸውን ጄዳ ለሚገኘዉ የዶይቼ ቨሌ ወኪል ነብዩ ሲራክ ገልጸዋል።  ዝርዝሩን እዚህ ጋር በመጫን ያዳምጡNo comments:

Post a Comment