Friday, September 28, 2012

የ2005 ዓ/ም አዲስ ዓመት አከባበር በስቶክሆልም

በስቶክሆልም እና አካባቢዋ የሚኖሩ በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን አዲሱን የኢትዮጵያ 2005 ወይም እንቁጣጣሽ መስከረም 8 2005 ዓ/ም ሃሉንዳ በሚገኘው የባህል አዳራሽ በመገኘት በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች አክብረውታል። የዚህን ዓመት በዓል ለየት የሚያደርገው ስዊድን ውስጥ ላለፉት 19 ዓመታት እዚህ አገር እና በመላው ዓለም ለሚኖሩና ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ዝግጅቶችን በማስራጨት የሚታወቀው የኢትዮጵያ ሬድዮ፡ እዚህ አገር ለ40 ዓመታት በስደት ለሚኖረውና በብእር ስሙ ሃይሉ ገሞራው ለሚታወቀው ታዋቂ ገጣሚና ደራሲ ሃይሉ ገብረ ዮሃንስ የዚህን ዓመት የክብር ሽልማት በማበርከቱ ነው። አንጋፋው እና ተወዳጁ አርቲስት ተሾመ አሰግድና ወጣቷ ድምጻዊ የዝና ነጋሽ በተለያዩ ጣእመ ዜማዎች የበዓሉን ታዳሚዎች አዝናንተዋል። Hundreds of Ethiopians who reside in Stockholm and its environs celebrated Ethiopia's New Year on September 8 2012 at Hallunda culture house. The voice of Ethiopia which has been on air for the last 19 years, honored famous Ethiopian poet/writer Hailu Geberyohannes a.k.a Hailu Gemoraw as 2004 Ethiopian of the year. Veteran singer Teshome Asseged and the young artists Yezena Negash entertained the public on that day.

No comments:

Post a Comment