-ተጠርጣሪው
ገዳይ በቁጥጥር ሥር ውሏል
በንፋስ
ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አቦ ማዞሪያ
ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሦስት ዓመታት በፊት
በተነሳ የመኖሪያ አዋሳኝ ድንበር ክርክር
ምክንያት የሦስት ሕፃናት እናትና አባት፣
የመከላከያ ሠራዊት አባል ነበር በተባለ
ተጠርጣሪ የካቲት 24
ቀን
2006 ዓ.ም.
ከቀትር
በኋላ በጥይት ተደብድበው ተገደሉ፡፡
የከባድ
ተሽከርካሪ ሾፌር መሆናቸው የተገለጸው አቶ
ዳንኤል ነጋሽና የቤት እመቤት ናቸው የተባሉት
ወ/ሮ
ምስለ ማሞ የመቶ እልቅና ማዕረግ በነበረውና
እስከ 1999 ዓ.ም.
ድረስ
የመከላከያ ሠራዊት አባል እንደነበረ በተገለጸው
ግለሰብ በጥይት ተደብድበው ሊገደሉ የቻሉት፣
በግልና በቀበሌ ይዞታነት ለሁለት በተከፈለ
ከመኖሪያ ግቢ ጋር በተያያዘ ተፈጥሮ በከረመ
የወሰን ውዝግብ ምክንያት መሆኑን ለማወቅ
ተችሏል፡፡
ተጠርጣሪ
ገዳይ ከሟቾች አጥር ጋር የተያያዘ የቀበሌ
ቤት ተከራይቶ ሲኖር፣ መውጫና መግቢያው በሟቾች
ግቢ ውስጥ እንዲሆን ለክፍለ ከተማው ወረዳ
ሦስት በማመልከቱ ይፈቀድለታል፡፡
የወረዳውን
ውሳኔ የተቃወሙት ባለይዞታዎች (ሟቾች)
ድርጊቱ
አግባብ አለመሆኑን በመግለጽ፣ ጉዳዩን ወደ
ፍርድ ቤት በመውሰድ ተጠርጣሪውንና ወረዳውን
ይከሳሉ፡፡ የክስ ሒደቱ ላለፉት በርካታ ወራት
የተጓተተ ቢሆንም፣