የነገሮች
ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡
‹‹ይህንን
ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መወያየት ክልክል ነው፡፡››
በማለት በተንጎላጀጀ ድምፅ ጠባቂው ተናገረ፡፡
ቀጠል አደረገናም ‹‹መነጋገር የምትችሉት
ስለቤተሰብ ጉዳዮች ብቻ ነው›› በማለት
ተናገረ፡፡ ይህን ከላይ ያለውን ሐሳብ የሚመለከት
ማንኛውም አንባቢ፣ ጉዳይ የተፈፀመው እዚህችው
እማማ ኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ አጃኢበኛ እስር
ቤቶች፣ ቤተሰብ መጠየቂያው እንደሆነ መጣራቱ
አይቀርም፡፡

ይሁንና
በመግቢያው ላይ ያለው ጽሑፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ
‹እናት› ከተሰኘውና እ.ኤ.አ.
በ1906
ከታተመው
የስመ ጥሩው ሩስያዊ ደራሲ ማክሲም ጎርኪይ
ታሪካዊ ልቦለድ ገፅ 102
ላይ
ነው፡፡ የዛሬ 108
ዓመት
አካባቢ ማለት ነው፡፡ አቤት ርቀቱ!...
ይህ
ርቀት ግን ለእኛ ምንም ማለት ያልሆነ ይመስላል፤
ለምን? ቢሉ
ዛሬም ይህንንና ይህን የመሳሰለውን አስፍተን
እየሠራን እንገኛለን፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ
ሁኔታዎች እየተጓዝን ያለነው የቁልቁለት ሩጫ
በእጅጉ አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል፡፡
የነገሮች
ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡