Showing posts with label ANC. Show all posts
Showing posts with label ANC. Show all posts

Saturday, December 7, 2013

ዝክረ ማንዴላ ወኢትዮጵያ

የማንዴላ እና የኢትዮጵያ ቁርኝት ከግማሽ ምዕተዓመት በላይ አስቆጥሯል። ኔልሰን ማንዴላ በአገራቸው እንዳይሰጣቸው  የተከለከሉትን ፓስፖርት ለመጀመሪያ ጊዜ በመስጠት ኢትዮጵያ ባለውለታ ስትሆን ይህንን የኢትዮጵያ ፓስፓርት በመጠቀም ማንዴላ ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀሱ አስችሏቸዋል። ከዚህ ባሻገርም ጠያራ (አውሮፕላን) አብራሪ የተመለከቱት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1962 ወደ አዲሰ ኣበባ ባመጣቸው ጠያራ ውስጥ ነበር። ይህ አጋጣሚ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በወቅቱ ተንሰራፍቶ በነበረው የዘር መድሎኦ በተያያዘ በነበራቸው አሉታዊ ተሞክሮ የተነሳ ከፍተኛ ግርምትን እና የጥቁር ዘር ማንነት ጥያቄ እንደጫረባቸው ለነጻነት የተደረገው ረዥሙ ጉዞ ( Long Walk To Freedom ) በሚል ባሳተሙት መጽሃፋቸው ላይ እንዲህ ሲሉ ገልጽውታል።