Wednesday, February 26, 2014

የዘነቡ ታደሰ የትዊተር ገጽ "የተጠለፈው" ይቅርታ የተከረቸመው የለውጥ ሃዋርያ ወይስ ኢሞራላዊ ምኒስትር ስለሆኑ?


 መንግሥት አካውንታቸው ተጠልፏል እያለ ነው
1924573_1397282537202040_1284874720_n
የሴቶች፣ የሕፃናትና የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ የካቲት 17 ቀን 2006 .. በትዊተር ማኅበራዊ ገጻቸው ላይ፣ ‹‹በተወዳጇ አፍሪካዬ ውስጥ ጥላቻና መገለል ቦታ የላቸውም፡፡
የአለባበስ ሥርዓት ወይም የፀረ ተመሳሳይ ጾታ ተጓዳኞች ሕጐችን ማውጣት የመንግሥታት ሥራ አይደለም፤›› በሚል የወጣው መልዕክት አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ መንግሥት ግን የሚኒስትሯ የትዊተር አካውንት መጠለፉን ገልጾ፣ ይህ መልዕክት የሚኒስትሯንም ሆነ የመንግሥትን አቋም አይወክልም ሲል
አስተባብሏል፡፡ በማህበራዊ ድረገጾች ማለትም ትዊተር እና ፌስቡክ መነጋገሪያ የሆነው ይህ የትዊተር መልእክት ሃያአራት  ሰዓት በላይ ሳይቆይ እንዲወገድ ተደርጎ የሚከተለው መልእክት በምኒስትሯ የትዊተር መዝገብ ላይ  እንዲሰራጭ ተደርጓል። Ethiopias-Minister-Zenebu-Tadesse-disclaims-pro-gay-tweets

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በኡጋንዳ የፀደቀውን ፀረ ተመሳሳይ ጾታ ተጓዳኞች ሕግ በመቃወም በሚኒስትሯ የትዊተር ገጽ ላይ የተጻፈው ይህ መልዕክት፣ በዓለም ዙሪያ ባሉ ተመሳሳይ ጾታ ተጓዳኝ ግለሰብ መብቶች ተከራካሪዎች አድናቆት ተችሮታል፡፡ ሆኖም ግን የሴቶች፣ የሕፃናትና የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ዓብይ ኤፍሬም፣ ‹‹መልዕክቱ በማይታወቁ ሰዎች የተጻፈ ሲሆን፣ የእሳቸውንም ሆነ የመንግሥትን አቋም የማይገልጽ ነው፤›› ብለዋል፡፡
አቶ ዓብይ አክለው፣ ‹‹ሚኒስትሯ ይህን የማኅበረሰብ ሚዲያ የሚጠቀሙት ሕዝቡ በቀጥታ ሊያገኛቸው የሚገቡ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ አዋጭ ሚዲያ በመሆኑ ነው፤›› ብለዋል፡፡ የትዊተር ገጻቸውን የሚያንቀሳቅሱት ራሳቸው ወይዘሮ ዘነቡ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ዓብይ፣ በገጻቸው ላይ በጠላፊዎች በተላለፈው መልዕክት ሚኒስትሯ ማዘናቸውን አስረድተዋል፡፡
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከማል የሚኒስትሯ የትዊተር አካውንት መጠለፉን አረጋግጠው፣ ‹‹የሚኒስትሯን አካውንት ጠልፈው በመግባት የእሳቸውንና የመንግሥትን አቋም የማይገልጽ መልዕክት ያስተላለፉት ግለሰቦች ጉዳይ ከተጣራ በኋላ፣ አስፈላጊው ዕርምጃ ይወሰዳል፤›› ብለዋል፡፡
የሚኒስትሯ የትዊተር አካውንት መቼ እንደተጠለፈ በውል ባይታወቅም፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ባን ኪ ሙን ተመሳሳይ ጾታ ተጓዳኞች እኩል መብት ይኑራቸው የሚል መልዕክታቸው፣ ጥር 1 ቀን 2006 .. በመዝገባቸው በድጋሚ ትዊት ተደርጓል፡፡ ሚኒስትሯ በዚህ የትዊተር ገጻቸው የተላለፉት መልዕክቶች በእሳቸው እንዳልተጻፉ ገልጸዋል፡፡
በአገሪቱ የተሻሻለው የወንጀል ሕግ ከአንቀጽ 629 እስከ 631 ድረስ በሰፈረው መሠረት የተመሳሳይ ጾታ  ባላቸው ግለሰቦች መካከል የሚደረግ ማንኛውንም ወሲባዊ ግንኙነት እስከ አሥራ አምስት ዓመት ድረስ በእስራት ያስቀጣል፡፡
ሚኒስትሯን በትዊተር ገጽ ላይ የሚከተሏቸው 1,600 ሰዎች የነበሩ ሲሆን፣ ማክሰኞ ምሽት ላይ ይህ ቁጥር 1,837 አሻቅቦ ነበር፡፡ እሳቸው ደግሞ የሚከተሏቸው 99  መዝገቦች ሲኖሩ፣ እስከ ማክሰኞ ምሽት ድረስ 672 የትዊተር መልዕክቶችን በገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
የምኒስትሯ የትዊተር መዝገብ መጠለፍን በመጠራጠር የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በዚያው  የማህበራዊ ድረገጽ መዝገባቸው ላይ ጉዳዩ  በተመለከተ ማረጋገጫ እንዲሰጣቸው በሚከተለው መልኩ ጥያቄዎችን  አቅርበው ነበር። 

ማርቆስለማ እንዲህ ሲሉ ጥያቄ አቅርበው ነበር "የተጠለፈው የትኛው ነው? ይሄኛው ወይስ የበፊቱ?
MarkosLemma@eweket ·
@ZenebuTadesse which one is hacked? this one or the previous one?

ሊሳሹማን በበኩሏ ስጋቷን በሚከተለው መልኩ ገልጻለች "የተከበሩ ምኒስትር ድምጽዎ ታፍኖ (በመንግስት ሃይሎች) ከሆነ ለእርሶ እውነተኛ ሃዘን እና ስጋት አለኝ"
Lisa Shoman@lmshoman
@ZenebuTadesse – Madam Minister, if you were silenced, you have my sincere condolences and concern.
ማህሌት የተባሉ ሌላ የማህበራዊ ገጽ አባል ደግሞ  የምኒስትሯን ድረ ገጽ መጠለፍ ተከትሎ የወጣውን መልእክት በጥርጣሬ እንዲህ ሲሉ ይጠይቃሉ
እሺ ታዲያ እርሶን ማን እንበል? ለምንድነው  በስማ በለው (በሶስተኛ ሰው) መልእክትዎን የሚገልጹት?
Mahlet@Mahlet_S
@ZenebuTadesse So who are you? Why tweet in the third person form ?
ምኒስትሯ ለእነዚህ ጥያቄዎች እና ስጋቶች ምንም ምላሽ ያልሰጡ ሲሆን የትዊተር መዝገባቸው ከሰዓታት በኋላ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ አምስት ሰዓት  ላይ አገልግሎቱን እንዲያቋርጥ ተደርጓል።ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ደግሞ የምኒስትሯ የትዊተር ገጽ ሙሉ በሙሉ የተሰረዘ ሲሆን ምንም ዓይነት ግንኙነት ማድረግ
እንደማይቻል የዚህ ጽሁፍ አቀናባሪ ለመረዳት ችሏል።
እንደሚታወቀው ፊንፊሸር የተባለውን የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን እና ደጋፊዎቻቸውን በበበይነ መረብ (ኢንተርኔት) ለመሰለል በምሊዮን የሚቆጠር መዋእለ ንዋይ እና የሰው ሃይል ያፈሰሰ መንግስት እንዴት በስሩ የሚመራቸውን የመንግስት ሃላፊዎች ከምፒውተር ሊከላከል አለመቻሉ በራሱ የወይዘሮ ዘነቡ የትዊተር መዝገብ ወይም ገጽ ተጠልፎ ነበር የሚለው የመንግስት ማስተባበያ ብዙም የሚያወላዳ አይሆንም። ይህ ጽሁፍ የተሰባሰበው በቀዳሚነት ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ድረገጽ ሲሆን የወሰኑት ደግሞ ከሌሎች ድረገጾች የተጨመሩ እና አንዳንድ የቃላት እና የዓረፍተነገር ማሻሻያዎች ተደርገውበታል።
ድራማው እንደቀጠለ ነው። በሚልዮን የሚቀጠረው ኢትዮጵያዊው ተራው ህዝብ ምን እንደፈጠረ የሚያውቀው ነገር የሌለ ሲሆን ይህ ውዝግብ ያመጣውን ያልታሰበ አሉታዊ የህዝብ ትኩረት ወይም ተቃውሞ የህውሃት መንግስት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚቆጣጠራቸው የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ልክ ይህ ተፈጠረ የተባለው ውዝግብ ከፍተኛ ተቃውሞ በህዝቡ ዘንድ እንዳስነሳ በማስመሰል የተለያየ ጥረቶችን ከማድረግ ባሻገር የትዊተር ገጻቸው ተጠለፈ የተባሉትን ምኒስትር ቃለመጠይቅ በማድረግ ጉዳዩ እንዲራገብ እና ለህብረተሰቡ በአሁኗ ሰዓት እጅግ አንገብጋቢ የሆኑ ሮሮዎች እና ችግሮች  አቅጣጫቸውን በማስቀየስ ሌላ በቀላሉ የሚጠቃ ወይም የሚወቀስ ቡድን ላይ በማነጣጠር ላይ ይገኛሉ። የሆኖ ሆኖ ምኒስትሯ የተባሉትን መልእክቶች በማህበራዊ ድረገጻቸው ላይ እንዳላተሙ ለመንግስት ከፍተኛ ቀረቤታ ላለው ዋልታ በሚከተለው መልኩ ቃላቸውን ሰጥተዋል።    

No comments:

Post a Comment