Friday, February 21, 2014

የግንቦት 7 ከፍተኛ ባለስልጣን የኢትዮጵያ መንግሥት ኮምፕውተሬን ይሰልላል ሲሉ ከሰሱ መንግሥት ውንጀላውን አስተባበለ

የኢንተርኔት ሰበራ፣ ዘረፋ፣ ስለላ፣ ሌብነት፣ ጥፋት
የኢትዮጵያ መንግሥት የተራቀቁ የስለላ ሶፍትዌሮችን እየለቀቀባቸው የኮምፕዩተሮቻቸውን ይዘት እንደሚሠርቅ እና የግል ግንኙነቶቻቸውንም እንደሚከታተል በውጭ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስሞታዎችን እያሰሙ መሆናቸው እየተነገረ ነው፡፡
አንድ የዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ነዋሪ በዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ፍርድ ቤት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ክሥ መመሥረታቸው፤ ሌላ አንድ ሰው ደግሞ ለእንግሊዝ ፖሊስ አቤቱታ ማስገባታቸው ታውቋል፡፡
ከትናንት በስተያ ማክሰኞ ዋሽንግተን ዲ.. ውስጥ በሚገኝ አንድ ፌደራል ችሎት የተከፈተ ዶሴ ከዚህ የስለላ አድራጎት ጀርባ ያለችው ኢትዮጵያ እንደሆነች ጠቁሞ ከሣሹ የአሥር ሺህ ዶላር የጉዳት ካሣ እንዲከፈለው ጠይቋል፡፡
እንግሊዝ ዋና ከተማ ለንደን ላይ በቀረበ ሌላ ክሥ እዚያ በስደት የሚኖሩትና የግንቦት ሰባት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል መሆናቸውን የተናገሩት ታደሰ ኬርስሞ ሰኞ ዕለት ባስገቡት ማመልከቻ ፊንፊሸር የሚባለውን ሶፍትዌር የሚቀምረው ዋና ተቀማጭነቱ እንግሊዝ ውስጥ የሆነ ጋማ ግሩፕ እንዲመረመርላቸው ጠይቀዋል፡፡
ኢትዮጵያን ከእንዲህ ዓይነቱ የኢንተርኔት ስለላ ጋር የሚያያይዙ ማስረጃዎች የተሰባሰቡትና የተደራጁት ካናዳ ውስጥ በሚገኝ ሲቲዘን ላብ በሚባል ድርጅት ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ “የኢትዮጵያ መንግሥት የኮምፕዩተር ጠለፋ ወይም የስለላ ተግባር አያካሂድም” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስ
ቃል አቀባይ አምባሣደር ዲና ሙፍቲ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡
ተጨማሪና ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ 

No comments:

Post a Comment