Thursday, March 29, 2012

ኖርዌይ, አሸብርአለዚያውጣ


Oslo District Court decided Muslim extremist Mullah Krekar should be remanded in custody for eight weeks

Ethiopian asylum seeker children to leave, Norway increases aid 

Oslo citizens welcome high immigrant numbers 

ልብ በሉ እነዚህ ሶስት የተቃርኖ  ይዘት ያላቸው የዜና እርዕሶች የታተሙት በዚህ ወር ማለትም በፈረንጆቹ ማርች በአንድ የኦን ላይን ጋዜጣ ላይ ነው። የመጀመሪያው የሚለው 
አሸባሪው ኢራቃዊ በኦስሎ ከተማ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ 
ሙላህ ክርካር የተባለው እስላማዊ አክራሪ የኦስሎ ክፍለከተማ ፍርድቤት ለስምንት ሳምንታት በቁጥጥር  ስር እንዲቆይ ውሳኔ አስተላለፈ። ሁለተኛው ርዕስ ደግሞ የሚለው  ኖርዌይ ኢትዮጵያውያዊ የሆኑ ከ450 በላይ የሚሆኑ የጥገኝነት ጠያቂ ሰዎች ህጻናት ከአገሯ  እንዲወጡ  በመስማማት ለኢትዮጵያ መንግስት የምትሰጠውን እርዳታ ጨመረች። ሶስተኛው ደግሞ የሚለው የኦስሎ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ሃገራቸው በከፍተኛ መንገድ እየጨመረ የመጣው የውጭ ሃገር ዜጎች ፍልሰት በጸጋ በመቀበል ላይ ናቸው። ከመጀመሪያው  ዜና ብንነሳ የ 55ዓመቱ የኢራቅ ኩርድ ብሄር ተወላጅ እና በሙሉ ስሙ የሚታወቀው ናጅሙዲን ፋራጅ አህመድ በ1991 ዓ᎐ም᎐ የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲሰጠው ያቀረበው ጥያቄ በኖርዌይ መንግስት ተቀባይነት አግኝቶ የመኖሪያና የኖርዊጅያን ዜግነት ቢሰጠውም ያጎረሰውን እጅ በመንከስ  አገሪቱን በሽብር ለማጥቃት በተለያዩ መንገዶች በመንቀሳቀስ ላይ ቢገኝም የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና የስደተኞች መስሪያ ቤቶች ባለስልጣናት እንደ አራስ ህጻን እሹሩሩ ከማለት አልፈው ይህ ግለሰብ እና ቤተሰቦቹ በህይወታቸው ላይ ጉዳት እንዳይደርስባቸው በከፍተኛ ወጪ ጥበቃ እያደሩጉላቸው ይገኛል።



ለአብነትም የኖርዌይ ወግ አጥባቂ ፓርቲ  መሪ በሆኑት ኤርና ሶልባሪ ላይ የመግደል ዛቻ2010 ዓ᎐ም᎐ ከማድረግ ባሻገር በሃገሪቱ በሚገኙ የቁርዓን መጽሃፍ ያቃጠሉ የኩርድ ብሄር ተወላጆችም ላይ ፋትዋ (በተገኙበት እንዲገደሉ የሚጠይቅ ትዕዛዝ/አዋጅ) ከማስተላለፉም በተጨማሪ አንሳር አል ኢስላም የተባለውን ታጣቂ የሽብርተኞች ቡድን በማቋቋም እና በመሪነት በማገልገሉ ምክንያት የኖርዊጅያን ዜግነቱን ተነጥቆ ወደ ሃገሩ እንዲመለስ ውሳኔ ቢሰጠም፦ለህይወቱ ዋስትና የኢራቅ መንግስት ልሰጥ አልችልም በማለቱ እስካሁን ድረስ ለጋሱ፣ታጋሹ፣ይቅር ባዩ፣ እና አዛኙ የኖርዌይ መንግስት አንቀባሮ እያኖረው ይገኛል። ይህ ግለሰብ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአሸባሪነት ከተመዘገቡ ሰዎች አንዱ ነው። እንዴት ነው እኔ ብቻ ነኝ እናተም ግራ ተጋብታቹሃል፣ አንድ የውጭ ሃገር ዜጋ ለሚኖርበት ሃገር ደህንነት እጅግ አስጊ መሆኑ እየታወቀ በሰብዓዊነት ስም የዛችን አገር ነዋሪዎችና የሌሎች አገር ዜጎችን እንዲያሸብር መፍቀድ ምንኛ ነው? 
ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በ ኦስሎ  ቤተክርስቲያን   
መልሱን ለእናንተ በመተው ወደ ሁለተኛው ዜና ስንሸጋገር በዛች አገር ከኢትዮጵያውን የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች በተወለዱ ከ450 በላይ ንጹሃን ህጻናት ህይወት ላይ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ እና የስደተኞች መ/ቤቶች ሃላፊዎች የዓለምዓቀፍ የሰብዓዊመብት እና የስደተኞች ድንጋጌዎችን በሚጻረር መልኩ ስለተወሰነው ኢሰብዓዊ፣ኢሞራላዊ፣ፍርደገምድል ውሳኔ የሚያትት ነው። ለማንም በግልጽ እንደሚታወቀው እነዚህ ከኖርዌይ ሌላ አገር የሌላቸው ከ450 በላይ የሚሆኑ ህጻናትም ሆኑ ከ2 እስከ 26ዓመት በዚያች አገር ጠንክረው በመስራት እና የሚጠበቅባቸውን ግብር እየከፈሉ የሚገኙት ወላጆቻቸው ለዛች አገር በየትኛውም መልኩ የደህንነትም ሆነ የኤኮኖሚ አደጋ እንደማያስከትሉ በትክክል ቢታወቅም በአገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ጸረ ስደተኛ እንቅስቃሴ ለማብረድ በማሰብ የአገሪቱ መንግስት ከመለስ ዜናዊ አምባገነን መንግስት ጋር ስምምነቱን በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ጨርሶ ኢትዮጵያውያኑን እንደማስታገሻ በመጠቀም ወደ ሃገራቸው በውድም ሆነ በግድ ለመመለስ እንቅልፍ አልባ ለሊት በማሳለፍ ላይ ይገኛል። እስቲ አስቡት ለመሆኑ በየትኛውስ መመዘኛ ቢሆን አንድን ለአገር ደህንነት በከፍተኛ ሁኔታ አስጊ የሆነ ሰውን እንዲኖር የወሰነ መንግስት በጎን ዞር ብሎ ከ450 በላይ የሚሆኑ ንጹሃን ሰዎችን ለአደጋ ማጋለጥ፡ ንቀትን፡ማን አለብኝነትና የእጅ አዙር ዘረኝነተን ያሳያል።
አጃኢብ አሉ ኖዊጅያንስ (ጥቅሷ የራሴ ነች) እስቲ ወደ ሶስትኛውና ወደ መጨረሻው ዜና ልውሰዳችሁ፡ እንደዚህ ዘገባ አገላለጽ ከሆነ እ᎐አ᎐አ᎐ በ2040 ዓ᎐ም᎐ በኖርዌይ ከሚኖረው ህዝብ 50 ከመቶው መጤ እንደሚሆን የሚገልጸውን ጥናት የዋናዋ ከተማ ኦስሎ አብዛኛው ነዋሪ በጸጋ እንደሚቀበለው ያትታል። በርግጥ ነዋሪዎቹ ይሄን ካሉ በሃገሪቱ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ለምን ኢትዮጵያውን ጥገኝነት ጠያቂዎችን በጉልበት በማባረር እነዚህን እንግዳ ተቀባይ ዜጎቹን ማስከፋት አስፈለገው?   እስካሁንም ወደፊትም ሊመለስ የማይችል ጥያቄ ይመስለኛል፤ በፖለቲካ ትክክለኛነት ስም ጉልበት እና ብዙ ደጋፊ ያለውን አሸባሪ እያባበሉ በማኖር ሌሎች ሰላማዊ እና ጠንካራ ሰራተኛ የሆኑ ግን ከኋላቸው አይዟችሁ ባይ የሌላቸውን ስደተኞች ማሰቃየት እና ቤት ንብረት ቤተሰብ ከመሰረቱበት አገር በሃይል ማስወጣት ከጊዚያዊ የፖለቲካ ጨዋታን ከማስጠበቅ ውጭ አንድ ቀን በታሪክ ፊት እንደሚያስጠይቅ የኖርዌይ ፖለቲከኞች ሊያስቡበት የሚገባ ጉዳይ ነው።    

ኖርዌይ, አሸብርአለዚያውጣ  ስኬዳል???         

No comments:

Post a Comment