Sunday, July 13, 2014

የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ሶስቱ ጋዜጠኞች በሌሉበት መዝገባቸው ተዘጋ

ሁለት ወር ከሃይ ቀናት በእስር ያሳለፉት ስድስቱ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች በሶስት የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ፡በሰንበት ሲመላለሱ ከርመው ትናንት ቅዳሜ በሌሉበት መዝገቡ ለዓቃቤ ህግ መተላለፉን በቦታው ተገኝታ የነበረችው ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ዘገበች። ሃምሌ ዓምስት ተቀጥረው የነበሩት ጋዜጠኞች ተስፋለም፡ወልደየስ፡ አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፡ኤዶም፡ካሳዬ እና የህግ መምህር እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ዘልዓለም ክብረት፡ እንዲሁም የዞን ዘጠኝ ጦማርያን ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃነ፡በአጠቃላይ ስድስቱ ተጠርጣሪዎች ፍርድቤት ይቀርባሉ ተብሎ እስከ ጠዋቱ አምስት ሰዓት ተኩል ድረስ ሲጠብቅ የነበረው ችሎት ተከታታይ በመጨረሻም ችሎቱ ማብቃቱ ተነግሮታል። ቆይታው ግራ ያጋባቸው፡ጠበቃው አቶ አመሃ መኮንን ሁኔታውን ለማጣራት ችሎት፡ገብተው ሲጠይቁ፡ "ውይ አለቀኮ"፡ የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። "እዚህ ውጭ ቁጭ ብለን እየጠበቅን እንዴት ነው አለቀ የሚባለው"፡ ብለው ላነሱት ጥያቄም "ስንጠራችሁ፡ አልሰማችሁም፡ የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል"። "ግቢ፡ውስጥ ከሶስት መቶ ሰው በላይ ተቀምጦ የእነርሱን ጉዳይ እየጠበቀ፡ጠበቃቸው እዚህ እያለ እንዴት፡አልሰማችሁም ይባላል" ብለው ቢጠይቁም ጠበቃ አይስፈልጋችውም ነበር። የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። "ተጠርጣሪዎቹስ መች ቀረቡ?" ብለው ሲጠይቁም "እነርሱ አይስፈልጉም ነበር፡ ፖሊስ ይህን መዝገብ ዘግቼ፡ጉዳዩን ለዓቃቤ ህግ፡ አስተላልፊያለሁ አለ። በዛ መሰረት መዝገቡ ተዘጋ" በማለት ምላሽ ሰጡት። 
ምንጭ: ኢካድፍ
የጦማሪው ማስታወሻ ለ78 ቀናት እና ማእልታት ምንም ዓይነት ክስ ሳይመሰርትባቸው የጓንታናሞ ታናሽ በሆነው ማእከላዊ እስርቤት የሚንገላቱት የኢትዮጵያ ተስፋዎች፡ ህይወት ላይ የምትጫወቱ ዳኛ፡ፓሊስና አቃቤህግ ተብዬዎች፡ታሪክ ፍርዱን ይሰጣችኋልትናንትው የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ጉዳይ የፍርድቤት ውሎ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ የሚባለው የህግ ስርዓት፡ ለእነማን እና በእነማን ጠለላ ስር እንድሆነ ለ101ኛ ጊዜ ፍንትው ብሎ ያሳያል። እነ ጠቅላይ ምኒስትር  ደሳላኝ ሃይለማርያም  አለ የሚሉን ህግ ተርጓሚ እና አስፈጻሚ ሚና እንዲህ ተደበላልቆ ትርጉም ያጣበት ጊዜ ላይ መድረሳችን፡ የዚህ አገር እጣ ፈንታ ከድጡ ወደማጡ   እያዘገመ  መሆኑን :ጥሩ አመላካች ነው።

No comments:

Post a Comment