Thursday, May 8, 2014

ሁለት የዞን 9 ጦማርያን አባላት በማእከላዊ እስርቤት ፖሊሶች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ገለጹ


የዞን 9 ጦማርያንን የጊዜ ቀጠሮ ሊያይ በተሰየመው ችሎት ዛሬ ሌላ አሰቃቂ ዜና አብሮ ሰምቷል፡፡ ሁለቱ የዞን9 አባላት በፍቃዱ ሃይሉና አቤል ዋበላ በማእከላዊ እስርቤት ፖሊሶች መመታታቸውን እና ውስጥ እግራቸው ላይ ግርፋት እንደተፈጸመባቸው የገለጹ ሲሆን ፓሊስ ማስረጃ የላቸውም ሲል ተከራክሯል፡፡ ለክርክሩ ምላሽም ውስጥ እግራቸውን ለፍርድ ቤቱ ማሳየት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቶርቸር ህግ መንግስታዊ አይደለም ሲል "አስተያየቱን" ሰጥቷል፡፡ እንደትላንትናው ሁሉ በተመሳሳይ ምክንያቶች የተነሳ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 10 ቀናትን ለምርመራ ፈቅዷል፡፡
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ለተከሳሾቹ ጭብጨባ እና ፉጨት ማሰማት የተከለከለ ሲሆን ተከሳሾች ሲወጡ ባሳዩት አጋርነትም ከዛሬ በኋላ ካጨበጨባችሁ እንዳትገቡ እናደርጋለን የሚል ማስፈራሪያም ተሰጥቷል፡፡ ወ/ ሮ ስንታየሁ የተባሉ የሬጅስትራር ሰራተኛ ጭብጨባውን እና ፉጨቱን ለዳኛ በመንገር (በተለመደ ቋንቋ በማቃጠር) አጋርነት እያሳዩ የነበሩትን ወጣቶች ተግባር ለማስቆም ሞክረዋል፡፡
በድጋሚ የዞን 9 አባላት  የወሰዷቸው ምንም አይነት የአሸባሪነት ስልጠና እንደሌለ እያረጋገጡ በህገ መነግስቱ አንቀጽ 18 መሰረት ማንኛውም ሰው ጭካኔ የተሞላበት ኢሰብአዊ  በሆነ መንገድ ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት የመጠበቅ መብት አለው ቢልም በታሰሩ አባላቶቻችን ላይ የደረሰውን ግርፋት አጥብቆ ያወግዛል፡፡
በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በመደወል እንዲሁም ኢሜሎችን በመላክ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄያችሁን በማቅረብ አጋርነታችሁን እንድታሳዩ እንጠይቃለን፡፡
ፍትህ ሚኒስትር አቶ ደሳለኝ ተረሳ 0115-51-50-99 /ext/286
0115-15 35 28
እምባ ጠባቂ አቶ ልዑል ስዩም / አቶ ገዛኅኝ ተስፋዬ , ህዝብ ግንኙነት 0111-58-06-52/ 0115-54-33-36
0115-53 20 73
የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አቶ አዲሱ ጴጥሮስ 0116293040,
0116293071
የፕሬዘዳንቱ ቢሮ አቶ ገብሩ አብረሃ / አቶ አድነው አበራ 0111-22-67-67 , 0111-24-46-14
0115-51-20-41
ፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት +251115512744
የኢትዩጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን 0 11-550-41-14 

No comments:

Post a Comment