ተፃፈ
ከስድስተኛ ተከሳሽ
በዘላለም
ክብረት
ወዳጄ
ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ?
እውን
እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ
ዘዴ አጥተን ወደ snail
mail እንመላለሳለን
ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ?
ለማንኛውም
እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣
ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡
‹‹
….ደብዳቤ
ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣
እንገናኝ
እና ልንገርሽ ሁሉንም….››
የደላው!
ቢያሻው
በደብዳቤ፣ ሲፈልግ በአካል እያማረጠ እኮ
ነው፡፡ ለእኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሁለቱም
ቅንጦት ነው (ወይ
ደብዳቤው አይደርስሽም ወይም አንቺን ማየቴ
ሊገደብ ይችላል)፡፡
ቆይ
ትንሽ የጎን ወሬ ላዋራሽና ምክንያቱን
እነግርሻለሁ፡፡ ‹‹አንቺ›› ተብለሽ በዚህ
ደብዳቤ ስለተጠቀስሽው ‹‹አንቺ››ና ይሄን
ደብዳቤ ለሚያነቡ ወዳጆች የዕምነት ክህደት
ቃሌን በትንሹ ላስፍር፡፡
እመቤት
ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ፍቅረኛ
(Ethiopian by choice) ዱቼ
ሞሶሎኒ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ፤ ወራሪው
ሃይል በመላው ኢትዮጵያ ‹‹ የኢትዮጵያን
ስም እያነሱ መፃፍ ክልክል ነው›› የሚል
ያልተፃፈ አዋጅ አውጆ እንደነበር ይነግሩናል፡፡
በዚህም ምክንያት ፀሀፍቱና አዝማሪያኑ ስውር
መጠሪያ መጠቀም ስላስፈለጋቸው እስከ ዛሬ
ድረስ ተወዳጁ ሕዝባዊ ዘፈን አንቺ ልጅ አንቺ
ልጅ እንደ ስውር የፍቅር ዘፈን ተበርክቷል፡፡
በዘፈኑ ‹‹አንቺ ልጅ ›› የተባለችውም
ኢትዮጵያ ናት፡፡ እኔስ በዚህ ዘመን ‹ይድረስ
ለባለ ታሪኩ›፣ ‹ይድረስ ለባለ ንብረቱ›…
እንደሱ የሀዘን ደብዳቤ ርእስ ‹ይድረስ
ለኢትዮጵያ › በማለት ፋንታ ‹ይድረስ ለአንቺ›
ለማለት ስውር መጠሪያ ተጠቅሜያለሁ?
፤
በፍፁም! ጌቶች
እንደሚሉት ሕገ መንግስቱ የመናገር ነፃነቴን
ሙሉ ለሙሉ አስከብሮልኛልናi
ቧልቱ
ይቆየንና በዚህ ደብዳቤ ርዕስ ዙሪያ ያለማንም
አስገዳጅነት የእምነት ክህደት ቃሌን ላስፍር
አንቺ የተባለችው ኢትዮጵያ አይደለችም፡፡
‹አንቺ› የኔዋ ሀቢቢ ግን ባለሽበት ይድረስሽ፡፡
ውዴ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ያለፈውን











