2011 ለነፃነት እኩልነት እና ፍትህ ታጋዮች የድል ለሰብአዊ መብት ረጋጮች እና ለአምባ ገነን መሪዎች ደግሞ የሽንፈት አመት በመሆኑ እጅግ ልንደሰትና የጀመርነውን ትግል በይበልጥ ማጠናከር ይገባል ;; የአምባ ገነኖች ጎራ ተራ በተራ እየተፈረካከሰ ግብአተ መሬቱ እየተፋጠነ ታሪክ ለመሆን የቀሩት ጥቂት ወራት ግፋ ቢል ዓመታት ናቸው :: እነሆ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የየመኑ አምባገነን ለ 33ዓመታት ጨምድዶ የያዘውን ስልጣን በቅርቡ እንደሚለቅ ማስታወቁን አልጀዚራ በሰበርዜናው ዘገቧል እንግዲህ ጥያቄው ማነህ ባለሳምንት ነው።ይህን ዜና ለየት የሚያደርገው ባሳለፍነው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ኖርዌይ የሚገኘው የዓለምአቀፉ የሰላም ድርጅት ማለትም ኖቤል የመኗዊቷን ጋዜጠኛና የሰብአዊመብት ተሟጋች ታዋኩል ካራመን እና ሴራሊዮውያኑን ማለትም ፕሬዚደንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ እንዲሁም የሴቶች መብት ተሟጓቿን ሊይማህ ግብዌን በጥምረት የ 2011 የዓለም ሰላም ተሸላሚዎች ለመድረግ መወሰኑን ተከትሎ የመጣ በመሆኑ ነው :: ይህ ክስተት የሚያረጋግጥልን እያንዳንዱ አምባገነን መሪ እንቅልፍአልባ ለሊት እንደሚያሳልፍ ነው የኛዎቹን ጨምሮ :: በኔ ግምት የየመኑ አምባገነን ለዚህ ውሳኔ የበቃው ስልጣን በቅቶት ሳይሆን የጓደኞቹ ማለትም የቤን አሊ :የጋዳፊ እና ሙባረክ እጣ ሳይደርሰው በፊት በአቁዋራጭ ለማምለጥ የተደረገ ሙከራ ይመስላል :: ያም ሆነ ይህ የየመን ህዝብ ላለፉት 6ወራት ያለማንም ደጋፊ እልህ አስጨራሹን ሰላማዊ ትግል ረሃብ ጥማትእንግልት እስራት ግድያ ሳያግደው የከፈለው የመስዋእትነት ውጤት ነው ይህ ድል የየመናውያን ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ህዝብም ጭምር ሲሆን በመላው ዓለም የአምባ ገነኖች ጭቆና ላንዴና ለመጨረሻ ለማስወገድ በመታገል እና በመሰዋት ላይ ላሉ ህዝቦች ትግላቸውን እግቡ እንዲያደርሱ የሚጋብዘና የሚያበረታታ ነው:: የዓለምአቀፉ የሰላም ድርጅት የዚህ ትግል አጋር በመሆኑ ሊመሰገን ይገባዋል :: የዘንድሮውን ሽልማት ለየት የሚያደርገው ተሸላሚዎቹ በሙሉ ሴቶች በመሆናቸው እና በድርጅቱ የ 101ዓመት ታሪክ መጀመሪያዋን አረባዊት በመሸለሙ ነው ::
አምባገነኑ የመለስ ዜናዊ መንግስት እነእስክንድርን:ረዕዮትን:ውብሽትን: ደበበን: አንዱአለምን: ደቲ ዳባን እና ሌሎች በሽህ የሚቆጠሩ ንጹሀን ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም 2 ስዊድናውያን ጋዜጠኞችን ሳይቀር በቃሊቲ እና በሌሎች እስር ቤቶች አጉሮ በማን አለብኝነት በማስቃየት እና በማጉላላት ላይ እንደሚገኝ የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ እያለ የኖርዌይ መንግስት ባደረገለት ጥሪ ትናንትና ባደረገለት ግብዣ ይህ አምባገነን ኦስሎ ተገኝቶ ሀይልን በተመለከተ ዐለማቀፍ ስብሰባ ላይ ንግግር ማድረጉና ኢትዮጵያውያኑም ድርጊቱን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በኦስሎ ከተማ ማድረጋቸው ይታወቃል:: ይህ በጣም የሚያሳዝንና የሚያስገርም ክስተት የአለማቀፉ የኖቤል የሰላም ድርጅትን አስደሳች ዜና ተከትሎ በቀናት ልዩነት መካሄዱ የኖርዌይ መንግስት ስለ ሰብዐዊ መብት መከበር ያለውን አመለካከት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው:: እንዲህ አይነቱ ተግባር መለስና ግብረአበር አምባገነኖችን የሚያበረታታና ድርጊታቸውን በይበልጥ እንዲገፉበት አይዟችሁ ከማለት አይተናነስም:: ምዕራባውያን መንግስታት ስለ ሰብዕዊ መብት መከበር ስለ ህግ የበላይነት ስለየመናገር እና መጻፍ ነጻነት ስለ መድበለፓርቲ የፈለገውን ቢለፍፉም በተግባር ግን እነ መለስን ከመሳሰሉ አምባገነን መሪዎች ጋር አብሮ በመስራት እነዚህን መሰረታዊ የሆኑ የማንኛውም የሰው ልጆች መብቶች እንደፈለጋቸው እንዲረግጡና እኛንም ለበለጠ ጭቆና:እስራት:እንግልት:እስር:ስደት:ረሀብ ወዘተ ለዘመናት እንድንማቅቅ ተፈርዶብናል:: የመለስ በዚህ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፍ መጋበዝ የዚህ አንዱ አካል ሲሆን በአሁን ሰዐት በአገሪቱ በተለያዩ የአገራችን ቦታዎች እየታሰሩ: እየታፈኑ:እየተራቡ እና እየተገደሉ ባሉ ወገኖቻችን ላይ እንደመሳለቅ ይቆጠራል:: ምዕራባውያን በሁለት ቢላ መብላታቸውን ካላቆሙ የነመለስን የስልጣን ዘመን በማራዘምና እኛ የምናደርገውን በነጻነት በእኩልነት እና በመከባበር ለመኖር የምናደርገውን ጥረት በማሰናከል አንድ ቀን በታሪክ እንደሚጠየቁ ሊገነዘቡ ይገባል:: በሊቢያ:በቱኒዚያ:በግብጽ እና በሌሎች በአምባገነን በሚመሩ አገሮች ከሰሩት ስህተት ለመማር አሁንም ጊዜው አልረፈደም::

sra fet bozzzne.yuo not werk.Nerway, Danemark all europ Amerka know Males is goodest in Afreka.all yuo adgitat amharo tolk, tolk. we not afred nobady.
ReplyDelete