እንኳን ወደ ስደተኞች ዓለም መጡ። ስደተኛነት ምርጫ አይደለም። Welcome to the world of REFUGEES! NOBODY chooses to be a REFUGEE!!!
Showing posts with label Atnaf Berahane. Show all posts
Showing posts with label Atnaf Berahane. Show all posts
Saturday, September 20, 2014
Confessions of the Ex-‘Revo’: Befekadu Hailu
የቀድሞው “የአብዮት አድናቂ” ኑዛዜ በፍቃዱ ዘ ኃይሉ
ወይ ጥንካሬ፡ ወይ ብስለት፡ ወይ የዓላማ ጽናት እንጂ ሌላ ምንም ሊባል አይችልም፡ይህንን የበፍቄን በሳል እና ትንተና የተሞላበት ደብዳቤ ለሚያነብ ሰው፡ በርግጥ፡ አንድ፡ ባልሰራው ወንጀል ቁምስቅሉን ከሚያይ እስረኛ የተጻፈ ነው ብሎ ለማመን እጅግ ይከብዳል። ዛሬም ይጽፋሉ፡ ይተቻሉ ያላንዳች ፍራቻ፡ ምንም እንኳን እንዲህ ዓይነቱ አልበገር ባይነት ተመርኩዞ በቀለኛውና ጨካኙ መንግስት የነገው ህይወታቸውን እንደሚያጨልመው እና በነዛ ቀጫጭን እጆቻቸው ላይ ያጠለቀውን ካቴና የበለጠ እንደሚያጠብቀው ቢረዱም። የታሰርነው፡ እኛ እንጂ እነሱማ ነጻ ናቸው።
ርዕሱን
አላስታውሰውም ‘ንጂ እ.ኤ.አ
በ2011 Arab Uprising በመባል
የሚታወሰውን አብዮትተከትሎ፣ ኢትዮጵያውያን
ፌስቡከኞችም (በተለይ
ዲያስፖራ የሚገኙ)
ግንቦት 20
ላይ (ልክ
በኢሕአዴግ የ20ኛ
አገዛዝ ዕድሜ)
“Anger day” በሚል
በፌስቡክ አብዮትመጥራታቸውን ተቃውሜ አንዲት
ጽሑፍ ጽፌ ነበር፡፡ በዓመቱ ደግሞ ‹‹
አብዮት ወረት ነው›› በሚል ርዕስ በፌስቡክ
አብዮት ለማስነሳት ፍላጎት ያላቸው በርካቶች
እንዳሉ ገልጬ ነገር ግን ይጎድላቸዋል
የሚባሉትንነገሮች ዘርዝሬ ጽፌ ነበር፡፡
በነዚህ ሁለት ጽሑፎች ላይ፣ ላዩን አብዮትን
የተቃወምኩ ቢመስልም እውነታው ግን ጽሑፎቹ
በተጻፉበትወቅት ሕዝቡም፣ ተቃዋሚ ልሂቃኑም፣
ሁኔታዎቹም ለአብዮት ዝግጁ አይደሉም የሚል
ዝንባሌ ማሳየቱ ነበር፡፡
ከሌላ
ዓመት በኋላደግሞ ‹‹ስለለውጥ›› በሚል
ርዕስ ተከታታይ ጽሑፎችን በ‹‹ዞን 9››
ላይ በግል
ተነሳሽነት ማስፈር ጀምሬ ነበር፡፡ ጽሑፉን
የጀመርኩት ‹‹ኢሕአዴግ ሥልጣኑን
በምርጫ ይለቃል?››
በሚል ጥያቄ
ነበር፡፡ ‹‹አይለቅም›› የምልባቸውን
ምክንያቶች ካስቀመጥኩ በኋላ የለውጥ አማራጭ
የምላቸውን (አብዮት፣ሰላማዊ
አለመታዘዝ /civil
disobedience/ የመሳሰሉትን)
በየዘርፉ
እየቀነጫጨብኩ ለማሳየት ነበር ዓላማዬ ከዚያም
‹‹የለውጥ ፍርሃት››፣ ‹‹የሥርዓት ለውጥ
እና ሃይማኖት››፣ ‹‹የ1966ቱ
የኢትዮጵያ አብዮት እና የማኅበራት ሚና››
የሚሉ ርዕሶችን በማንሳት በሐሳቦቹ ላይ
በሐቀኝነት ለመከራከር ጥረት አድርጌያለሁ
(ከዚህ
በላይ አልገፋሁበትም እንጂ)፡፡
በበኩሌ ስለአብዮት በደንብ ያነበብኩትም፣
ያሰብኩትም፣ የጻፍኩትም፣ የተረዳሁትም ያኔ
ነበር፡፡ ያኔ በአብዮት ላይ የነበረኝ እምነት
ተሸርሽሮ ግማሽ ደርሶ ነበር፡፡ ተንጠፍጥፎ
ያለቀው ግን
Saturday, August 30, 2014
ክሶቼ የቅጣት ጣሪያቸው እስከ ሞት ድረስ ነው። በእስር ላይ የሚገኘው የህግ መምህሩ እና ጦማሪው ዘላለም ክብረት
ብርቅዬው የኢትዮጵያ ልጅ ዘላለም ክብረት እግር ተወርች እየማቀቀ ከሚገኝበት እስርቤት ስለእስሩ፡ስለአሳሪዎቹ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የህግ አስፈጻሚዎች፡ ተርጓሚዎች (ለመሆኑ ግን ህግ የሚባለው ነገርስ አለ) እና ሌሎች ባለጊዜዎች የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው የሚባለውን ህገመንግስት በመጣስ በእሱ እና በሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ወገኖች ላይ የሚፈጽሙትን ለህሊና የሚዘገንን ድርጊት ለሁለተኛ ጊዜ በከተበው ሃያል ብእሩ እነሆ ብሎናል። ከዘላለም ደብዳቤ ምን ያህል የመንፈስ ጥንካሬ እና ለሰው ልጆች መብት መከበር ያለውን ተጋድሎ እና እስርቤት እንኳን ሆኖ ገዢዎቻችን የጤፍ ቅንጣት ያህል እንደማይፈራቸው ለመገንዘብ ይቻላል። ሌላው በጣም ዘላለምን ልዩ የሚያደርገው እንደዚያ ባለ አሰቸጋሪ ሁኔታ ላይ ሆኖ የደረሱበትንና እየደረሱበት ያሉትን ኢሰብዓዊ በደሎች እያዋዛ በመጻፍ ለተደራሲ ማቅረብ መቻሉ ነው። የዘላለም የህግ እና የሰብዓዊ መብቶች እውቀት በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በዜጎቹ ላይ እየፈጸመ ያለውን ቅጥ ያጣ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ርቃኑን አውጥቶታል። በዚህም የተነሳ ይህ በቀለኛ መንግስት ዘላለምን ለወራት እንዲያም ሲል ለዓመታት እንደ እነ እስክንድር ነጋ፡ ርዕዮት ዓለሙ፡ በቀለ ገርባ እና ሌሎችም እንዲማቅቅ እንደሚፈርድበት ሳይታለም የተፈታ ነው።
Friday, August 22, 2014
መንግስቴ የ 15 እና የ14 ዓመት ልጆችን በአሸባሪነት ጠርጥሮ እንደሚያስርም ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ዘላለም ክብረት
ተፃፈ
ከስድስተኛ ተከሳሽ
በዘላለም
ክብረት
ወዳጄ
ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ?
እውን
እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ
ዘዴ አጥተን ወደ snail
mail እንመላለሳለን
ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ?
ለማንኛውም
እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣
ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡
‹‹
….ደብዳቤ
ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣
እንገናኝ
እና ልንገርሽ ሁሉንም….››
የደላው!
ቢያሻው
በደብዳቤ፣ ሲፈልግ በአካል እያማረጠ እኮ
ነው፡፡ ለእኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሁለቱም
ቅንጦት ነው (ወይ
ደብዳቤው አይደርስሽም ወይም አንቺን ማየቴ
ሊገደብ ይችላል)፡፡
ቆይ
ትንሽ የጎን ወሬ ላዋራሽና ምክንያቱን
እነግርሻለሁ፡፡ ‹‹አንቺ›› ተብለሽ በዚህ
ደብዳቤ ስለተጠቀስሽው ‹‹አንቺ››ና ይሄን
ደብዳቤ ለሚያነቡ ወዳጆች የዕምነት ክህደት
ቃሌን በትንሹ ላስፍር፡፡
እመቤት
ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ፍቅረኛ
(Ethiopian by choice) ዱቼ
ሞሶሎኒ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ፤ ወራሪው
ሃይል በመላው ኢትዮጵያ ‹‹ የኢትዮጵያን
ስም እያነሱ መፃፍ ክልክል ነው›› የሚል
ያልተፃፈ አዋጅ አውጆ እንደነበር ይነግሩናል፡፡
በዚህም ምክንያት ፀሀፍቱና አዝማሪያኑ ስውር
መጠሪያ መጠቀም ስላስፈለጋቸው እስከ ዛሬ
ድረስ ተወዳጁ ሕዝባዊ ዘፈን አንቺ ልጅ አንቺ
ልጅ እንደ ስውር የፍቅር ዘፈን ተበርክቷል፡፡
በዘፈኑ ‹‹አንቺ ልጅ ›› የተባለችውም
ኢትዮጵያ ናት፡፡ እኔስ በዚህ ዘመን ‹ይድረስ
ለባለ ታሪኩ›፣ ‹ይድረስ ለባለ ንብረቱ›…
እንደሱ የሀዘን ደብዳቤ ርእስ ‹ይድረስ
ለኢትዮጵያ › በማለት ፋንታ ‹ይድረስ ለአንቺ›
ለማለት ስውር መጠሪያ ተጠቅሜያለሁ?
፤
በፍፁም! ጌቶች
እንደሚሉት ሕገ መንግስቱ የመናገር ነፃነቴን
ሙሉ ለሙሉ አስከብሮልኛልናi
ቧልቱ
ይቆየንና በዚህ ደብዳቤ ርዕስ ዙሪያ ያለማንም
አስገዳጅነት የእምነት ክህደት ቃሌን ላስፍር
አንቺ የተባለችው ኢትዮጵያ አይደለችም፡፡
‹አንቺ› የኔዋ ሀቢቢ ግን ባለሽበት ይድረስሽ፡፡
ውዴ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ያለፈውን
Thursday, August 21, 2014
Ethiopian Court Denies Bail to 3 Journalists & 6 #FreeZone9Bloggers: RSF
Reporters Sans Fronetiers (RSF), one of the International Freedom of Expression watchdogs disclosed this today following yesterday's orchestrated trial held in Ethiopia's capital Addis Ababa. Since the prosecutor couldn't corroborate the fabricated charges against these innocent citizens who did nothing but exercised birthrights, it repeats the two decades tradition by denying bail and adjourning the trial for the 8th times. Here's the details of RSF's reportage about the "hearing".
Three
journalists and six bloggers who have been held
for the past five months were denied bail by a federal court in
Addis Ababa yesterday after the prosecution argued that article 3 of
the 2009 anti-terrorism law, under which they are detained, precludes
release on bail.
The
defence said article 3’s bail prohibition does not apply because
none of them has been individually charged with a specific crime
under the anti-terrorism law. The defence also argued that article 3
violates the constitutional guarantee of the right to release on
bail.
The
three journalists are
Monday, August 11, 2014
"We gave our Confession after being Brutally Treated" Leaked Letter by jailed Zone9 Blogger
![]() |
| Befeqadu Hailu, Zone9 Blogger |
First of all I'd like to thank Mahilet Solomon, for her tremendous job in translating this leaked letter by one of the members of Zone 9 bloggers aka Befeqadu Hailu, just a day after it was published. It shows not only her translation skill but also her unparalleled devotion to the freedom of expression, and above all her care for thousands of fellow Ethiopians who are being incarcerated for the crimes they didn't commit. Befqadu also should be commended for penning this very troubling and obvious account under such brutal circumstances where he, other members of Zone 9 bloggers, journalists, opposition party leaders and their followers have to go through everyday and night in present day Ethiopia. What Befqadu wrote is not something new, however it helps to open our eyes about the alarming situation with regard to the human-rights abuses in Ethiopia especially against those under police custody. The Ethiopian government denied and is still denying all these allegations, even though firsthand experiences by the likes of Befqadu and research documents by other human-rights watchdogs reveal these broad-light gross abuses against innocent and unarmed Ethiopians who did nothing but exercised their constitutional and birthrights. I hope, one day all the culprits of these heinous crimes will be brought to justice and eventually innocent victims of this brutal system will be freed. Here's the full excerpt of the English version of Befqadu's leaked letter from one of Ethiopia's notorious prisons called Kilinto.
"Dear Hyena no need for excuses just eat me” - Ethiopian Proverb By BefeQadu Hailu
Translated by Mahilet Solomon
"So
what do you think is your crime?" I was asked by one of my
interrogators while I was telling him about what I did as a blogger, an
advocate and an activist. Later on, after I was allowed to meet with my
"collaborators" according to my prisoners and asked each other, we found
out we were all asked this same question “what do you think is your
crime”? This describes the overall outcome of our interrogation. Since
they couldn’t figure out what our supposed crime was or what law we were
suspected of violating, we were asked
Sunday, August 10, 2014
‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በጦማሪው በፍቃዱ ሃይሉ ተጽፎ ከቂሊንጦ እስርቤት ሾልኮ የወጣ ጽሁፍ
ይህ በቅርቡ በተለያዩ ድረገጾች እና የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ይፋ የሆነው የዞን ዘጠኝ ጦማር አባል የሆነው እና ከሌሎች አምስት ባልደረቦቹ እና ሶስት ጋዜጠኞች ጋር በህውሃት የጸጥታ ሰራተኞች ታግቶ ላለፉት ሶስት ወራት ያለምንም ክስ እና ወንጀል በቂሊንጦ ምርመራ ክፍል ላይ ባለሰራው ወንጀል ፍዳውን የሚያየው የጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ አጭር ጽሁፍ፡ አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ኢፍትሃዊ ስርዓት እና አምባገነንት በመጠኑም ቢሆን ያሳያል። እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ግን፡ ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ተመሳሳይ ወይም ከዚህ የከፋ ወንጀል እየተፈጸመባቸው ሲሆን እነዚህን በደሎች እንደበፍቃዱ ለህዝብ የሚያደርሱባቸው መንገዶችም ሆነ ችሎታውም እንደሌላችው መገንዘብ ይገባል። ህውሃት፡ ይህን መሰሉን ኢሰብዓዊ ድርጊት ሲፈጽም የመጀመሪያው አይደለም የመጨረሻውም አይሆንም። የበፈቃዱ ሃይሉ፡የአቤል ዋበላ ፡የአስማማው ሃይለጊዮርጊስ ፡የናትናኤል ፈለቀ፡የዘላለም ክብረት፡የኤዶም ካሳዬ፡የማህሌት ፋንታሁን፡የተስፋለም ወልደየስ፡የእስክንድር ነጋ ፡የርዕዮት ዓለሙ፡የውብሸት ታዬ፡የአንዷለም አራጌ፡ የበቀለ ገርባ እና የሌሎች በሺሆች የሚቆጠሩ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ወንጀል፡ ለአገራቸው መቆርቆራቸው እና በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ህጸጾች ለማጋለጥ መድፈራቸው ብቻ ነው።
‹‹ታዲያ
ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!››፣
ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና
እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም
ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው
ሳበቃ፡፡ በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ
ከ‹‹አባሪዎቼ››
ጋር
መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ
ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል፡፡
ይኼ ነው እንግዲህ የምርመራችንን ሒደት
የሚገልፀው ጥያቄ፡፡ ‹‹ተጠርጥረን››
የተያዝንበትን
ጉዳይ የሚያረጋግጥ ሥራ ሠርተን ባለመገኘታችን
Monday, July 14, 2014
ከ ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ጠበቃ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ
‹‹የአካል ነጻነታቸው እንዲከበርም ክስ እንመሰርታለን››
የአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለመጨረሻ ጊዜ ከሚል ማስጠንቀቂያ ጋር ለፖሊስ የሰጠው የ28 ቀን ቀጠሮ ቅዳሜ የሚያበቃበት በመሆኑ የዞን ዘጠኞችና የጋዜጠኞቹን ጉዳይ ሲከታተሉ የቆዩ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና ጋዜጠኞች ቀደም ብለው ፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ደርሰዋል፡፡ምን ይወሰን ይሆን? በሁሉም ልብ የሚመላለስ ጥያቄም ነበር፡፡ከዘጠኙ ታሳሪዎች መካከል ስምንቱን በፍርድ ቤት ሲወክሉ የቆዩት ጠበቃ አምሀም ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ቀደም ብለው ቅጥር ግቢው ተገኝተዋል፡፡
አራት ሰዓት እንደሚጀመር የተገመተው ችሉቱ እስከ አምስት ከሩብ ድረስ በሌሎች ጉዳዩች
ተወጥሮ ቆይቷል፡፡ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ነፍጥ ባነገቱ ወታደሮች ታጅበው መምጣት የነበረባቸው ኪቦርድ አንጋቾች
እስራት ያልበገረውን ተስፋቸውን እየዘሩ ሊመጡ አልቻሉም፡፡ሁኔታው አግራሞት የፈጠረባቸው የተወሰኑ ጋዜጠኞች ወደ
መዝገብ ቤት በማምራት መረጃ ጠየቁ፡፡የተሰማው በግቢው ውስጥ የነበሩትን ጠበቃ አምሀ መኮንንን ጨምሮ ያስገረመ፣ ያሳዘነና
ያሳፈረ ነበር፡፡ከጠበቃው ጋር ዳዊት ሰለሞን ያደረገው አጠር ያለ ቃለ ምልልስ እንደወረደ እነሆ፡፡
ጥያቄ---ወደ ፍርድ ቤቱ ሲመጡ በአእምሮዎ ያመላልሱት የነበረው ነገር ምንድን ነው?ጠበቃ አምሀ---ምናልባት ምርመራ ባለመጨረሳችን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠን ይላሉ እያልኩ ነበር፡፡ይህንን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ በምን አይነት መንገድ እንደሚመልስ ለማወቅም ፈልጌ ነበር፡፡የሆነው ግን በፍጹም ያልጠበቅነው ነገር ነው፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ያመሩ ጋዜጠኞች ‹‹የልጆቹ መርማሪ ነኝ ያለ ሰው ምርመራዬን በመጨረሴ ለአቃቤ ህግ አስተላልፊያለሁ›› በማለቱ መዝገቡ እንደተዘጋ እንደተነገራቸው እንደነገሩኝ እውነት መሆኑን አጣርቻለሁ፡፡
ጥያቄ --- ሁኔታውን እንደሰሙ ምን አደረጉ?
ጠበቃ አምሀ -- እኛ ከቀጠሮው ሰዓት ቀደም ብለን ግቢው ውስጥ ተገኝተን መርማሪው እንዲህ ዓይነት ነገር ሲያቀርብ መስማት ነበረብን፡፡ በፍጹም እንዲህ አይነት መደረግ እንደሌለበት ቅሬታ እንደተሰማንና የተፈጸመው ነገር ህገ ወጥ መሆኑን ለዳኛው ተናግረናል፡፡
ጥያቄ -- ህገ ወጥ የሆነው ምንድን ነው?
ጠበቃ አምሀ --ለፖሊስ ልጆቹን ለተጨማሪ 28 ቀናት እንዲያስር ፈቅዶለት የነበረው ፍርድ ቤቱ ነው፡፡እስካሁን ድረስ ደምበኞቼ የታሰሩት በፍርድ ቤት እውቅና ነው፡፡ከዛሬ አራት ሰዓት ጀምሮ ግን ደምበኞቼ የታሰሩት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመሆኑ እስራታቸው ህገ ወጥ ነው፡፡ፖሊስ ልጆቹን ፍርድ ቤት አቅርቦ ምርመራውን መጨረሱን ማስረዳትና ክስ የሚመሰርት ከሆነም ማሳወቅ ይገባው ነበር፡፡የሚመሰርተው ክስ ዋስትና የሚያስከለክልና የማያስከለክል መሆኑን መወሰን የነበረበት ፍርድ ቤቱ ነው፡፡ይህ ሳይደረግ መዝገቡ ተዘግቷል መባሉ ህገ ወጥ ነው፡፡
ጥያቄ -- ከአሁን በኋላ ለደምበኞችዎ ሊያደርጉ የሚችሉት ነገር ምንድን ነው?
ጠበቃ አምሀ -- ሰኞ ወይም ማክሰኞ የደምበኞቼ የአካል ነጻነት እንዲከበር ክስ እመሰርታለሁ፡፡ሰኞን የምንጠብቀው እንደተናገሩት ክስ የሚመሰርቱ ከሆነና የት እንደሚመሰርቱ ለማጣራት ነው፡፡
ጥያቄ --በ‹‹ሃብየስ ኮርፐስ›› ደምበኞችዎ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ክስ የምትመሰርቱት በየትኛው ፍርድ ቤት ነው?
ጠበቃ አምሀ --ክሱን የምንመሰርተው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው፡፡ጥያቄ --ደምበኞችዎን በማዕከላዊ በወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲጎበኙ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ነገር ግን እስካሁን ድረስ አቤል ዋበላን ሰዎች ማግኘት እንዳልቻሉ እየተናገሩ ነው ምክንያቱን ለማጣራት ሙከራ አድርጋችኋል?
Cases of Zone9 Bloggers & Journalists referred to the Court in the Absence of both the Defendants & their Lawyer
The first instance court of Arada bench was expected to wrap up the
pre-trial ‘hearing’ which took more than 70 days and yet the bloggers
were not even brought before the judge. Mr.Amaha Mekonnen,
a lawyer defending the bloggers & journalists who are detained on
unclear but shaping up to be on terrorism charges expected the first
instance court at Arada bench to rest the pre-trial procedure last
Saturday. The court had set the 12th July hearing for closing arguments
but with an extraordinary move the police referred the case to the
Federal High Court without even the presence of neither the defendants nor their
defense lawyer himself. The shift overlooked the court and contravenes even the
standard procedure of the biased justice system. The lawyer speaks to Dawit Solomon, a journalist based in Addis Ababa about the issue. Here
are the translated excerpts from the interview.
DAWIT: What were your thoughts on your way to the court for Saturday’s procedure?
| Amaha Mekonen Defense Lawyer of Zone 9 bloggers & Journalists |
AMAHA: I expected the police might demand for more
time to wrap up their interrogation as usual. I also sought to see how
the court would reply to this repeated claim of the police.
Nevertheless, to the shock of me and all people who were here what
unfolded was really baffling. Since the detainees were not brought to
the court some journalists went straight to the court’s registrar to ask
about the case. Then a person who claimed himself as “the detective” of
the case told the journalists since he is done with the interrogation
he submitted the case for a prosecutor. He further claimed that the case
is closed. This was what I was told by the journalists then I also went
in to verify which I found it true. They closed the case without the
presence of neither my clients nor me who is
representing them.
DAWIT: What action have you taken after you heard?
AMAHA: We have been to court’s compound way
earlier than the scheduled time of the hearing. When the detectives/police officers presented their arguments it should be in our presence. I
have tried to explain our disappointment to the judge. This is
basically a grave breach of law.
DAWIT: So what is the encroachment? Where is the breach of the law?
Sunday, July 13, 2014
የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ሶስቱ ጋዜጠኞች በሌሉበት መዝገባቸው ተዘጋ
ሁለት
ወር ከሃይ ቀናት በእስር ያሳለፉት ስድስቱ
ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች በሶስት የጊዜ
ቀጠሮ መዝገብ፡በሰንበት ሲመላለሱ ከርመው ትናንት ቅዳሜ በሌሉበት መዝገቡ ለዓቃቤ ህግ
መተላለፉን በቦታው ተገኝታ የነበረችው ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ዘገበች። ሃምሌ ዓምስት
ተቀጥረው የነበሩት ጋዜጠኞች ተስፋለም፡ወልደየስ፡
አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፡ኤዶም፡ካሳዬ እና
የህግ መምህር እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ዘልዓለም
ክብረት፡ እንዲሁም የዞን ዘጠኝ ጦማርያን
ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃነ፡በአጠቃላይ
ስድስቱ ተጠርጣሪዎች ፍርድቤት ይቀርባሉ
ተብሎ እስከ ጠዋቱ አምስት ሰዓት ተኩል ድረስ
ሲጠብቅ የነበረው ችሎት ተከታታይ በመጨረሻም
ችሎቱ ማብቃቱ ተነግሮታል። ቆይታው ግራ
ያጋባቸው፡ጠበቃው አቶ አመሃ መኮንን ሁኔታውን
ለማጣራት ችሎት፡ገብተው ሲጠይቁ፡ "ውይ አለቀኮ"፡
የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። "እዚህ ውጭ ቁጭ
ብለን እየጠበቅን እንዴት ነው አለቀ የሚባለው"፡
ብለው ላነሱት ጥያቄም "ስንጠራችሁ፡ አልሰማችሁም፡
የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል"። "ግቢ፡ውስጥ ከሶስት
መቶ ሰው በላይ ተቀምጦ የእነርሱን ጉዳይ
እየጠበቀ፡ጠበቃቸው እዚህ እያለ እንዴት፡አልሰማችሁም
ይባላል" ብለው ቢጠይቁም ጠበቃ አይስፈልጋችውም
ነበር። የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። "ተጠርጣሪዎቹስ
መች ቀረቡ?" ብለው ሲጠይቁም "እነርሱ አይስፈልጉም
ነበር፡ ፖሊስ ይህን መዝገብ ዘግቼ፡ጉዳዩን
ለዓቃቤ ህግ፡ አስተላልፊያለሁ አለ። በዛ
መሰረት መዝገቡ ተዘጋ" በማለት ምላሽ ሰጡት።
ምንጭ: ኢካድፍ
የጦማሪው ማስታወሻ ለ78 ቀናት እና ማእልታት ምንም ዓይነት ክስ ሳይመሰርትባቸው የጓንታናሞ ታናሽ በሆነው ማእከላዊ እስርቤት
የሚንገላቱት የኢትዮጵያ ተስፋዎች፡ ህይወት ላይ የምትጫወቱ ዳኛ፡ፓሊስና አቃቤህግ ተብዬዎች፡ታሪክ ፍርዱን ይሰጣችኋል። የትናንትናው የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ጉዳይ የፍርድቤት ውሎ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ የሚባለው የህግ ስርዓት፡ ለእነማን እና በእነማን
ጠለላ ስር እንድሆነ ለ101ኛ ጊዜ ፍንትው ብሎ ያሳያል። እነ ጠቅላይ ምኒስትር ደሳላኝ ሃይለማርያም አለ የሚሉን ህግ ተርጓሚ እና አስፈጻሚ ሚና እንዲህ ተደበላልቆ ትርጉም ያጣበት ጊዜ ላይ መድረሳችን፡ የዚህች አገር እጣ ፈንታ ከድጡ ወደማጡ እያዘገመ መሆኑን :ጥሩ አመላካች ነው።
Sunday, May 18, 2014
የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን እና የሶስቱ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች የቅዳሜና እሁድ ውሎ በህውሃት የካንጋሩ ፍርድቤት
ጋዜጠኛ
ጽዮን ግርማ በአራዳ
ምድብ ችሎት በአካል በመገኘት እንደዘገበችው እንደዘገበችው በዛሬው እለት የተከናወነው የፍርድ ቤት ድራማ ያው ህውሃት እንደለመደው በፍቃዱ ሃይሉ ማህሌት ፋንታሁን እና አቤል ዋበላ ላይ ፖሊስ ከትላንትናው ጋር ተመሳሳይ የሆነ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የጠየቀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ 14 ቀን ፈቅዶለታል፡፡ፖሊስ
የጸረ ሽብር አዋጁን በመጥቀስ በሽብር ክስ ለማቅረብ ስላሰበ 28 ቀን እንዲሰጠው የጠየቀ ቢሆንም ዳኛው ያለምንም
የተለየ ተጨማሪ ነገር ከመነሻ ጥርጣሬ ለመቀየር ፖሊስ አሳማኝ ምክንያት ባለማቅረቡ 14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ
ብቻ ፈቅደዋል። የዛሬውን ውሎ ለየት የሚያደርገው፡ ፖሊስ የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች እና ወዳጆችን እንዳያለቅሱ፡ለታሳሪዎቹ እጃቸውን
እንዳያውለበልቡ እና ምንም ዓይነት ምስል በፍርድቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳያነሱ/እንዳይቀርጹ መከልከሉ የአፈናውን
መጠነሰፊነት ያሳያል። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በትዊተር ላይ ዜጎች በሚከተለው መልኩ ቁጣቸው እና ሮሮአቸውን ሲገልጹ ነበር።
“እጅ ማውለብለብና ማልቀስ የተከለከለ ነው:: ይኽን የሚያደርግ ሰው ይዘን እንኼዳለን::” ፖሊስ
*መተንፈስ ክልክል ነው* pic.twitter.com/MooV7BOzIy
— Paliku Piluku (@PalikuPiluku) May 18, 2014
ህውሃት ኢትዮጵያውያንን መከልከል የቀረው መተንፈስ ብቻ ሳይሆን አይቀርም፡ ይሄንኑ በተመለከተ ደግሞ አንድ ፓሊኩ የተባሉ ግለሰብ በሚከተለው መልኩ ገልጸውታል
Thursday, May 8, 2014
ሁለት የዞን 9 ጦማርያን አባላት በማእከላዊ እስርቤት ፖሊሶች ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ገለጹ

የዞን 9 ጦማርያንን የጊዜ ቀጠሮ ሊያይ በተሰየመው ችሎት ዛሬ ሌላ አሰቃቂ ዜና አብሮ ሰምቷል፡፡ ሁለቱ የዞን9 አባላት በፍቃዱ ሃይሉና አቤል ዋበላ በማእከላዊ እስርቤት ፖሊሶች መመታታቸውን እና ውስጥ እግራቸው ላይ ግርፋት እንደተፈጸመባቸው የገለጹ ሲሆን ፓሊስ ማስረጃ የላቸውም ሲል ተከራክሯል፡፡ ለክርክሩ ምላሽም ውስጥ እግራቸውን ለፍርድ ቤቱ ማሳየት እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ፍርድ ቤቱ ቶርቸር ህግ መንግስታዊ አይደለም ሲል "አስተያየቱን" ሰጥቷል፡፡ እንደትላንትናው ሁሉ በተመሳሳይ ምክንያቶች የተነሳ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ 10 ቀናትን ለምርመራ ፈቅዷል፡፡
በዛሬው
የፍርድ ቤት ውሎ ለተከሳሾቹ ጭብጨባ እና ፉጨት
ማሰማት የተከለከለ ሲሆን ተከሳሾች ሲወጡ
ባሳዩት አጋርነትም ከዛሬ በኋላ ካጨበጨባችሁ
እንዳትገቡ እናደርጋለን የሚል ማስፈራሪያም
ተሰጥቷል፡፡ ወ/ ሮ
ስንታየሁ የተባሉ የሬጅስትራር ሰራተኛ
ጭብጨባውን እና ፉጨቱን ለዳኛ በመንገር
(በተለመደ
ቋንቋ በማቃጠር) አጋርነት
እያሳዩ የነበሩትን ወጣቶች ተግባር ለማስቆም
ሞክረዋል፡፡
በድጋሚ
የዞን 9 አባላት የወሰዷቸው ምንም አይነት የአሸባሪነት
ስልጠና እንደሌለ እያረጋገጡ በህገ መነግስቱ
አንቀጽ 18 መሰረት
ማንኛውም ሰው ጭካኔ የተሞላበት ኢሰብአዊ በሆነ መንገድ ክብሩን ከሚያዋርድ አያያዝ ወይም ቅጣት
የመጠበቅ መብት አለው ቢልም በታሰሩ አባላቶቻችን
ላይ የደረሰውን ግርፋት አጥብቆ ያወግዛል፡፡
በሚከተሉት
ስልክ ቁጥሮች በመደወል እንዲሁም ኢሜሎችን
በመላክ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄያችሁን
በማቅረብ አጋርነታችሁን እንድታሳዩ እንጠይቃለን፡፡
ፍትህ
ሚኒስትር አቶ ደሳለኝ ተረሳ
0115-51-50-99 /ext/286
0115-15 35 28
0115-15 35 28
እምባ
ጠባቂ አቶ ልዑል ስዩም / አቶ ገዛኅኝ ተስፋዬ , ህዝብ ግንኙነት 0111-58-06-52/
0115-54-33-36
0115-53 20 73
0115-53 20 73
የፌደራል
ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አቶ አዲሱ ጴጥሮስ 0116293040,
0116293071
0116293071
የፕሬዘዳንቱ
ቢሮ አቶ ገብሩ አብረሃ / አቶ አድነው አበራ 0111-22-67-67 , 0111-24-46-14
0115-51-20-41
0115-51-20-41
ፌደራል
ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት +251115512744
የኢትዩጲያ
ሰብአዊ መብት ኮሚሽን 0
11-550-41-14
ምንጭ፡ የዞን9 ፌስቡክ
Monday, April 28, 2014
Ethiopia file Charges against #FreeZone9Bloggers, Journalists detained over the Weekend
Charges
were brought against a group of bloggers writing for Zone9 and three
journalists detained by security forces on Friday April 25th
and Saturday April 26th.
Friends
of the detainees were told this morning at the Ma’ekelawi, the
central investigation office where the detainees were are kept since
Friday that charges were already filed against the detainees on
Sunday April 27th.
According to journalist Lily Yekoye,
Sunday, April 27, 2014
Ethiopia detains bloggers and journalist
The
Ethiopian government has arrested six independent bloggers and a
journalist in what human rights group Amnesty International has
called a "suffocating grip on freedom of expression".
Six
members of independent blogger and activist group ‘Zone 9’ and a
prominent Ethiopian journalist were arrested on Friday in the capital
Addis Ababa.
All
six bloggers were arrested at night by armed security forces and
taken from their homes to the Federal Police Crime Investigation
Sector ‘Maikelawi’, where political prisoners are alleged to be
held in pre-trial, and sometimes arbitrary detention.
The
Zone 9 group who are said to be very
Subscribe to:
Posts (Atom)





