Thursday, July 10, 2014

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የልብ ህክምና ሆስፒታል መስራች ኢትዮስዊዲሽ የልብ ሃኪም ለ13ወራት ያለምንም ክስ እና ፍርድ ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ ይገኛሉ


Fikru Maru. Privat ኢትዮጵያ አገሬ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ
የስዊድን ቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ ጠዋት እንደዘገበው የ63 ዓመት እድሜ ያላቸው ዶክተር ፍቅሩ ማሩ  በትውልድ ኢትዮጵያዊ  በዜግነት ስዊድናዊ ሲሆኑ፡ እዚህ ስዊድን አገር ውስጥ አሉ ከሚባሉ በጣት የሚቆጠሩ የልብ ሃኪሞች በግምባር  ቀደምትነት ይጠቀሳሉ። ጣቢያው ዶ/ሩ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ  ለመጀመሪያ ጊዜ በልጃቸው አማካኝነት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ መረዳት እንደሚቻለው፡ እኝህ አገር ወዳድ እና በጎ አድራጊ የልብ ህክምና ባለሙያ እንደተራ ወንጀለኛ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቂሊንጦ እስርቤት ከዘመድ፡ከወዳጅ፡ እንዲሁም ከሚወዱት ሙያቸው ተገልለው ሳይማር ያስተማረኝን ወገኔን ልጥቀም ባሉ፡ በእርጅና ዘመናቸው፡ እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ። በትናንትናው  እለት በዋለው ችሎት ላይ  ተገኝተው የነበሩት የዶ/ሩ ልጅ ኤሚ ፍቅሩ ለቴሌቪዥን ጣብያው እንዳስረዱት፡ አባታቸውን ላለፉት ሶስት  ወራት ለመጎብኘት እንዳልቻሉ ነው። በዋና ከተማዋ የሚገኘውን እና ብቸኛ   የሆነውን አዲስ  ልዩ የልብ ህክምና ሆስፒታል  ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ከአምስት ዓመታት በፊት ያቋቋሙት እኝህ አንጋፋ    የህክምና ባለሙያ፡ እሳቸው ብቻ ሊቀይሩት የሚችሉት ካሪዲያክ ደፊብሪለተር cardiac defibrillator የተባለ ወሳኝ ህይወት አድን መሳሪያ የተገጠመላቸው የልብ ህመምተኞች በእሳቸው መታሰር ምክንያት በመሞት ላይ እንደሚገኙ እጅጉን እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል። ዶ/ር ፍቅሩ ተከሰው የታሰሩት በሙስና  ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩት ከቀድሞው የጉምሩክ ሃላፊ ጋር  ምስጢራዊ ግንኙነት አላቸው በሚል ቢሆንም፡ እስካሁን ድረስ ለቀረበባቸው  ክስ፡ ፓሊስ ምንም ዓይነት ተጨባጭ ማስረጃ ሳያቀርብ ላለፉት  አስራ ሶስት ወራት በከፍተኛ እንግልት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።  እጅግ የሚያሳዝነው የሙያ አጋራቸው የሆኑት የቀድሞው የጤና ጥበቃ ምኒስትር እና በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር በመሆን በማገልገል  ላይ የሚገኙ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ይህ ኢሰብዓዊ እና ኢፍትሃዊ ድርጊት እልባት አግኝቶ ዶ/ር ፍቅሩ በሙያቸው በሺሆች   የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የልብ ህምተኞችን ህይወት እንዲታደጉ ምንም ጥረት አለማድረጋቸው አንድ ቀን በታሪክ ፊት ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።
ምንጭ፡ የስዊድሽ ቴሌቪዥን

No comments:

Post a Comment