ህምም የዛሬን አያድርገው እና አቶ ሽመልስ ከማል ቀደምት ከሚባሉት የግል ጋዜጣ ባለቤቶች እና ጋዜጠኞች ነበሩ። ከስራቸው ጋር
በተያያዘም ለእስር ተዳርገው እንደነበር የመመረቂያ ጽሁፌን ለማዘጋጀት ከዛሬ ዓስር ዓመት (አቤት ጊዜው እንዴት ይሮጣልጃል) ኢትዮጵያ ሄጄ እሳቸው እና ባልደረቦቻቸው እንዲጸድቅ ደፋ ቀና ሲሉለት የነበረውው የፕሬስ ረቂቅ ህግ በተመለከተ ባደረግኩላቸው ጥናታዊ ቃለመጥይቅ ላይ ገልጸውልኝ ነበር። እነሆ ዛሬ ምኒስትር ሆነው የቀድሞ የሙያ አጋሮቻቸው የነበሩትን ንጽሃን ኢትዮጵያን በህግ ጠለላ ሆነው ግማሹን ለእስር ገሚሱን ደግሞ ለስደት ማጋለጣቸው ሳያንስ እንዲህ ዓይነት ዓይንአውጣ ውሸት በአደባባይ መናገር ግለሰቡ ታማኝነታቸው ሳይማር ያሰተማራቸውን እና ለተመረቁበት የህግ ትምህርት ስነምግባር ሳይሆን ለማን እና ለእነማን እንደሆነ በየጊዜ እያስመሰከሩ ይገኛሉ። ቦ ጊዜ ለሁሉ አይደለም የተባለው፡ ለማንኛውም ለሳምንታዊው አዲስአድማስ ጋዜጣ የሰጡት ቅጥፈት የተሞላበት ቃለምልልስ ይሄን ይመስላል።
ክስ
ያልተመሰረተባቸው ጋዜጦችና መፅሄቶች
የሚያትምልን አጣን አሉ
“ማተሚያ
ቤቶች አናትምም ማለታው ሊያስመሰግናቸው
ይገባል” አቶ ሽመልስ ከማል
ፍትህ
ሚኒስቴር በ6 የግል
ሚዲያ ተቋማትና ባለቤቶቻቸው ላይ ክስ መመስረቱን
ተከትሎ 16 የሚደርሱ