
ምንጭ: ኢካድፍ
የጦማሪው ማስታወሻ ለ78 ቀናት እና ማእልታት ምንም ዓይነት ክስ ሳይመሰርትባቸው የጓንታናሞ ታናሽ በሆነው ማእከላዊ እስርቤት
የሚንገላቱት የኢትዮጵያ ተስፋዎች፡ ህይወት ላይ የምትጫወቱ ዳኛ፡ፓሊስና አቃቤህግ ተብዬዎች፡ታሪክ ፍርዱን ይሰጣችኋል። የትናንትናው የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ጉዳይ የፍርድቤት ውሎ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ የሚባለው የህግ ስርዓት፡ ለእነማን እና በእነማን
ጠለላ ስር እንድሆነ ለ101ኛ ጊዜ ፍንትው ብሎ ያሳያል። እነ ጠቅላይ ምኒስትር ደሳላኝ ሃይለማርያም አለ የሚሉን ህግ ተርጓሚ እና አስፈጻሚ ሚና እንዲህ ተደበላልቆ ትርጉም ያጣበት ጊዜ ላይ መድረሳችን፡ የዚህች አገር እጣ ፈንታ ከድጡ ወደማጡ እያዘገመ መሆኑን :ጥሩ አመላካች ነው።
No comments:
Post a Comment