Twenty four years old Iranian asylum seeker Hamid has been declared brain dead in a Brisbane hospital following his family's decision to switch off his life support. He had been declared ‘brain dead’ after contracting septicaemia from an infection contracted while in offshore detention on Papua New Guinea’s Manus Island, a refugee advocacy group says. Hamid Kehazaei's family decided to donate his organs
እንኳን ወደ ስደተኞች ዓለም መጡ። ስደተኛነት ምርጫ አይደለም። Welcome to the world of REFUGEES! NOBODY chooses to be a REFUGEE!!!
Tuesday, September 9, 2014
Young Iranian asylum seeker died in Australia for medical neglect
Twenty four years old Iranian asylum seeker Hamid has been declared brain dead in a Brisbane hospital following his family's decision to switch off his life support. He had been declared ‘brain dead’ after contracting septicaemia from an infection contracted while in offshore detention on Papua New Guinea’s Manus Island, a refugee advocacy group says. Hamid Kehazaei's family decided to donate his organs
Calais : de l’exaspération des habitants au désespoir des migrants
Le nombre de sans-papiers à Calais,
dont la très grande majorité souhaite se rendre en Angleterre, a
explosé depuis le début de l'année 2014. Une situation qui pousse
à bout les habitants et les migrants. France 24 est allé à leur
rencontre.
Que
la proposition de Londres doive être prise au sérieux ou non, la
menace lancée par
'Israel 'coercing Eritreans and Sudanese to leave' Human Rights Watch
Saturday, September 6, 2014
አንድም የተሰደደ ጋዜጠኛ የለም: ሚኒስትር ዴኤታ ሽመልስ ከማል
ህምም የዛሬን አያድርገው እና አቶ ሽመልስ ከማል ቀደምት ከሚባሉት የግል ጋዜጣ ባለቤቶች እና ጋዜጠኞች ነበሩ። ከስራቸው ጋር
ክስ
ያልተመሰረተባቸው ጋዜጦችና መፅሄቶች
የሚያትምልን አጣን አሉ
“ማተሚያ ቤቶች አናትምም ማለታው ሊያስመሰግናቸው ይገባል” አቶ ሽመልስ ከማል
ፍትህ ሚኒስቴር በ6 የግል ሚዲያ ተቋማትና ባለቤቶቻቸው ላይ ክስ መመስረቱን ተከትሎ 16 የሚደርሱ
“ማተሚያ ቤቶች አናትምም ማለታው ሊያስመሰግናቸው ይገባል” አቶ ሽመልስ ከማል
ፍትህ ሚኒስቴር በ6 የግል ሚዲያ ተቋማትና ባለቤቶቻቸው ላይ ክስ መመስረቱን ተከትሎ 16 የሚደርሱ
Saturday, August 30, 2014
ክሶቼ የቅጣት ጣሪያቸው እስከ ሞት ድረስ ነው። በእስር ላይ የሚገኘው የህግ መምህሩ እና ጦማሪው ዘላለም ክብረት
ብርቅዬው የኢትዮጵያ ልጅ ዘላለም ክብረት እግር ተወርች እየማቀቀ ከሚገኝበት እስርቤት ስለእስሩ፡ስለአሳሪዎቹ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የህግ አስፈጻሚዎች፡ ተርጓሚዎች (ለመሆኑ ግን ህግ የሚባለው ነገርስ አለ) እና ሌሎች ባለጊዜዎች የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው የሚባለውን ህገመንግስት በመጣስ በእሱ እና በሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ወገኖች ላይ የሚፈጽሙትን ለህሊና የሚዘገንን ድርጊት ለሁለተኛ ጊዜ በከተበው ሃያል ብእሩ እነሆ ብሎናል። ከዘላለም ደብዳቤ ምን ያህል የመንፈስ ጥንካሬ እና ለሰው ልጆች መብት መከበር ያለውን ተጋድሎ እና እስርቤት እንኳን ሆኖ ገዢዎቻችን የጤፍ ቅንጣት ያህል እንደማይፈራቸው ለመገንዘብ ይቻላል። ሌላው በጣም ዘላለምን ልዩ የሚያደርገው እንደዚያ ባለ አሰቸጋሪ ሁኔታ ላይ ሆኖ የደረሱበትንና እየደረሱበት ያሉትን ኢሰብዓዊ በደሎች እያዋዛ በመጻፍ ለተደራሲ ማቅረብ መቻሉ ነው። የዘላለም የህግ እና የሰብዓዊ መብቶች እውቀት በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በዜጎቹ ላይ እየፈጸመ ያለውን ቅጥ ያጣ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ርቃኑን አውጥቶታል። በዚህም የተነሳ ይህ በቀለኛ መንግስት ዘላለምን ለወራት እንዲያም ሲል ለዓመታት እንደ እነ እስክንድር ነጋ፡ ርዕዮት ዓለሙ፡ በቀለ ገርባ እና ሌሎችም እንዲማቅቅ እንደሚፈርድበት ሳይታለም የተፈታ ነው።
Friday, August 22, 2014
በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ብቻ አስር የግል ጋዜጠኞች አገር ጥለው ተሰደዱ ፡ ዶይቸ ቨሌ
የኢትዮጵያ
መንግስት ያስረናል ወይም ሌላ ጠንካራ እርምጃ
ይወስድብናል ብለው የሚሰጉ የግል ጋዜጠኞች
ሃገሪቱን ጥለው
መሰደዳቸውን እንደ ቀጠሉ
ነው።ከሳምንት በፊት ለግል መገናኛ ዘዴዎች
ይሰሩ የነበሩ ሶስት ጋዜጠኞች ከሃገር
ተሰደዋል።በያዝንው ሳምንት ደግሞ ሌሎች
ሰባት ጋዜጠኞች ወደ ውጭ ሃገር ተሰደዋል።
የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት መንግስት
ለትችት ትዕግስት አለመኖሩ፤የአገሪቱ የፍትህ
ስርዓት ከፖለቲካ ጋር መደባለቁና ሚዲያን
የማያበረታቱ አዋጆችንና ፖሊሲዎችን መኖራቸው
ዋንኞቹ ምክንያቶች ናቸው። ባለፉት ጥቂት
ወራቶች እንኳ ከግሉ ሚዲያ ብዙ ጋዜጠኞች
ሲታሰሩ ወይም ሲሰደዱ ሌሎች የህትመት ውጤቶቻቸውን
እንዲዘጉ ተገደዋል። ላለፉት 119
ቀናት
በላይ በእስር ላይ የሚገኙት ጦማሪዎችና
ጋዜጠኞች የተከሰሱበት ምክንያት እንኳ
፤ተሟጋቾቹ እንደሚሉት፤ከታሰሩበት ቀን ጀምሮ
ለ8ኛ
ጊዜ እስከ ተቀጠሩበት ድረስ ያለው የፍርድ
ሂደት ለብዙ ሚዲያዎች፤የህግ ተንታኞችና
ጉዳዩን ለሚከታተሉ አካላት አነጋጋሪ ሆኖ
ዘልቋል።የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስቴር በቅርብ
ጊዜ ሎሚ፤እንቁ፤ጃኖ፤ፋክት መጽሄቶችና አፍሮ
ታይምስ ጋዜጣ ህገ-መንግስታዊ
ስርዓቱን በሃይል ለመናድ የሃሰት ወሬ ነዝተዋል
በሚል ከሷቸዋል።ይህንንም ተከትሎ ከሁለቱ
መጽሄቶች ውጭ ቁጥራቸው 10
የሚሆኑ
የተቀሩት መጽሄቶችና ጋዜጣ ዋና አዘጋጆች
አገር ጥለው ተሰደዋል።
የሎሚ
መጽሄትና የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ጠበቃ አቶ
ተማም አባ ቡልጉ የክስ ሂደቱን ሲያስረዱ
የተከሰሱበት ጭብጥ ህገ-መንግስታዊ
ስርዓቱን ለመናድ ነው የሚል ነው። ይህም
ከጸረ-ሽብር
ህጉ ጋር የተያያዘ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ጋር
የተያያዘ ነው።
እነዚህ
የሚዲያ ውጤቶች የክስ ወረቀት የደረሳቸው
ህትመታቸው ከተዘጋ ወይም እንዳይታተም ከተደረገ
ሁለት ሳምንታት በኋላ ሲሆን ህትመቶቹ ላይ
የወጡ ጽሁፎችን እንደ ክስ ነጥብ አድርጎ አቃቢ
ህግ አንስቷል።እንደ አቶ ተማም አገላለጽ
የተጠቀሱት ነጥቦች እውነት የሚያስከስስ
አለመሆኑን ተናግረው ለምሳሌ ሎሚ መጽሄት
በሰኔ 6/2006
ይዞ
በወጣው "በአለም
በጨቋኝነቱ አቻ የማይገኝለት የሚዲያ ምህዳር
በኢትዮጵያ በሚል ጽሁፍ ነበር።
አቶ
ተማም ከ1997
በኋላ
የወጡት ህገ ወጥ ህጎች ለምሳሌ የጸረ-ሽብር
ህጉ አላስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው እንደምክንያትም
የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ያሉትን ወንጀሎች
ለመቅጣት በቂ መሆኑን ይናገራሉ።
የጋዜጠኞች
መብት ተከራካሪው በምህፃሩ ሲፒጄ የምስራቅ
አፍሪቃ ዳይሬክተር ሚስተር ቶም ሮድስ በኢትዮጵያ
ሁኔታው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱንና
በእስር ቤት የሚገኙ ጋዜጠኞችም ቁጥር መጨመሩን
ይናገራሉ።
ሲፒጄ
ትናንት ባወጣው መግለጫ በርካታ ኢትዮጵያውያን
ጋዜጠኞች ከመንግስት የሚደርስባቸውን ጫና
በመሸሽ ከሃገር ለመሰደድ እየተገደዱ ነው።እዚያው
ሃገር ውስጥ ለመቆየት የሞከሩት ደግሞ ለእስራት
ይደረጋሉ።ጋዜጠኞቹ ለሚመሰረትባቸው ክስም
ሆነ ለሚሰነዘርባቸው ጫና ይህ ነው የሚባል
ተጨባጭ ምክንያት የለም እንደ ድርጅቱ መግለጫ።ቶም
ሮድስ እንደሚሉት ከ2001
ጀምሮ
በነበሩት አምስት አመታት ውስጥ ብቻ ከ 40
በላይ
ጋዜጠኞች አገር ጥለው ተሰደዋል።
መርጋ
ዮናስ
ነጋሽ
መሐመድ
ምንጭ፡ ዶይቸ ቨሌ
መንግስቴ የ 15 እና የ14 ዓመት ልጆችን በአሸባሪነት ጠርጥሮ እንደሚያስርም ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ዘላለም ክብረት
ተፃፈ
ከስድስተኛ ተከሳሽ
በዘላለም
ክብረት
ወዳጄ
ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ?
እውን
እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ
ዘዴ አጥተን ወደ snail
mail እንመላለሳለን
ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ?
ለማንኛውም
እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣
ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡
‹‹
….ደብዳቤ
ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣
እንገናኝ
እና ልንገርሽ ሁሉንም….››
የደላው!
ቢያሻው
በደብዳቤ፣ ሲፈልግ በአካል እያማረጠ እኮ
ነው፡፡ ለእኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሁለቱም
ቅንጦት ነው (ወይ
ደብዳቤው አይደርስሽም ወይም አንቺን ማየቴ
ሊገደብ ይችላል)፡፡
ቆይ
ትንሽ የጎን ወሬ ላዋራሽና ምክንያቱን
እነግርሻለሁ፡፡ ‹‹አንቺ›› ተብለሽ በዚህ
ደብዳቤ ስለተጠቀስሽው ‹‹አንቺ››ና ይሄን
ደብዳቤ ለሚያነቡ ወዳጆች የዕምነት ክህደት
ቃሌን በትንሹ ላስፍር፡፡
እመቤት
ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ፍቅረኛ
(Ethiopian by choice) ዱቼ
ሞሶሎኒ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ፤ ወራሪው
ሃይል በመላው ኢትዮጵያ ‹‹ የኢትዮጵያን
ስም እያነሱ መፃፍ ክልክል ነው›› የሚል
ያልተፃፈ አዋጅ አውጆ እንደነበር ይነግሩናል፡፡
በዚህም ምክንያት ፀሀፍቱና አዝማሪያኑ ስውር
መጠሪያ መጠቀም ስላስፈለጋቸው እስከ ዛሬ
ድረስ ተወዳጁ ሕዝባዊ ዘፈን አንቺ ልጅ አንቺ
ልጅ እንደ ስውር የፍቅር ዘፈን ተበርክቷል፡፡
በዘፈኑ ‹‹አንቺ ልጅ ›› የተባለችውም
ኢትዮጵያ ናት፡፡ እኔስ በዚህ ዘመን ‹ይድረስ
ለባለ ታሪኩ›፣ ‹ይድረስ ለባለ ንብረቱ›…
እንደሱ የሀዘን ደብዳቤ ርእስ ‹ይድረስ
ለኢትዮጵያ › በማለት ፋንታ ‹ይድረስ ለአንቺ›
ለማለት ስውር መጠሪያ ተጠቅሜያለሁ?
፤
በፍፁም! ጌቶች
እንደሚሉት ሕገ መንግስቱ የመናገር ነፃነቴን
ሙሉ ለሙሉ አስከብሮልኛልናi
ቧልቱ
ይቆየንና በዚህ ደብዳቤ ርዕስ ዙሪያ ያለማንም
አስገዳጅነት የእምነት ክህደት ቃሌን ላስፍር
አንቺ የተባለችው ኢትዮጵያ አይደለችም፡፡
‹አንቺ› የኔዋ ሀቢቢ ግን ባለሽበት ይድረስሽ፡፡
ውዴ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ያለፈውን
Thursday, August 21, 2014
Ethiopian Court Denies Bail to 3 Journalists & 6 #FreeZone9Bloggers: RSF
Reporters Sans Fronetiers (RSF), one of the International Freedom of Expression watchdogs disclosed this today following yesterday's orchestrated trial held in Ethiopia's capital Addis Ababa. Since the prosecutor couldn't corroborate the fabricated charges against these innocent citizens who did nothing but exercised birthrights, it repeats the two decades tradition by denying bail and adjourning the trial for the 8th times. Here's the details of RSF's reportage about the "hearing".
Three
journalists and six bloggers who have been held
for the past five months were denied bail by a federal court in
Addis Ababa yesterday after the prosecution argued that article 3 of
the 2009 anti-terrorism law, under which they are detained, precludes
release on bail.
The
defence said article 3’s bail prohibition does not apply because
none of them has been individually charged with a specific crime
under the anti-terrorism law. The defence also argued that article 3
violates the constitutional guarantee of the right to release on
bail.
The
three journalists are
Monday, August 11, 2014
"We gave our Confession after being Brutally Treated" Leaked Letter by jailed Zone9 Blogger
![]() |
| Befeqadu Hailu, Zone9 Blogger |
First of all I'd like to thank Mahilet Solomon, for her tremendous job in translating this leaked letter by one of the members of Zone 9 bloggers aka Befeqadu Hailu, just a day after it was published. It shows not only her translation skill but also her unparalleled devotion to the freedom of expression, and above all her care for thousands of fellow Ethiopians who are being incarcerated for the crimes they didn't commit. Befqadu also should be commended for penning this very troubling and obvious account under such brutal circumstances where he, other members of Zone 9 bloggers, journalists, opposition party leaders and their followers have to go through everyday and night in present day Ethiopia. What Befqadu wrote is not something new, however it helps to open our eyes about the alarming situation with regard to the human-rights abuses in Ethiopia especially against those under police custody. The Ethiopian government denied and is still denying all these allegations, even though firsthand experiences by the likes of Befqadu and research documents by other human-rights watchdogs reveal these broad-light gross abuses against innocent and unarmed Ethiopians who did nothing but exercised their constitutional and birthrights. I hope, one day all the culprits of these heinous crimes will be brought to justice and eventually innocent victims of this brutal system will be freed. Here's the full excerpt of the English version of Befqadu's leaked letter from one of Ethiopia's notorious prisons called Kilinto.
"Dear Hyena no need for excuses just eat me” - Ethiopian Proverb By BefeQadu Hailu
Translated by Mahilet Solomon
"So
what do you think is your crime?" I was asked by one of my
interrogators while I was telling him about what I did as a blogger, an
advocate and an activist. Later on, after I was allowed to meet with my
"collaborators" according to my prisoners and asked each other, we found
out we were all asked this same question “what do you think is your
crime”? This describes the overall outcome of our interrogation. Since
they couldn’t figure out what our supposed crime was or what law we were
suspected of violating, we were asked
Sunday, August 10, 2014
‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በጦማሪው በፍቃዱ ሃይሉ ተጽፎ ከቂሊንጦ እስርቤት ሾልኮ የወጣ ጽሁፍ
ይህ በቅርቡ በተለያዩ ድረገጾች እና የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ይፋ የሆነው የዞን ዘጠኝ ጦማር አባል የሆነው እና ከሌሎች አምስት ባልደረቦቹ እና ሶስት ጋዜጠኞች ጋር በህውሃት የጸጥታ ሰራተኞች ታግቶ ላለፉት ሶስት ወራት ያለምንም ክስ እና ወንጀል በቂሊንጦ ምርመራ ክፍል ላይ ባለሰራው ወንጀል ፍዳውን የሚያየው የጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ አጭር ጽሁፍ፡ አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ኢፍትሃዊ ስርዓት እና አምባገነንት በመጠኑም ቢሆን ያሳያል። እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ግን፡ ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ተመሳሳይ ወይም ከዚህ የከፋ ወንጀል እየተፈጸመባቸው ሲሆን እነዚህን በደሎች እንደበፍቃዱ ለህዝብ የሚያደርሱባቸው መንገዶችም ሆነ ችሎታውም እንደሌላችው መገንዘብ ይገባል። ህውሃት፡ ይህን መሰሉን ኢሰብዓዊ ድርጊት ሲፈጽም የመጀመሪያው አይደለም የመጨረሻውም አይሆንም። የበፈቃዱ ሃይሉ፡የአቤል ዋበላ ፡የአስማማው ሃይለጊዮርጊስ ፡የናትናኤል ፈለቀ፡የዘላለም ክብረት፡የኤዶም ካሳዬ፡የማህሌት ፋንታሁን፡የተስፋለም ወልደየስ፡የእስክንድር ነጋ ፡የርዕዮት ዓለሙ፡የውብሸት ታዬ፡የአንዷለም አራጌ፡ የበቀለ ገርባ እና የሌሎች በሺሆች የሚቆጠሩ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ወንጀል፡ ለአገራቸው መቆርቆራቸው እና በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ህጸጾች ለማጋለጥ መድፈራቸው ብቻ ነው።
‹‹ታዲያ
ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!››፣
ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና
እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም
ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው
ሳበቃ፡፡ በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ
ከ‹‹አባሪዎቼ››
ጋር
መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ
ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል፡፡
ይኼ ነው እንግዲህ የምርመራችንን ሒደት
የሚገልፀው ጥያቄ፡፡ ‹‹ተጠርጥረን››
የተያዝንበትን
ጉዳይ የሚያረጋግጥ ሥራ ሠርተን ባለመገኘታችን
Wednesday, August 6, 2014
Ethiopia: 5 Popular Govt critic Magazines & a Newspaper facing criminal charges
* Addis Guday Weekly Magazine, by Rose publishing P.L.C.;
* Lomi Weekly Magazine, by Dadimos Publishing P.L.C;
* Enque Bi-weekly Magazine by Alemayehu Publishing P.L.C;
* Fact Weekly Magazine by Yofa Publishing P.L.C;
* Jano Bi-weekly Magazine by Asnake Publishing P.L.C;
The sixth one is a newly launched weekly newspaper called Afro-Times, which is affiliated to Lomi Magazine.
The
statement claimed that
the decision to lodge criminal charges was taken after several attempts
to convince the magazines to change their practices. It also claimed
that the
public has been "demanding" for legal measures through various
channels. Oh really? Fool me once, shame on you. Fool me twice, shame on
me.
Not surprisingly, Ethiopia's Premier assured the US at the US-Africa summit yesterday
( August 5, 2014) that his government is working hard to fight
"terrorism"; err since when unarmed bloggers, journalists, leaders of
civil societies and opposition parties have become terrorists?
Source: ERTA (Ethiopian Radio & Television Agency)
Source: ERTA (Ethiopian Radio & Television Agency)
ፍትህ ምኒስቴር አምስት የግል መጽሄቶችን እና አንድ ጋዜጣን ህገመንግስቱን በሃይል ለመናድ ሞክረዋል በማለት ከሰሰ
1ኛ ሳምንታዊው አዲስ ጉዳይ መጽሄት፡ እና ሮዝ የግል አሳታሚ ድርጅት
2ኛ ሳምንታዊው ሎሚ መጽሄት፡ እና ዳዲሞስ የግል አሳታሚ ድርጅት
3ኛ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተመው እንቁ እና አለማየሁ የግል አሳታሚ ድርጅት
4ኛ ሳምንታዊ ፋክት መጽሄት እና ዮፋ የግል አሳታሚ ድርጅት
5ኛ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተመው ጃኖ መጽሄት እና አስናቀ የግል አሳታሚ ድርጅት ሲሆኑ
ስደስተኛው እና በቅርብ ጊዜ መታተም የጀመረው አፍሮ ታይምስ የተባለው ሳምንታዊ ጋዜጣ የሎሚ መጽሄት አጋር እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ጠቅላይ ምኒስትራችን አሜሪካን አገር በተካሄደው የአፍሮ አሜሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ መንግስታቸው ከምንግዜውም በበለጠ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ቁርጠኝነቱን ለፕሬዚዳንት ኦባማ እና ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል። ሽብርተኞቹ የተባሉት እንግዲህ፡ በማእከላዊ፡በቃሊቲ፡በቂሊንጦ፡በዝዋይ እና በሌሎች እስርቤቶች ባልሰሩት ወንጀሎች ተይዘው ክስ ሳይመሰርትባቸው ወይም በሃሰት ተወንጅለው የሚሰቃዩት የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች፡ጋዜጠኞች፡የሲቪል ተቋማት መሪዎች፡የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና ተከታዮቻቸው፡ እና ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ መሳሪያ ያልጨበጡ ኢትዮጵያውያን የጸረሽብረተኛ ህጉ ሰለባዎች ናቸው።
Monday, July 14, 2014
ከ ስድስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ጠበቃ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ
‹‹የአካል ነጻነታቸው እንዲከበርም ክስ እንመሰርታለን››
የአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለመጨረሻ ጊዜ ከሚል ማስጠንቀቂያ ጋር ለፖሊስ የሰጠው የ28 ቀን ቀጠሮ ቅዳሜ የሚያበቃበት በመሆኑ የዞን ዘጠኞችና የጋዜጠኞቹን ጉዳይ ሲከታተሉ የቆዩ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና ጋዜጠኞች ቀደም ብለው ፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ደርሰዋል፡፡ምን ይወሰን ይሆን? በሁሉም ልብ የሚመላለስ ጥያቄም ነበር፡፡ከዘጠኙ ታሳሪዎች መካከል ስምንቱን በፍርድ ቤት ሲወክሉ የቆዩት ጠበቃ አምሀም ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ቀደም ብለው ቅጥር ግቢው ተገኝተዋል፡፡
አራት ሰዓት እንደሚጀመር የተገመተው ችሉቱ እስከ አምስት ከሩብ ድረስ በሌሎች ጉዳዩች
ተወጥሮ ቆይቷል፡፡ከማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ነፍጥ ባነገቱ ወታደሮች ታጅበው መምጣት የነበረባቸው ኪቦርድ አንጋቾች
እስራት ያልበገረውን ተስፋቸውን እየዘሩ ሊመጡ አልቻሉም፡፡ሁኔታው አግራሞት የፈጠረባቸው የተወሰኑ ጋዜጠኞች ወደ
መዝገብ ቤት በማምራት መረጃ ጠየቁ፡፡የተሰማው በግቢው ውስጥ የነበሩትን ጠበቃ አምሀ መኮንንን ጨምሮ ያስገረመ፣ ያሳዘነና
ያሳፈረ ነበር፡፡ከጠበቃው ጋር ዳዊት ሰለሞን ያደረገው አጠር ያለ ቃለ ምልልስ እንደወረደ እነሆ፡፡
ጥያቄ---ወደ ፍርድ ቤቱ ሲመጡ በአእምሮዎ ያመላልሱት የነበረው ነገር ምንድን ነው?ጠበቃ አምሀ---ምናልባት ምርመራ ባለመጨረሳችን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠን ይላሉ እያልኩ ነበር፡፡ይህንን ጥያቄ ፍርድ ቤቱ በምን አይነት መንገድ እንደሚመልስ ለማወቅም ፈልጌ ነበር፡፡የሆነው ግን በፍጹም ያልጠበቅነው ነገር ነው፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ያመሩ ጋዜጠኞች ‹‹የልጆቹ መርማሪ ነኝ ያለ ሰው ምርመራዬን በመጨረሴ ለአቃቤ ህግ አስተላልፊያለሁ›› በማለቱ መዝገቡ እንደተዘጋ እንደተነገራቸው እንደነገሩኝ እውነት መሆኑን አጣርቻለሁ፡፡
ጥያቄ --- ሁኔታውን እንደሰሙ ምን አደረጉ?
ጠበቃ አምሀ -- እኛ ከቀጠሮው ሰዓት ቀደም ብለን ግቢው ውስጥ ተገኝተን መርማሪው እንዲህ ዓይነት ነገር ሲያቀርብ መስማት ነበረብን፡፡ በፍጹም እንዲህ አይነት መደረግ እንደሌለበት ቅሬታ እንደተሰማንና የተፈጸመው ነገር ህገ ወጥ መሆኑን ለዳኛው ተናግረናል፡፡
ጥያቄ -- ህገ ወጥ የሆነው ምንድን ነው?
ጠበቃ አምሀ --ለፖሊስ ልጆቹን ለተጨማሪ 28 ቀናት እንዲያስር ፈቅዶለት የነበረው ፍርድ ቤቱ ነው፡፡እስካሁን ድረስ ደምበኞቼ የታሰሩት በፍርድ ቤት እውቅና ነው፡፡ከዛሬ አራት ሰዓት ጀምሮ ግን ደምበኞቼ የታሰሩት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በመሆኑ እስራታቸው ህገ ወጥ ነው፡፡ፖሊስ ልጆቹን ፍርድ ቤት አቅርቦ ምርመራውን መጨረሱን ማስረዳትና ክስ የሚመሰርት ከሆነም ማሳወቅ ይገባው ነበር፡፡የሚመሰርተው ክስ ዋስትና የሚያስከለክልና የማያስከለክል መሆኑን መወሰን የነበረበት ፍርድ ቤቱ ነው፡፡ይህ ሳይደረግ መዝገቡ ተዘግቷል መባሉ ህገ ወጥ ነው፡፡
ጥያቄ -- ከአሁን በኋላ ለደምበኞችዎ ሊያደርጉ የሚችሉት ነገር ምንድን ነው?
ጠበቃ አምሀ -- ሰኞ ወይም ማክሰኞ የደምበኞቼ የአካል ነጻነት እንዲከበር ክስ እመሰርታለሁ፡፡ሰኞን የምንጠብቀው እንደተናገሩት ክስ የሚመሰርቱ ከሆነና የት እንደሚመሰርቱ ለማጣራት ነው፡፡
ጥያቄ --በ‹‹ሃብየስ ኮርፐስ›› ደምበኞችዎ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ክስ የምትመሰርቱት በየትኛው ፍርድ ቤት ነው?
ጠበቃ አምሀ --ክሱን የምንመሰርተው በከፍተኛው ፍርድ ቤት ነው፡፡ጥያቄ --ደምበኞችዎን በማዕከላዊ በወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲጎበኙ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ነገር ግን እስካሁን ድረስ አቤል ዋበላን ሰዎች ማግኘት እንዳልቻሉ እየተናገሩ ነው ምክንያቱን ለማጣራት ሙከራ አድርጋችኋል?
Cases of Zone9 Bloggers & Journalists referred to the Court in the Absence of both the Defendants & their Lawyer
The first instance court of Arada bench was expected to wrap up the
pre-trial ‘hearing’ which took more than 70 days and yet the bloggers
were not even brought before the judge. Mr.Amaha Mekonnen,
a lawyer defending the bloggers & journalists who are detained on
unclear but shaping up to be on terrorism charges expected the first
instance court at Arada bench to rest the pre-trial procedure last
Saturday. The court had set the 12th July hearing for closing arguments
but with an extraordinary move the police referred the case to the
Federal High Court without even the presence of neither the defendants nor their
defense lawyer himself. The shift overlooked the court and contravenes even the
standard procedure of the biased justice system. The lawyer speaks to Dawit Solomon, a journalist based in Addis Ababa about the issue. Here
are the translated excerpts from the interview.
DAWIT: What were your thoughts on your way to the court for Saturday’s procedure?
| Amaha Mekonen Defense Lawyer of Zone 9 bloggers & Journalists |
AMAHA: I expected the police might demand for more
time to wrap up their interrogation as usual. I also sought to see how
the court would reply to this repeated claim of the police.
Nevertheless, to the shock of me and all people who were here what
unfolded was really baffling. Since the detainees were not brought to
the court some journalists went straight to the court’s registrar to ask
about the case. Then a person who claimed himself as “the detective” of
the case told the journalists since he is done with the interrogation
he submitted the case for a prosecutor. He further claimed that the case
is closed. This was what I was told by the journalists then I also went
in to verify which I found it true. They closed the case without the
presence of neither my clients nor me who is
representing them.
DAWIT: What action have you taken after you heard?
AMAHA: We have been to court’s compound way
earlier than the scheduled time of the hearing. When the detectives/police officers presented their arguments it should be in our presence. I
have tried to explain our disappointment to the judge. This is
basically a grave breach of law.
DAWIT: So what is the encroachment? Where is the breach of the law?
Sunday, July 13, 2014
የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች እና ሶስቱ ጋዜጠኞች በሌሉበት መዝገባቸው ተዘጋ
ሁለት
ወር ከሃይ ቀናት በእስር ያሳለፉት ስድስቱ
ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች በሶስት የጊዜ
ቀጠሮ መዝገብ፡በሰንበት ሲመላለሱ ከርመው ትናንት ቅዳሜ በሌሉበት መዝገቡ ለዓቃቤ ህግ
መተላለፉን በቦታው ተገኝታ የነበረችው ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ዘገበች። ሃምሌ ዓምስት
ተቀጥረው የነበሩት ጋዜጠኞች ተስፋለም፡ወልደየስ፡
አስማማው ኃይለጊዮርጊስ፡ኤዶም፡ካሳዬ እና
የህግ መምህር እና የዞን ዘጠኝ ጦማሪ ዘልዓለም
ክብረት፡ እንዲሁም የዞን ዘጠኝ ጦማርያን
ናትናኤል ፈለቀና አጥናፉ ብርሃነ፡በአጠቃላይ
ስድስቱ ተጠርጣሪዎች ፍርድቤት ይቀርባሉ
ተብሎ እስከ ጠዋቱ አምስት ሰዓት ተኩል ድረስ
ሲጠብቅ የነበረው ችሎት ተከታታይ በመጨረሻም
ችሎቱ ማብቃቱ ተነግሮታል። ቆይታው ግራ
ያጋባቸው፡ጠበቃው አቶ አመሃ መኮንን ሁኔታውን
ለማጣራት ችሎት፡ገብተው ሲጠይቁ፡ "ውይ አለቀኮ"፡
የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። "እዚህ ውጭ ቁጭ
ብለን እየጠበቅን እንዴት ነው አለቀ የሚባለው"፡
ብለው ላነሱት ጥያቄም "ስንጠራችሁ፡ አልሰማችሁም፡
የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል"። "ግቢ፡ውስጥ ከሶስት
መቶ ሰው በላይ ተቀምጦ የእነርሱን ጉዳይ
እየጠበቀ፡ጠበቃቸው እዚህ እያለ እንዴት፡አልሰማችሁም
ይባላል" ብለው ቢጠይቁም ጠበቃ አይስፈልጋችውም
ነበር። የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። "ተጠርጣሪዎቹስ
መች ቀረቡ?" ብለው ሲጠይቁም "እነርሱ አይስፈልጉም
ነበር፡ ፖሊስ ይህን መዝገብ ዘግቼ፡ጉዳዩን
ለዓቃቤ ህግ፡ አስተላልፊያለሁ አለ። በዛ
መሰረት መዝገቡ ተዘጋ" በማለት ምላሽ ሰጡት።
ምንጭ: ኢካድፍ
የጦማሪው ማስታወሻ ለ78 ቀናት እና ማእልታት ምንም ዓይነት ክስ ሳይመሰርትባቸው የጓንታናሞ ታናሽ በሆነው ማእከላዊ እስርቤት
የሚንገላቱት የኢትዮጵያ ተስፋዎች፡ ህይወት ላይ የምትጫወቱ ዳኛ፡ፓሊስና አቃቤህግ ተብዬዎች፡ታሪክ ፍርዱን ይሰጣችኋል። የትናንትናው የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ጉዳይ የፍርድቤት ውሎ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ የሚባለው የህግ ስርዓት፡ ለእነማን እና በእነማን
ጠለላ ስር እንድሆነ ለ101ኛ ጊዜ ፍንትው ብሎ ያሳያል። እነ ጠቅላይ ምኒስትር ደሳላኝ ሃይለማርያም አለ የሚሉን ህግ ተርጓሚ እና አስፈጻሚ ሚና እንዲህ ተደበላልቆ ትርጉም ያጣበት ጊዜ ላይ መድረሳችን፡ የዚህች አገር እጣ ፈንታ ከድጡ ወደማጡ እያዘገመ መሆኑን :ጥሩ አመላካች ነው።
Friday, July 11, 2014
ባለፈው ሚያዚያ የተቀሰቀሰውን የተማሪዎች ዓመጽ ተከትሎ መንግስት ሃያ ጠባብ ዓመለካት አላቸው ያላቸውን የኦሮሚያ ቲቪ ጋዘጠኞችን ከስራ አባረረ፡ ሲፒጄ
የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ወይም ሲፒጄ በሚል የምጽሃረ ቃል የሚጠራው ዓለምዓቀፉ ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ ተሟጋች ቡድን ትናንትናው እለት በድረገጹ ላይ እንዳስታወቀው፡ እነዚህ ሃያ የሚሆኑ በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚተዳደረው የኦሮሚያ ቴሌቪዥን ባልደረቦች ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከስራ ገበታቸው የተሰናበቱ ሲሆን በዓሁኑ ሰዓት መንግስት በሰበብ አስባብ እንዳያስራቸው በመስጋት ተደብቀው እንደሚገኙ አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ጋዜጠኛ ለሲፒጄ ከሰጠው ቃለመጠይቅ ለመረዳት ተችሏል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጁን 25 እነዚሁ ሰራተኞች ወደ ቴሌቪዥን ጣቢያው መግባት እንደማይችሉ በስራ ሃላፊዎቻቸው እንደተነገራቸው ገልጸው፡ በምን ምክንያት ውሳኔው ሊተላለፍባቸው እንደተቻለ ምንም የተገለጸላቸው ነገር አለመኖሩን ለሲፒጄ አስታውቀዋል።
"መንግስት እሱ በሚፈልገው/በሚመርጠው አስተሳሰብ ሊያጠምቅህ ካልቻለ፡ ከስራ ገበታህ ያፈናቅልሃል"
የጋዜጠኞቹን መባረር ተከትሎ አቶ በረከት ስምኦን እና የፋና ብርድካስት በአዳማ ከተማ ባዘጋጁት ግምገማ የኦሮሚያ ጋዜጠኞች እንዲሳተፉ የተደረጉ ሲሆን፡ ዓላማው የጋዜጠኛውን ክህሎት እና የስራ ብቃት ለማጎልበት ሳይሆን የጋዜጠኞቹን የፖለቲካ አቋም ለመሰል የተሸረበ ሴራ እንደነበረ፡ በዚሁ ግምገማ ላይ የተሳተፉ ጋዜጠኞች ተናግረዋል። ግምገማውን ያዘጋጁት አንዳንድ ካድሬዎች ለጋዜጠኞቹ እንዳሰረዱት፡ የተቋውሞ ሰልፉን በተመለከት የኦሮሚያ ቲቪ ሲያቀርቡት በነበረው ዘገባ ላይ መንግስት ደስተኛ እንዳልነበር ነው።
እንደሲፒጄ ዘገባ፡ እነዚህ ከስራ የተባረሩት ጋዜጠኞች ከአምስት ዓመት በላይ የስራ ልምድ እንዳላቸው ለመረዳት ተችሏል።
ምንጭ ሲፒጄ
Ethiopian Heart Patients are dying due to the imprisonment of A Renown Ethio-Swedish Cardiologist for 13 months
A prominent Ethio-Swedish
cardiologist from Sweden changed the course of medicine and saved
many lives in Ethiopia, but now Dr.Fikru Maru is wrongfully
imprisoned since May, 2013. Ethiopian officials accused him of having
a secret contact with a former chief
of Ethiopian custom's authority, who has been also charged with
suspicion of corruption and in jail since last year.
Right
now, Dr. Fikru is placed in " Kilinto Prison which has
- 3 different zones, and Dr. Fikru belongs to zone 2,
- 7 different rooms, each room carries around 90 prisoners,
- is located in one of the hottest areas of Ethiopia (an average temperature between 35-40 degree Celsius),
- water is very scarce, malaria is rampant and sanitation at its worst.
It's not
only sad but inhumane for a very well known cardiologist to be
treated like petty criminals for the crimes he neither committed nor charged with. He is sleeping on the floor on the flea and mice
infested cell, thousands Kilometers away from his closest family who
live in Sweden. According to his first ever interview he made since
his arrest last year with the Swedish
National Television on July 10th 2014, what saddens
him most at the moment is some of his cardiac patients are dying
since he is the only person who could change cardiac defibrillators
implanted in their body. His Swedish colleagues who used to go and
treat patients at Addis Cardiac Hospital, are not going there for
fear of being detained by the Ethiopian officials.
As a family member said some days ago,
As a family member said some days ago,
Thursday, July 10, 2014
በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የልብ ህክምና ሆስፒታል መስራች ኢትዮስዊዲሽ የልብ ሃኪም ለ13ወራት ያለምንም ክስ እና ፍርድ ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ ይገኛሉ
የስዊድን ቴሌቪዥን ጣቢያ ዛሬ ጠዋት እንደዘገበው የ63 ዓመት እድሜ ያላቸው ዶክተር ፍቅሩ ማሩ በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ስዊድናዊ ሲሆኑ፡ እዚህ ስዊድን አገር ውስጥ አሉ ከሚባሉ በጣት የሚቆጠሩ የልብ ሃኪሞች በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ። ጣቢያው ዶ/ሩ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር ላይ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በልጃቸው አማካኝነት ጋር ባደረገው ቃለምልልስ መረዳት እንደሚቻለው፡ እኝህ አገር ወዳድ እና በጎ አድራጊ የልብ ህክምና ባለሙያ እንደተራ ወንጀለኛ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኘው ቂሊንጦ እስርቤት ከዘመድ፡ከወዳጅ፡ እንዲሁም ከሚወዱት ሙያቸው ተገልለው ሳይማር ያስተማረኝን ወገኔን ልጥቀም ባሉ፡ በእርጅና ዘመናቸው፡ እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ በመሰቃየት ላይ ይገኛሉ። በትናንትናው እለት በዋለው ችሎት ላይ ተገኝተው የነበሩት የዶ/ሩ ልጅ ኤሚ ፍቅሩ ለቴሌቪዥን ጣብያው እንዳስረዱት፡ አባታቸውን ላለፉት ሶስት ወራት ለመጎብኘት እንዳልቻሉ ነው። በዋና ከተማዋ የሚገኘውን እና ብቸኛ የሆነውን አዲስ ልዩ የልብ ህክምና ሆስፒታል ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር በመሆን ከአምስት ዓመታት በፊት ያቋቋሙት እኝህ አንጋፋ የህክምና ባለሙያ፡ እሳቸው ብቻ ሊቀይሩት የሚችሉት ካሪዲያክ ደፊብሪለተር cardiac defibrillator የተባለ ወሳኝ ህይወት አድን መሳሪያ የተገጠመላቸው የልብ ህመምተኞች በእሳቸው መታሰር ምክንያት በመሞት ላይ እንደሚገኙ እጅጉን እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል። ዶ/ር ፍቅሩ ተከሰው የታሰሩት በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩት ከቀድሞው የጉምሩክ ሃላፊ ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት አላቸው በሚል ቢሆንም፡ እስካሁን ድረስ ለቀረበባቸው ክስ፡ ፓሊስ ምንም ዓይነት ተጨባጭ ማስረጃ ሳያቀርብ ላለፉት አስራ ሶስት ወራት በከፍተኛ እንግልት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል። እጅግ የሚያሳዝነው የሙያ አጋራቸው የሆኑት የቀድሞው የጤና ጥበቃ ምኒስትር እና በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ምኒስትር በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ይህ ኢሰብዓዊ እና ኢፍትሃዊ ድርጊት እልባት አግኝቶ ዶ/ር ፍቅሩ በሙያቸው በሺሆች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የልብ ህምተኞችን ህይወት እንዲታደጉ ምንም ጥረት አለማድረጋቸው አንድ ቀን በታሪክ ፊት ተጠያቂ ያደርጋቸዋል።
ምንጭ፡ የስዊድሽ ቴሌቪዥንWednesday, July 9, 2014
የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ የነበሩት እና በየመን መንግስት ባለስልጣናት ተላልፈው የተሰጡት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በኢቴቪ ላይ ቀረቡ
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ለማምራት ባለፈው ሳምንት ሰንዓ ዓየር ማረፊያ ላይ አውሮፕላን ለመቀየር ሲሉ በየመናውያን የጽጥታ ሃይሎች ከተያዙ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የተላለፉ የሚታወስ ሲሆን፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ እይታ የቀረቡት መንግስት በሚቆጣጠረው የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው። ዜና አቅራቢው ተመስገን በየነ ከወትሮው ለየት ባለ ንቃት እና ፈገግታ በመታጀብ አያቱ ሊሆኑ የሚችሉትን ግለሰብ አንተ እያለ በመዘርጠጥ ዜናው ሲያስደምጥ ነበር። አቶ አንዳርጋቸው በዚሁ ተቀናብሮ (ደበበ እሸቱ፡ ብርቱካን ሚዴቅሳ፡ ስዊድናውያን ጋዜጠኞቹን እና ሌሎችም በመቶ የሚቆጠሩ የቀድሞ እስረኞች ልብ ይሏል) በተሰጣቸው የንስሃ በሚመስል ቃለ ምልልስ ላይ፡ በእስር ላይ መዋላቸውን በጸጋነት እንደሚቀበሉት ሲናገሩ ተደምጠዋል። አጃኢብ ነው፡ ውድ የኢትዮጵያ ልጅ ስማ፣ ላልሰማ አሰማ ኢትዮጵያ ውስጥ ማእከላዊ የሚባል እስርቤት ሰላምህን የሚሰጥ ስለሆነ፡ ቦታ እንዳያመልጥህ ተሽቀዳደም። እቺ የተቀነባበረች ዜና የቀረበችው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሌሎች የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የአቶ አንዳርጋቸው ደህንነት እንዳሳሰባቸው በመግለጽ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ዓለምዓቀፍ ዘመቻ በጀመሩበት ሰዓት መሆኑ እነሱም ድራማ መስራት አይሰለቻቸው እኛም መመልከት ያሰኛል። የብሄራዊ ደህንነት ድርጅቱ በተጨማሪ ለተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎች እና ደጋፊዎች፡ ለጋዜጠኞች እና ጦማሪያን እንዲሁም በዞን ዘጠኝ ለሚኖረው ኢትዮጵያዊ በሙሉ በጸረሽብሩ "ህጋችን" ለእስር ከመዳረግ እንደማንድን በገደምዳሜ ተነግሮናል። ለማንኛውም ተመስገንን እንዲህ ያስፈነደቀው ዜና ከዚህ በታች በሚገኘው ቪድዮ ላይ መመልከት ይችላሉ።
Saturday, July 5, 2014
የዞን ዘጠኝ ጦማርያን የማዕከላዊ ፖሊሶች የእምነት ክህደት ቃል በኃይል አስፈርመውናል ይላሉ
ወከባው ቀጥሏል
የፌደራል
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት
በስድስቱ ጦማሪያንና በሦስቱን ጋዜጠኞች ላይ
የፌደራል ፖሊስ የተለያየ ምክንያት እየሰጠ
ቀጠሮ የሚያራዝመውን ሁለት መዝገብ አንዴ
ሲያቀራርበው መልሶ ደግሞ ሲያራርቀው ቆይቶ
አሁን ደግሞ መዝገቦቹን መልሶ አቀራርቧቸዋል።
ችሎቱን በፍርድቤቱ በመገኘት የዘገበችው ጽዮን ግርማ ለኢትዮጵያ ዛሬ ድረገጽ ከላከችው ዘገባ ለመረዳት እንደሚቻለው እስረኞቹ
ራሳቸውን መከላከል በማይችሉበት ኹኔታ ፖሊስ
ያረቀቀውን የእምነት ክህደት ቃል ተገደው
እንዲፈርሙ አድርጓቸዋል። የሦስቱ ብሎገሮች
አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን
ቀጠሮ ሰኔ 22 ቀን
2006 ዓ.ም
እንዲቀርቡ የሚል የነበረ ሲኾን ከጠዋት ጀምሮ
ችሎቱን ለመታደም የመጣውን ቤተሰብ፣ ጓደኞቻቸው፣
ጋዜጠኞች፣ ዲፕሎማቶችና የወጣቶች ደጋፊዎች
በአጠቃላይ ወደ ሦስት መቶ የሚጠጋ ሰው ከችሎት
ውስጥ የሚሰማውን አዲስ ነገር ለመጠበቅ በግቢው
ውስጥ ቆመው ነበር። ከጠዋቱ አራት ሰዓት
አካባቢ
Subscribe to:
Posts (Atom)






