የማንዴላ እና የኢትዮጵያ ቁርኝት ከግማሽ ምዕተዓመት በላይ አስቆጥሯል። ኔልሰን ማንዴላ በአገራቸው እንዳይሰጣቸው የተከለከሉትን ፓስፖርት ለመጀመሪያ ጊዜ በመስጠት ኢትዮጵያ ባለውለታ ስትሆን ይህንን የኢትዮጵያ ፓስፓርት በመጠቀም ማንዴላ ከቦታ ቦታ እንዲንቀሳቀሱ አስችሏቸዋል። ከዚህ ባሻገርም ጠያራ (አውሮፕላን) አብራሪ የተመለከቱት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1962 ወደ አዲሰ ኣበባ ባመጣቸው ጠያራ ውስጥ ነበር። ይህ አጋጣሚ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በወቅቱ ተንሰራፍቶ በነበረው የዘር መድሎኦ በተያያዘ በነበራቸው አሉታዊ ተሞክሮ የተነሳ ከፍተኛ ግርምትን እና የጥቁር ዘር ማንነት ጥያቄ እንደጫረባቸው ለነጻነት የተደረገው ረዥሙ ጉዞ ( Long Walk To Freedom ) በሚል ባሳተሙት መጽሃፋቸው ላይ እንዲህ ሲሉ ገልጽውታል።
በእነዚህ እና በሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች የተነሳ ማንዴላ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ልዩ ስሜት እና ወሰን የሌለው ፍቅር በዚህ መልኩ በመጽሃፋቸው ላይ አስፍረዋል።
ማንዴላ በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የታዘቧቸውን ነገሮችን በዚሁ መጽሃፋቸው ላይ ከትበዋል። ለምሳሌ አዲስ አበባን ከጠበቋት በታች እንዳገኟት እና በጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው የፊውዳል ስርዐት ዴሞክራሲን ለመገንባት ጥሩ እንዳልነበረ።
"Our first stop was Addis Ababa, the Imperial City, which did not live up to its title, for it was the opposite of grand, with only a few tarred streets, and more goats and sheep than cars. Apart from the Imperial Palace, the university, and the Ras Hotel, where we stayed, there were few structures that could compare with even the least impressive buildings of Johannesburg."
"የመጀመሪያው ቆይታችን የንጉስ ነገስቱ መናገሻ በሆነችው አዲስ አበባ ነበር ሆኖም ግን ከጠበቅኩት በተቃራኒው ከመኪኖች የበለጠ በጎች እና ፍየሎች በትናንሽ ጥርጊያ መንግዶችዋ ላይ የሚርመሰመሱባት ትንሽ ከተማ ነበር ያገገኘሁት። ኢዮቤልዩ ቤተመንግስት፣ ከዩኒቨርሲቲው እና እኛ ካረፍንበት የራስ ሆቴል ህንጻዎች በስተቀር በከተማው ውስጥ ጆሃንስበርግ ውስጥ ተራ ከሚባሉት ህንጻዎች ጋር እንኳን ሊወዳድሩ የሚችሉ ህንጻዎች አዲስ አበባ ዉስጥ አልነበሩም።"
በወቅቱ የነበረውን የዘውድ አገዛዝ በተመለከተ ደግሞ ይሄን ታዝበው ነበር።
"Contemporary Ethiopia was not a model when it came to democracy, either. There were no political parties, no popular organs of government, no separation of powers; only the emperor, who was supreme."
"የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ አስተዳደር ለዴሞክራሲ የሚመች ቅርጽ አልነበረም። በአገሪቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ ጠንካራ የሆኑ የመንግስት ልሳኖች ወይም የመንግስት ስልጣን ክፍፍል አልነበሩም። አጼው ሁሉን ነገር ነበሩ፤ አድራጊ ፈጣሪ ከማንም በላይ።"
ማንዴላ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከአጼ ሃይለስላሴም ጋር የተገናኙ ሲሆን ይህንንም በሚከተለው መልኩ ገልጸውታል።
"His Imperial Majesty, who was dressed in an elaborate brocaded army uniform. I was surprised by how small the emperor appeared, but his dignity and confidence made him seem like the African giant that he was. It was the first time I had witnessed a head of state go through the formalities of his office, and I was fascinated. He stood perfectly straight, and inclined his head only slightly to indicate that he was listening. Dignity was the hallmark of all his actions."
"ግርማዊነታቸው ሙሉ እና እጅግ ያሸበረቀ ወታደራዊ ልብስ ተጎናጽፈው ነበር። የቁመታቸውን ማጠር ሳይ በጣም ብደነግጥም የነበራቸው ግርማ እና ሞገስ እንዲሁም በራስ መተማመን ግን የአፍሪካ ታላቅ ሰው እንደነበሩ ያስመስክራል። ለመጀመሪያ ጊዜ አንደ መሪ በጽህፈት ቤቶች እየተዘዋወረ ሲጎበኝ በማየቴ እጅግ በጣም ተደነቅኩ። ቀጥ ያለው አቋቋማቸው እና ትንሽ ዘንበል ያለው ራሳቸው የሚባለውን ነገር እንደሚያዳምጡ ያመላከታል። ክብር እሳቸው ለሚያደርጓችው ማናቸውም እንቀስቃሴዎች ዋነኛ መገለጫ ነበር።"
በወቅቱ የአገሪቱ ፖሊስ ከፍተኛ አዛዥ የነበሩት እና በአጼው ላይ የተቃጣውን መፈንቅለመንግስት ያከሸፉት ኮልኔል ታደሰ ብሩ ለኔልሰን ማንዴላ የወታደራዊ ሳይንስ ስልጠና ኮልፌ በሚገኘው ማሰልጠኛ እንደሰጧቸው ተናግረዋል። በጊዜው የነበረውን የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ እንደሚከተለው ታዝበው ነበር።
"The country was extremely backward: people used wooden plows and lived on a very simple diet supplemented by home-brewed beer. Their existence was similar to the life in rural South Africa; poor people everywhere are more alike than they are different."
"አገሪቱ በጣም ሁላቀር ነች፣ ገበሬው ከእንጨት በተሰራ ማረሻ የሚያርስ ሲሆን የሚበላው ደግሞ ተራ ምግብ ቤት ዉስጥ ከሚጠመቅ ጠላ ጋር ነው። አናኗራቸው ከደቡብ አፍሪካ ገጠርማ አካባቢዎች ጋር ተመሳሳይነት አለው፣ የትም አካባቢ ያሉ ድሆች ከሚለያዩባቸው ይልቅ የሚመሳሰሉባቸው ነገሮች ይበልጣሉ።"
በዚሁ ዐመት ዴቪድ ሞትሰማያዊ በሚል ስም የተዘጋጀ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ማንዴላ ተረከቡ። ወታደራዊው ስልጠናቸው ታቅዶ የነበረው ለስድስት ወራት ቢሆንም በውቅቱ ከንቅናቄያቸው ማለትም ከአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ በቀረበላቸው አስቸኳይ ጥሪ የተነሳ ስልጠናውን በማቋረጥ ወደ አገራቸው ተመለሱ። ኮልኔል ታደሰ ለማንዴላ ወደ ካርቱም የሚያደርጉትን ጉዞ ካመቻቹላቸው በኋላ አውቶማቲክ ሽጉጥ እና ሁለት መቶ ዙር ዝናር ጥይት በስጦታ መልክ እንዳበረከቱላቸው በማመስገን ማንዴላ ዝናሩን
በተመለከተ እንደሚከተለው ይገልጹታል።
"Despite my fatigue marches, I found it wearying to carry around all that ammunition. A single bullet is surprisingly heavy: hauling around two hundred is like carrying a small child on one’s back."
"በዛ ወታደራዊ ስልጠና ሰውነቴ ቢዝልም፤ ዝናር ጥይቱን ከማድረግ ወደኋላ አላገደኝም። አንዷ ጥይት የሚያስደንቅ ክብደት አላት ሁለት መቶ ዙር ዝናር ማደረግ ደግሞ ልክ አንድን ህጻን ልጅ በጀርባ መሸከም ያክል ይከብዳል።"
ኔልሰን ማንዴላ ደቡብ አፍሪካ ከገቡ በኋል ብዙም ሳይቆዩ በወቅቱ የነበረው የነጮች ዘረኛ መንግስ አገርን በመክዳት በሽብርተኝነት እና የሌላ አገርን ፓስፖርት በመያዝ በመክሰስ የእድሜልክ እስራት ከበየነባቸው በኋላ ለሃያሰባት ዐመታት ታስረው እንደ አውሮፓውያኑ ቀመር በ 1990 ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ኢትዮጵያ በጸረ አፓርታይድ ትግሉ ለእርሳቸው እና ለአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ላበረከተችው ወታደራዊ፡ቁሳዊ እና ሞራላዊ ድጋፎች ለማመስገን አዲስ አበባ ሲገኙ በወቅቱ የአገሪቱ መሪ የነበሩት ኮለኔል መንግስቱ ሃይለማርያ ቦሌ ዓለምዓቀፍ አየር ማረፊያ ሲቀበሏቸው የሚያሳየው ምስል ከዚህ በታች ይገኛል።
''We
put down briefly in Khartoum, where we changed to an Ethiopian
Airways flight to Addis. Here I experienced a rather strange
sensation. As I was boarding the plane I saw that the pilot was
black. I had never seen a black pilot before, and the instant I did I
had to quell my panic. How could a black man fly an airplane? But a
moment later I caught myself: I had fallen into the apartheid
mind-set, thinking Africans were inferior and that flying was a white
man’s job. I sat back in my seat, and chided myself for such
thoughts. Once we were in the air, I lost my nervousness and studied
the geography of Ethiopia, thinking how guerrilla forces hid in these
very forests to fight the Italian imperialists.”
"ለጥቂት ጊዜ ካርቱም ካረፍን በኋላ በረራችንን ወደ ኢትዮጵያ አየርመንገድ በመቀየር ጉዟችንን ወደ አዲስ አበባ አቀናን። ይሄ ለየት ያለ ሰሜት ነው የፈጠረብኝ። ወደ ጠያራው ስገባ አብራሪው ሰው የቆዳ ቀለሙ ጥቁር ሆኖ አገኘሁት። በህይወቴ ሙሉ ጥቁር ጠያራ አብራሪ አይቼ ሰለማላውቅ፣ ከፍተኛ የሆነ ደንጋጤን ፈጠረብኝ። እንዴት አንደ ጥቁር ሰው ጠያራ ሊያበር ይችላል በማለት። ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግን እራሴን ፈተሽኩ፤ በደቡብ አፍሪካ ተንሰራፍቶ የሚገኘው የዘር መድሎ ስርዓት የበታችነት አስተሳሰብ እንደተጠመድኩ ተረዳሁ ማለትም አፍሪካውያኖች የበታች አንደሆኑ እና ጠያራ ማብረር ለነጮች ብቻ የተመደበ ስራ እንደሆነ። ወንበሬ ላይ ከተቀመጥኩ በኋላ አንዲህ ዓይነቱን ሃሳብ በማሰቤ ራሴን ወቀስኩ። ልክ አየር ላይ ስንወጣ የነበረኝ መረበሽ ሁሉ ጠፍቶ የኢትዮጵያን መልካዓዊምድር በማየት እንዴት ኢትዮጵያዊያን አርበኞች የአገራቸውን ጫካ ተገን በማድረግ በሽምቅ ዉግያ የጣሊያንን ወራሪ እንዳርበርበዱት መደመም ጀመርኩ።"በእነዚህ እና በሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች የተነሳ ማንዴላ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ልዩ ስሜት እና ወሰን የሌለው ፍቅር በዚህ መልኩ በመጽሃፋቸው ላይ አስፍረዋል።
"Ethiopia
has always held a special place in my own imagination and the
prospect of visiting Ethiopia attracted me more strongly than a trip
to France, England, and America combined. I felt I would be visiting
my own genesis, unearthing the roots of what made me an African. And
he continue to imagine the meeting with the then Ethiopian emperor
as:Meeting the emperor himself would be like shaking hands with
history."
"ኢትዮጵያን ሁልግዜም ሳስባት የነበረው ለየት ባለ ሁኔታ ነው። ወደፈረንሳይ ብሪታንያ እና አሜሪካን ለመጓዝ ሳስብ የሚሰማኝ ስሜት ቢጠቃለል ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ ሳስብ ከሚፈጠርብኝ ደስታ በእጅጉ ያንሳል። ውስጤ የሚሰማኝ ልክ እትብቴ ወደተቀበረበት ቦታ የምሄድ እና አፍሪካዊ ማንነቴን ፈልፍዬ የማገኝበት ስሜት ነበር። ግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴን በአካል ማግኘት ደግሞ እጅግ ታሪካዊ ሁነት ነበር።" ማንዴላ በወቅቱ ኢትዮጵያ ውስጥ የታዘቧቸውን ነገሮችን በዚሁ መጽሃፋቸው ላይ ከትበዋል። ለምሳሌ አዲስ አበባን ከጠበቋት በታች እንዳገኟት እና በጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው የፊውዳል ስርዐት ዴሞክራሲን ለመገንባት ጥሩ እንዳልነበረ።
"Our first stop was Addis Ababa, the Imperial City, which did not live up to its title, for it was the opposite of grand, with only a few tarred streets, and more goats and sheep than cars. Apart from the Imperial Palace, the university, and the Ras Hotel, where we stayed, there were few structures that could compare with even the least impressive buildings of Johannesburg."
"የመጀመሪያው ቆይታችን የንጉስ ነገስቱ መናገሻ በሆነችው አዲስ አበባ ነበር ሆኖም ግን ከጠበቅኩት በተቃራኒው ከመኪኖች የበለጠ በጎች እና ፍየሎች በትናንሽ ጥርጊያ መንግዶችዋ ላይ የሚርመሰመሱባት ትንሽ ከተማ ነበር ያገገኘሁት። ኢዮቤልዩ ቤተመንግስት፣ ከዩኒቨርሲቲው እና እኛ ካረፍንበት የራስ ሆቴል ህንጻዎች በስተቀር በከተማው ውስጥ ጆሃንስበርግ ውስጥ ተራ ከሚባሉት ህንጻዎች ጋር እንኳን ሊወዳድሩ የሚችሉ ህንጻዎች አዲስ አበባ ዉስጥ አልነበሩም።"
በወቅቱ የነበረውን የዘውድ አገዛዝ በተመለከተ ደግሞ ይሄን ታዝበው ነበር።
"Contemporary Ethiopia was not a model when it came to democracy, either. There were no political parties, no popular organs of government, no separation of powers; only the emperor, who was supreme."
"የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ አስተዳደር ለዴሞክራሲ የሚመች ቅርጽ አልነበረም። በአገሪቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆኑ ጠንካራ የሆኑ የመንግስት ልሳኖች ወይም የመንግስት ስልጣን ክፍፍል አልነበሩም። አጼው ሁሉን ነገር ነበሩ፤ አድራጊ ፈጣሪ ከማንም በላይ።"
ማንዴላ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከአጼ ሃይለስላሴም ጋር የተገናኙ ሲሆን ይህንንም በሚከተለው መልኩ ገልጸውታል።
"His Imperial Majesty, who was dressed in an elaborate brocaded army uniform. I was surprised by how small the emperor appeared, but his dignity and confidence made him seem like the African giant that he was. It was the first time I had witnessed a head of state go through the formalities of his office, and I was fascinated. He stood perfectly straight, and inclined his head only slightly to indicate that he was listening. Dignity was the hallmark of all his actions."
"ግርማዊነታቸው ሙሉ እና እጅግ ያሸበረቀ ወታደራዊ ልብስ ተጎናጽፈው ነበር። የቁመታቸውን ማጠር ሳይ በጣም ብደነግጥም የነበራቸው ግርማ እና ሞገስ እንዲሁም በራስ መተማመን ግን የአፍሪካ ታላቅ ሰው እንደነበሩ ያስመስክራል። ለመጀመሪያ ጊዜ አንደ መሪ በጽህፈት ቤቶች እየተዘዋወረ ሲጎበኝ በማየቴ እጅግ በጣም ተደነቅኩ። ቀጥ ያለው አቋቋማቸው እና ትንሽ ዘንበል ያለው ራሳቸው የሚባለውን ነገር እንደሚያዳምጡ ያመላከታል። ክብር እሳቸው ለሚያደርጓችው ማናቸውም እንቀስቃሴዎች ዋነኛ መገለጫ ነበር።"
በወቅቱ የአገሪቱ ፖሊስ ከፍተኛ አዛዥ የነበሩት እና በአጼው ላይ የተቃጣውን መፈንቅለመንግስት ያከሸፉት ኮልኔል ታደሰ ብሩ ለኔልሰን ማንዴላ የወታደራዊ ሳይንስ ስልጠና ኮልፌ በሚገኘው ማሰልጠኛ እንደሰጧቸው ተናግረዋል። በጊዜው የነበረውን የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ እንደሚከተለው ታዝበው ነበር።
"The country was extremely backward: people used wooden plows and lived on a very simple diet supplemented by home-brewed beer. Their existence was similar to the life in rural South Africa; poor people everywhere are more alike than they are different."
"አገሪቱ በጣም ሁላቀር ነች፣ ገበሬው ከእንጨት በተሰራ ማረሻ የሚያርስ ሲሆን የሚበላው ደግሞ ተራ ምግብ ቤት ዉስጥ ከሚጠመቅ ጠላ ጋር ነው። አናኗራቸው ከደቡብ አፍሪካ ገጠርማ አካባቢዎች ጋር ተመሳሳይነት አለው፣ የትም አካባቢ ያሉ ድሆች ከሚለያዩባቸው ይልቅ የሚመሳሰሉባቸው ነገሮች ይበልጣሉ።"
በዚሁ ዐመት ዴቪድ ሞትሰማያዊ በሚል ስም የተዘጋጀ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ማንዴላ ተረከቡ። ወታደራዊው ስልጠናቸው ታቅዶ የነበረው ለስድስት ወራት ቢሆንም በውቅቱ ከንቅናቄያቸው ማለትም ከአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ በቀረበላቸው አስቸኳይ ጥሪ የተነሳ ስልጠናውን በማቋረጥ ወደ አገራቸው ተመለሱ። ኮልኔል ታደሰ ለማንዴላ ወደ ካርቱም የሚያደርጉትን ጉዞ ካመቻቹላቸው በኋላ አውቶማቲክ ሽጉጥ እና ሁለት መቶ ዙር ዝናር ጥይት በስጦታ መልክ እንዳበረከቱላቸው በማመስገን ማንዴላ ዝናሩን
በተመለከተ እንደሚከተለው ይገልጹታል።
"Despite my fatigue marches, I found it wearying to carry around all that ammunition. A single bullet is surprisingly heavy: hauling around two hundred is like carrying a small child on one’s back."
"በዛ ወታደራዊ ስልጠና ሰውነቴ ቢዝልም፤ ዝናር ጥይቱን ከማድረግ ወደኋላ አላገደኝም። አንዷ ጥይት የሚያስደንቅ ክብደት አላት ሁለት መቶ ዙር ዝናር ማደረግ ደግሞ ልክ አንድን ህጻን ልጅ በጀርባ መሸከም ያክል ይከብዳል።"
ኔልሰን ማንዴላ ደቡብ አፍሪካ ከገቡ በኋል ብዙም ሳይቆዩ በወቅቱ የነበረው የነጮች ዘረኛ መንግስ አገርን በመክዳት በሽብርተኝነት እና የሌላ አገርን ፓስፖርት በመያዝ በመክሰስ የእድሜልክ እስራት ከበየነባቸው በኋላ ለሃያሰባት ዐመታት ታስረው እንደ አውሮፓውያኑ ቀመር በ 1990 ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ኢትዮጵያ በጸረ አፓርታይድ ትግሉ ለእርሳቸው እና ለአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ላበረከተችው ወታደራዊ፡ቁሳዊ እና ሞራላዊ ድጋፎች ለማመስገን አዲስ አበባ ሲገኙ በወቅቱ የአገሪቱ መሪ የነበሩት ኮለኔል መንግስቱ ሃይለማርያ ቦሌ ዓለምዓቀፍ አየር ማረፊያ ሲቀበሏቸው የሚያሳየው ምስል ከዚህ በታች ይገኛል።
No comments:
Post a Comment