ከአደጋው
በኋላ ህዝብና ፖሊስ መጋጨታቸውን በግርግሩም
ሶስት ሰዎች በጥይት መቁሰላቸውን የአዲስ
አበባው የዶይቼ ቨሌ ወኪል ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ዘግቧል ።
በሐረር
ከተማ በአንድ ስራውን ባልጀመረ የገበያ ማዕከል በደረሰው የእሳት
አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል
። ከአደጋው በኋላ ህዝብና ፖሊስ የተጋጩት የገበያ ማዕከሉን የእሳት አደጋ መከላከያ ለማዳን ምንም ጥረት ባለማድረጉ እና ማዕከሉ ስራ ባልጀመረበት ሁኔታ ለአምስተኛ ጊዜ እንዲቃጠል መደረጉን በመቃወም ቅሬታቸውን ለማሰማት በመውጣታቸው እንደሆነ ንብረታቸው የወደመባቸው የሃረር ከተማ ነዋሪዎች ለዮሐንስ ገብረ
እግዚአብሔር በምሬት ገልጸዋል። ዮሐንስ በስልክ
ያነጋገራቸው የከተማይቱ ነዋሪዎች እንዳሉት
ትናንት ምሽት በደረሰው በዚሁ የእሳት አደጋ
የገበያ ማዕከሉ ሙሉ በሙሉ ወድሟል ። እሳቱን
ለማጥፋት የአካባቢው ነዋሪዎችም ሆነ የእሳት
አደጋ ሠራተኞች ያደረጉት ጥረት አልተሳካም
።
ዮሐንስ የላከውን የድምጽ ዘገባ ለማዳመጥ እዚህ ጋር ይጫኑ
ምንጭ ዶይቼ ቨሌ
No comments:
Post a Comment