ከ55 ሺሕ በላይ አባላት አሉኝ የሚለው የአዲስ
አበባ አስተዳደር ወጣቶች ፎረም፣ ሁለት መቶ ሺሕ ሰዎች ተሳታፊ የሚሆኑበት ፀረ ተመሳሳይ ጾታ ተጓዳኞች ሰላማዊ ሠልፍ
በመጋቢት ወር 2006 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ለማካሄድ ጥያቄ አቀረበ፡፡
ከቀናት በፊት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደብዳቤ ማስገባቱን፣ የፎረሙ ወጣት ተኮር ዘርፍ ሰብሳቢ ኃይለ ሚካኤል ብዙአየሁ በሳምንት ሁለት ጊዜ ለሚታተመው የመንግስት ደጋፊ እንደሆነ ለሚታማው የሪፖርተር ገልጿል፡፡
ፎረሙ ሰላማዊ ሠልፍ ብቻም ሳይሆን የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች የሚገኙበትና ብዙዎች
የሚካፈሉበት የውይይት መድረክ ለማድረግ ማቀዱም ተገልጿል፡፡ ፎረሙ የፀረ ግብረ ሰዶማዊነት ሰላማዊ ሠልፍ ለማድረግ
ለከተማ አስተዳደሩ ጥያቄ ያቀረበው፣ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማውያንን ሕይወት የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም
ካሳተመው ወይንዬ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከሚሰኝ መንፈሳዊ ማኅበር ጋር በመተግበር እንደሆነ ኃይለ ሚካኤል
ተናግሯል፡፡
ሙሉ ዝርዝሩን ለማንበብ
እዚህ ጋር ይጫኑ።
እዚህ ጋር ይጫኑ።
ወጉ አይቅርብን እኛስ ከዩጋንዳ በምን እናንሳለን ነው፡መቼም ሌላ ምን ሊባል አይችልም። በየእያንዳንዷ ሰከንድ ስንት ኢትዮጵያዊ
በምትደፈርበት፡እንደ ጌኛ ፈረሰ በጋጠ ወጥ ወንዶች በምትጠፈጠፍበት እና ከትምህር ቤት የተሰጣቸውን የቤት ስራ በመስራት ፋንታ
አቅመ ሄዋን ያልደረሱ በሺህ የሚቆጠሩ ህጻናት ገላቸውን ወደው ሳይሆን ተገደው በመቸርቸር ባጨናነቋት የአፍሪካ
መዲና እነሆ ህውሃት እና ተከታዮቹ ተመሳሳይ ጾታ ከመውደድ/ከማፍቀር ውጭ አንዳች ወንጀል ባልሰሩ
ኢትዮጵያውያን ወገኖች ላይ የራሳቸውን የጥላቻ እና የማሳደድ ዘመቻቸውን ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ። እንዲህ ዓይነቱን
የጥላቻ ዘመቻ በማድረግ የህብረተሰቡን ገሃዳዊ እና ነባራዊ ችግሮች ለማረሳሳት ወይም አቅጣጫው ወደሌላው ተጠቂ
ህብረተሰብ እንዲተኮር ማድረግ የአምባገነን መሪዎች እና ካድሬዎቻቸው ብቸኛ ዘዴ ወይም መገለጫ እንደሆነ ከሂትለር
ጀርመን፡ ከሙሴቪኒ ዩጋንዳ ከከጆንሰን ናይጄሪያ እና መሰሎች ለመረዳት ይቻላል። የካድሬዎቹስ ይሁን በጣም
የሚያሳዝነው እና የሚያሳፍረው ግን ፍቅርን፤መቻቻል እና ይቅርባይነትን ለተከታዮቻቸውም ሆነ ለሌሎች መስበክ እና
በተግባር ማሳየት የሚጠበቅባቸው የሃይማኖት መሪዎች የዚህ የጥላቻ ዘመቻ አንድ አጋር መሆናቸው ነው። እነኝህ
የሃይማኖት መሪዎች አንዲት ጊዜ እንኳን በስልጣን ላይ ያለው ህውሃት
መራሹ መንግስት ላላፉት ዓስርት ዓመታት ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ዜጎችን እንዳሻው ሲያስር፡ሲገድል፡ከቤት ንብረታቸው ሲያፈናቅል፡በረሃብ ሲቀጣ እና ሌሎች ለህሊና ዘግናኝ የሆኑ በደሎችን ሲፈጽም ተቋውሞ ያላሰሙ ዛሬ የሞራል ዋስ ጠበቃ ለመሆን ላይ ታች የሚያደርጉት ሩጫ እና ሁካታ ሰው መሳይ በሸንጎ እንጂ ሌላ ምንም ሊባል አይችልም። እስኪ እንጥፍጣፊ የሆነች ሰብዓዊነት ካላችሁ፡ በቃሊቲ፡በዝዋይ፡በቂሊንጦ እና በሌሎች በአገሪቱ እንደ አሸን በፈሉት ማጎሪያዎች ባልሰሩት ወንጀል የሚሰቃዩትን በሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን ወገኖቻችን እንዲፈቱ በገዢው ፓርቲ ላይ ጫና አድርጉ፡ እሱ ካቃታችሁ ደግሞ በየደጃፎቻችሁ ላይ የቀን ጸሃይ የለሊት ቁር ከዓመት ዓመት የሚፈራረቁባቸው እና ተራምዳችኋቸው የምታልፏቸውን ነዳያን ከዚህ ዘላለማዊ ሰቆቃ ታደጓቸው። የዛኔ ነው እንግዲህ የሞራል ጠበቃ በመሆን መከራከር የምትችሉት፡ከዛ በመለስ የምታደርጉት ሁካታ እና ወከባ ከትዝብት ውጭ ምንም የሚያተርፍላችሁ አንዳች ፋይዳ የለም። መጽሃፉም የሚለው፡ ጎረቤትህን እንደራስህ ውደድ እንጂ አሳድ፡አዋክብ ወይም ግደል አይደለም።
No comments:
Post a Comment