ዛሬ ማምሻውን የጀርመን ድምጽ ባሰራጨው ዘገባ በኢትዮጵያ
የቀድሞው የአሜሪካ አምባሳደር ዴቪድ ሺን
ኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነታቸውን ወደ ሰላማዊ
መንገድ ለመመለስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊወያዩ
ይገባል ሲሉ አሳሰቡ። አምባሳደሩ ፣ ከዚህ
ቀደም በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት በተደረገ
ድርድር ውጤት ባድመ የኤርትራ መሆኗን
እትዮጵያውያን መቀበል ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ኤርትራ በበኩሏ ፣ አምባሳደሩ እንዳሉት ፤
ኢትዮጵያ በአሰብ ወደብ እንድትጠቀም ልትፈቅድ
ይገባል። አምባሳደር ዴቪድ ሺን ፤ አሰብ
የኢትዮጵያ ናት የሚለው እሳቤ ጊዜው ያለፈበት
ነው ማለታቸውም ተጠቅሷል። እቺ ዛቻ መሰል ማስጠንቀቂያ በርቀት መቆጣጠሪያ የመተላለፏ አንድምታ ምንን ለማመላከት ነው። ለማንኛውም ዘገባውን አምባሳደሩ አሜሪካን አገር ለሚገኘው የጀርመን ድምጽ ባልደረባ የሰጡት ቃለምልልስ እዚህ ጋር በመጫን ያዳምጡ። ህምምም ነገሩ የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ ወይስ ሌላ ድብቅ ዓላማ???
No comments:
Post a Comment