ከዚህ በታች የምትመለከቷቸው ካርታ እና ሰንጠረዥ እንደ አውሮፖውያን አቆጣጠር ከጥቅምት 1999 እስከ ጥቅምት 2013 በተለያዩ የአረብ አገራት በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸሙ ልዩ ወንጀሎችን በዝርዝር የሚያሳዩ ናቸው። ከእነዚህ ወንጀሎች መካከል ማሰቃየት፡ግርፊያ፡ድብደባ፡አስገድዶ መድፈር፡ባርነት፡የሰሩበትን መከልከል እና እራስን ማጥፋት ወዘተ የሚገኙ ሲሆን ወንጀሎቹ የተፈጸሙባቸው ወገኖች ስም፡ ቦታዎች፡ቀን እና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችም ተካተውበታል።
ይህንን መረጃ ያገኘሁት ከአንድ ሰለስደተኞች መብት ላይ ከሚከራከር ድርጅት ድረ ገጽ ላይ ሲሆን በመካከለኛው ምስራቅ ከሚኖሩ
የውጭ አገር ዜጎች ኢትዮጵያውያን የእነዚህ ከላይ የዘረዘርኳቸው ወንጀል ግንባር ቀደም ተጠቂዎች እንደሆኑ ያሳያል። ለእዚህ ድርጅት በተጠቂ ወገኖቼ ስም ምስጋናዬ እያቀረብኩ በእነዚህ ዓመታት 86 ኢትዮጵያውያን የጥቃት ሰለባ መሆናቸውን በዓረብ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃንን፡ ሆስፒታሎችንና ፖሊስ ጣቢያዎችን ምንጭ በማድረግ ይህ አጭር ዘገባ ያሳያል። ዘገባው በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሰለባዎችን ሊያካትት ያልቻለው በመረጃ እጦት እንደሆነ እገምታለሁ። ሌሎቹ በዚህ ዘገባ ላይ ያልተካተቱን እና ህይወታቸውን ያጡ፡በእስር ላይ የሚገኙ፡ የት እንዳሉ የማይታወቁ፡ በየእለቱ ተገደው የሚደፈሩ፡ የሚራቡ የሚጠሙ፡ ቀን ከለሊት ከባርነት ባልተናነሰ መልኩ ያለምንም ክፍያ ወገባቸው እስኪጎብጥ የሚፈጉትን እህቶቻችን እና ወንድሞቻንን ቤቱ ይቁጠረው። እነዚህን ሰንጠረዡ ላይ የሚገኙ መረጃዎችን በዝርዝር ለማየት ከፈለጉ በስተቀኝ በኩል በሁለቱ ሰንጠረዦች መካካል የሚገኘው ትንሽ ሳጥን ላይ የሚገኙትን ትናንሽ ቀስቶች ወደ ፊት እና ወድ ኋላ እንዲሄዱ በመጫን መጠቀም የሚችሉ ሲሆን ከታች የሚገኘው ትልቅ ባለብዙ ቀለማት ሳጥን ደግሞ ወንጀሎቹ የተፈጸሙባቸውን አገራት እና ዓመታት፡ የወንጀሎቹን ዓይነት እና ምን ያህል እንደሆኑ የሚያመለክቱ ናቸው። እነዚህን መረጃዎች ለሌሎች በኢሜይል፡በፌስቡክ፡በትዊተር እና በሌሎችም ማህበራዊ ድረገጾች በማካፈል ይሄን ከእለት ወደ እለት በመካከለኛው ምስራቅ በተለይም በሳውዲ አረቢያ ግፈኞች በወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን አስከፊ ወንጀል ለመላው ዓለም በማዳረሰ የበኩሉዎን የዜግነት እና የሰብዓዊነት ግዴታ እንዲወጡ በመጠየቅ መረጃዎቹን በተመለከተ ጥያቄዎች ካሎት በኢሜይል ወይም ከዚህ ጦማር በታች በሚገኘው የአስተያየት መስጫ ሳጥን ውስጥ ማስቀመጥ ይችላሉ።
No comments:
Post a Comment