ከዚህ በታች ያስቀመጥኳቸው የኢሜይል ምልልሶች ለዛሬው ጦማሬ መነሻ ቢሆኑኝም ለረጅም ጊዜ ግን በውስጤ ሳብላላውና እራሴንም ሆነ ሌሎች ተማርን የምንል ኢትዮጵያውያን ወገኖች እርስበእርሳችን ለመግባባት ወይም መልእክት ለመለዋወጥ ከአማርኛና ሌሎች ኢትዮጵያዊ ቋንቋዎች ይልቅ ለምን ሌሎች የባእድ ቋንቋዎችን መጠቀም እንደምንመርጥ ግራ ያጋባኛል። ስንፍና፡ የአዋቂነት ምልክት ወይስ የራስ የሆነ ነገርን የመጥላትና የማንቋሸሽ አባዜ (self-loathing) ወይም የማንነት ቀውስ (identity crisis) ካልሆነ ሌላ ምን ይባላል? በጣም ግርም የሚለው ደግሞ ከእኛ በላይ ኢትዮጵያዊ ለአሳር የሚሉ ግለሰቦችና ቡድኖች
በዚህ የውጭ ቋንቋ አምላኪነት ተዘፍቀው ማየቱ ከማነጋገር አልፎ ወዴት እያመራን ነው ያሰኛል። አዲስ አበባ በሚገኙ ብዛት ያላቸው የግል ት/ቤቶች "በት/ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ አማርኛ መናገር እና ድንጋይ መወርወር ክልክል ነው" የሚሉ አሳፋሪ ማስታወቂያዎችን ማየት እንደተራ ነገር ከመቆጠር አልፎ በጣም ጥራት ያለው ት/ቤት ምልክት እየሆነ ከመጣ አስርት ዓመታትን አስቆጥሯል።
"From: Theodros Arega
To: R*****k Me*****a <r*****k.*@gmail.com>
Sent: Sunday, June 23, 2013 11:47 PM
Subject: Re: SV: ስዊድንኛ መጠቀም ለምን አስፈለገ?
To:
Sent: Sunday, June 23, 2013 11:47 PM
Subject: Re: SV: ስዊድንኛ መጠቀም ለምን አስፈለገ?
እኔም አመሰግናለሁ። ግን ግን እንግሊዚኛውም እኮ ያው አልሸሹም ዞር አሉ ነው፡ አይ የኛ ነገር፡ ብቻ ይቅር
Hi
Thanks
for your comment.
Regards
Skickat
från min Samsung Mobil
-------- Originalmeddelande --------
Från: Theodros Arega
Datum: 23-06-2013 0:54 (GMT+01:00)
Till: R*****k Me*****a
Rubrik: ስዊድንኛ መጠቀም ለምን አስፈለገ?
-------- Originalmeddelande --------
Från: Theodros Arega
Datum: 23-06-2013 0:54 (GMT+01:00)
Till: R*****k Me*****a
Rubrik: ስዊድንኛ መጠቀም ለምን አስፈለገ?
አመሰግናለሁ ስለ መልእክቱ ግን
ያልገባኝ ነገር ስዊድንኛ መጠቀም ለምን
አስፈለገ? ይህ ዝግጅት
የተጠራው ለኢትዮጵያውያን ነወይስ ስዊድናውያንም
ጭምር ነው? ወይስ ሰማኒያ
ሚሊዮን ኢትዮጵያዊው የሚገለገልበት
የአማርኛ ቋንቋ ከስዊድንኛ ስለሚያንስ ነው?
በዚህ መልኩ ነው የአገርን ባህልና
ትውፊት የምናስከብረው፡ለልጅልጆቻችን የምናስተላልፈው? ይ ሄ
በጣም የሚያሳዝን የሚያስተዛዝብና
ባጭሩ መቀጨት ያለበት ልምድ ይመስለኛል።
From: R*****k Me*****a <r*****k.*@gmail.com>
To:
Sent: Saturday, June 22, 2013 11:59 PM
Subject: Inbjudan
To:
Sent: Saturday, June 22, 2013 11:59 PM
Subject: Inbjudan
Hej
alla!
Vi
har på grund av olika förhinder inte kunnat ha tidigare
Get-together möten. Men nu har vi glädjen att meddela er om
att det är dags för ett nytt Get-together möte.
Detta kommer att äga rum den 29 juni kl 14.00 plats
Hägerstensvägen 162 i Fenix lokalen. Om vädret tillåter så
är vi ute och grillar och platsen för grillning kommer
att hållas på stranden i Axelsberg. Vi går i samlad trupp
tillsamman.
Vi
hälsar er välkomna
Organisatörerna"
ለምሳሌ ይህ ከላይ የምትመለከቱት መልእክት የደረሰኝ እዚህ ስዊድን አገር ከሚገኝ የተቃዋሚ ፓርቲ ሲሆን ነገርየው በየወሩ በሚያካሄደው የኢትዮጵያውያን የመገናኛ መድረክ ላይ እንድገኝ የሚጠይቅ በስዊድንኛ የተጻፈ የግብዣ ጥሪ ነው። ይሄን ጉዳይ በተመለከተ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ተነጋግረንበት አንዳንዶቹ እንዲህ ዓይነቱ ልምድ ተገቢ እንዳልሆነ አምነውበት በአሁን ወቅት አብዛኛው የምናደርጋቸው የመልእክትም ሆነ የመረጃ ልውውጦች የግዕዝ ወይም የላቲን ፊደላትን በመጠቀም በአማርኛ ሲሆን ሌሎች ግን ሞት ቢመጣ ከስዊድንኛ ወይም ከእንግሊዘኛ ውጭ እንደማይጠቀሙ አቋማቸውን አሳውቀዋል፡ ለዚህ እንደምክንያት የሚያቀርቡት ኮምፒውተራቸው ላይ የግዕዝ ፊደል ሶፍትዌር አለመኖሩን አለዚያም ደግሞ የአማርኛ ቋንቋን ለጽሁፍ መጠቀም ከባድ እና አስቸጋሪ እንደሆነ ነው። ምነው ስንት የማይጠቅም ፍሬከርስኪ በምናጨናንቀው ኮምፒውተር ላይ በነጻና በቀላሉ መጫን የሚቻለውን የግዕዝ ፊደላት ሶፍትዌር ለመጫን እንደምን ተሳነን? እንደዚች አይነቷ ሰበብ እንኳን ዶሮን ሲያታልሏት ዓይነት እንጂ ሌላ ምንም ሊባል አይችልም።
የሚቀጥለው የኢሜይል መልእክት የደረሰኝ ደግሞ ከአንድ በውጭ አገር ከሚገኝ በኢትዮጵያዊያን የሚንቀሳቀስ ድረገጽ ሲሆን እንዲህ ዓይነቱ በእንግሊዘኛ የሚካሄድ የመልእክት ልውውጥ ሳቀበል ይሄ የመጀመሪያዬ አይደለም ምንም እንኳን እኔ መጀመሪያ መልእክቴን አማርኛን ተጠቅሜ ብልክላቸውም።
"From: Theodros Arega
To: ***** Ethiopia <s*******ol100@gmail.com>
Sent: Sunday, June 23, 2013 11:49 PM
Subject: Re: ስደተኛው iREFUGEE:ቢግብራዘርአፍሪካ፡ቤቲ፡እና እኛ
Sent: Sunday, June 23, 2013 11:49 PM
Subject: Re: ስደተኛው iREFUGEE:ቢግብራዘርአፍሪካ፡ቤቲ፡እና እኛ
እሺ ችግር የለውም future ነው ወይስ feature:)
From: ***** Ethiopia
To: "iREFUGEE, Theodros Arega"
Sent: Sunday, June 23, 2013 2:12 AM
Subject: Re: ስደተኛው iREFUGEE:ቢግብራዘርአፍሪካ፡ቤቲ፡እና እኛ
Sorry Arega, we don't future anything related to that topic.
2013/6/22 iREFUGEE, Theodros Arega <theoyesaddis@yahoo.co.uk>
iREFUGEE, Theodros Arega has sent you a link to a blog:
ሰላም ቤቲን እና ቢግ ብራዘር አፍሪካን የሚመለከት ጦማር ልኬላችኋለሁ፡ በድረገጻችሁ ታትሙልኝ ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ። ቴዎድሮስ አረጋ ስቶክሆልም ስዊድን
Blog: ስደተኛው iREFUGEE
Post: ቢግብራዘርአፍሪካ፡ቤቲ፡እና እኛ
Link: http://irefugee.blogspot.com/2013/06/blog-post.html
--
Powered by Blogger
http://www.blogger.com/ "
ህምምም እንዴ ቋንቋ ፍጠሩ እኮ አልተባልንም፡ ተስተካክሎ እና ተበጅቶ ለሺህ ዓመታት ከትውልልድ ሲወራረስ የኖረን ቋንቋ መጠቀም እና ማዳበር ለምን እንዲህ ዳገት እንደሆነብን በጣም ያሳዝናል። ሌሎች አገሮች እኮ ሞቶ የተቀበረ ቋንቋቸው እንዲያንሰራራ ስንት መዋእለ ንዋይ ሲያፈሱ እኛ ግን በስነጽሁም ሆነ በስነቃል የዳበረና ልንኮራበት የሚገባንን ቋንቋ ገድሎ ለመቅበር የምናደርገው ሩጫ ነገ በታሪክም ሆነ በሚመጡት ትውልዶች ከተጠያቂነት አያድነንም። እርሶስ በእለት ተእለት ውሎዎ ምን ያህል ኢትዮጵያዊ ቋንቋዎችን ከሌሎች ኢትዮጵውያን የቤተሰቦ አባላትም ሆነ ወዳጅ ዘመዶቾ ጋር መልእክት ለመለዋወጥ ይጠቀሙባቸዋል? ወይስ እንዳአብዛኛዎቻችን የአማርኛ ፎቢያ ተጠናውቶታል? እስቲ ሁላችንም ራሳችንን እንፈትሽ?
No comments:
Post a Comment