የቅርብ አለቆቹ በጣም ሲያቸግሩት "ኢችም እንጀራ ሆና ሚጥሚጣ በዛባት" ይል ነበር አንድ ኤርሚያስ/ዩሱፍ የሚባል ጋምቤላ ከዓመታት በፊት ለመምህርነት በሄድኩበት ወቅት የተወዋወቅኩትና አሁን በህይወት የሌለ መምህር አፈሩ ይቅለልትና። በስንት ዘመኔ የረሳኋትን ተረት ለዚህ ጽሁፍ መግቢያ እንድጠቀም ያነሳሳኝ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ አንድ የጦማሬ ተከታታይ በኢትዮጵያ የጦማሬን እንዳትጎበኝ የመታገዷን ዜና እንኳን ደስ አለህ ብሎ ስላበሰረኝ ከዚህ ብስራት ጋር በተያያዘ ለመጦመር በማሰብ ነው። ለነገሩ ጦማሬ እንዲህ ዓይነት እጣ እንደሚጠብቃት ባስብም፡በትክክል እገዳው እንደተጣለባት ማረጋገጫውን እንዲሰጠኝ ጠይቄው እነሆ ዛሬ ይሄ እገዳ በትክክል እንደተደረገ ከላከልኝ ማስረጃ ለማወቅ ችያለሁ። እንዲዚህ የ የጦማሬ ተከታታይ ገለጻ ከሆነ ማንም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር የኢንተርኔት ተጠቃሚ የጦማሬን የድረ ገጽ አድራሻ www.irefugee.blogspot.com በመጻፍ ለመግባት ሲሞክር የሚከተለው የእገዳ መልእክት ይደርሰዋል።
The requested URL could not be retrieved
While trying to retrieve the URL: http://www.facebook.com/l/HAQEBMIL1AQG6vdD5h4p64gDcIwjBBV9OCBMk0sR2__mXww/irefugee.blogspot.com/2012/06/2012.html?spref=tw
The following error was encountered:
We can not connect to the server you have requested.
This means that:
The server might be busy at this time.
The server is not reachable.
Please try later to see if you can go through.
Generated Tue, 05 Jun 2012 06:46:48 GMT
While trying to retrieve the URL: http://www.facebook.com/l/HAQEBMIL1AQG6vdD5h4p64gDcIwjBBV9OCBMk0sR2__mXww/irefugee.blogspot.com/2012/06/2012.html?spref=tw
The following error was encountered:
We can not connect to the server you have requested.
This means that:
The server might be busy at this time.
The server is not reachable.
Please try later to see if you can go through.
Generated Tue, 05 Jun 2012 06:46:48 GMT
ይሄ እገዳ በትክክል ስራ ላይ የዋለው መቼ እንደሆነ በትክክል ባላውቅም ይህ ግለሰብ ጦማሬን ለመጎብኝት ባለፈው ዓርብ ሰኔ 1 2004 ዓ᎐ም᎐ ሞክሮ ሊሳካለት ባለመቻሉ ጦማሬን ለመጎብኘት ሌላ ህብኡ (ፕሮክሲ ሰርቭር) ለመጠቀም እንደተገደደ ገልጾልኛል። እኔም እገዳው በትክክል መፈጸሙን ለማረጋገጥ ባደረግኩት ማጣራት የሚከተለውን ውጤት አግኝቻለሁ። በጦማሬ ላይ በኢትዮጵያ የደህንነትና መረጃ መ/ቤት ከመጣሉ በፊት ባሉት ቀናት/ሳምንታት እና ወር ጦማሬን ከኢትዮጵያ የጎበኙት ሰዎች ቁጥር ዝርዝር ይሄን ይመስላል። ባለፈው ሳምንት
ከኢትዮጵያ ጦማሬን 14 ሰዎች እንደጎበኙት ያገኘሁት መረጃ የሚያሳይ ሲሆንከመቶ አርባ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያው ውስጥ የሚኖሩ ጎብኚዎች ደግሞ ባለፈው ወር ጦማሬን እንደጎበኟት የጦማሬ የእለት ከእለት መመዝገቢያ ሰነድ ያሳያል። ከእነዚህ መረጃዎች ለመገመት እንደሚቻለው በርግጥም ጦማሬ በነበረከት ስምኦን ና ሽመልስ መልካም ፍቃድ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳትጎበኝ እገዳ የተጣለባት ወይ ያለፈው ሳምንት አልያም ከዛ በፊት ባለው ሳምንት እንደሆነ ነው። ለዚህ መላምቴ ማረጋገጫ የሚሆነኝ ደግሞ ለተወደዱና ለተከበሩ ጠ/ምኒስትራችን በሃገር አማሪካን የተደረገላቸውን ፍቅር እና አክብሮት የተሞላበት አቀባበል በተመለከተ በእንግሊዝ አፍና በአማርኛ የጦመርኩዋቸውን ጡመራዎች በብዙ መቶ የሚቆጠሩ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ጎብኚዎች ስላነበቡዏቸቸውው ይመስለኛል።
ወይ ጣጣዬ እቺም ጦማር ሆና እነበረከትና ሽመልስ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳትጎበኝ በቆለፏት ቁጥር እንደ እነ አቤ ቶኪቻው ጦማር 1 ጦማር 2 ጦማር ጦማር 101 እያልኩ አዳዲስ ጦማሮች መክፈት ሊኖርብኝ ነው ማለት ነው?
በውጭ ሃገር በሚገኙ ጦማሮች እና የዜና ድረገጾች ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይጎበኙ የሚደረገው አፈና ከተጀመረ ትንሽ ቆየት ቢልም እንዲህ በዘመቻ መልክ የተጠናከረው ግን የተከበሩ ጠቅላይ ምኒስትራችን በቡድን 8 ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አማሪካን አገር ቆይታ አድርገው ከተመለሱ በኋላ ይመስላል። ይህን ክስተት በተመለከተ የኒውዮርክ ታይምስ እና ሃፊንግተንፖስት በጉዳዩ ላይ በዝርዝር የጻፉ ሲሆን በቅርቡ ለአዲስቷ ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ የጋራ ግንባር አኢጋን ይፋ የሆነው እና እጅግ በጣም የሚያስፈራውና የዜጎችን ግለሰባዊ ነጻነት እና ህገመንግስታዊ መብቶች በሚጋፋ መልኩ በገዢው ፓርቲ የደህንነት አካላት በምስጢር ዜጎች በተንቀሳቃሽ ስልኮች የሚያደርጓቸውን የመልእክት ልውውጦች የመጥለፍና የመቅዳት እና የመሰለል ተግባሮች ናቸው። የአኢጋን ውስጣዊ ምንጮች እንዳረጋገጡ ዛሬ ዛሬ በገዢው ፓርቲ የስለላ መረብ እና የኢትዮ ቴሌኮም የተቀናጀ ትብብር በኢትዮጵያ የሚገኙ ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎች በብርጋዴር ጄኔራል ተክለብርሃን ወልደአረጋይ የሚመራው፣ በቀጥታ ተጠሪነቱ ለአቶ መለስ የሆነውና የ“መንፈስ” ያህል የሚፈራው ኢንሳ፤ ዜድቲኢ ከዘረጋው የቴሌኮም አገልግሎቶች ጋር በቀጥታ የተዛመደ ቴክኖሎጂ በቻይና ኮሙኒስት መንግስት አማካይነት በመታጠቁ፣ በዚሁ ቴክኖሎጂ አማካይት የአገሪቱን የመረጃ ፍሰት መቆጣጠር እንዲችል ተሞክሯል። በሌላ አነጋገር ነጻ ሞባይል፣ ነጻ መደበኛ ስልክ፣ ነጻ ኢሜል (ጾዳቤ)፣ ነጻ የፌስ ቡክና ተመሳሳይ አገልግሎቶች በህወሃት የስለላ መዋቅር ውስጥ እንዲወድቁ ተለፍቷል፤ እየተለፋም ነው። ከቴሌ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑ ወገኖች ከጥንቃቄ ጉድለትም ይሁን ባለማወቅየህወሃት/ኢህአዴግን የስለላ ኮሮጆ በየዋህነት እየሞሉ እንደሆነ አይሸሽጉም።* ወደዚህ የስለላ ኮሮጆ ውስጥ የሚገቡ መረጃዎች እንደ አስፈላጊነታቸው ይተነተናሉ። አንዳዶቹም እንደ ሁኔታው እየተቀጠሉና እየተበጠሱ ለፍርድ ቤት የፈጠራ ወንጀል ማስደገፊያነትና ማስረጃነት ይውላሉ። በኢንሳ ከሚገኙት መምሪያዎች መካከል “የስጋት ትንተና (Threat Analysis)” የሚባለው በዚሁ በመቀጠልና በመበጠስ ሥራ የተካነ ስለሆነ ከቤተሰብ፣ ከጓደኛ፣ ከትዳር አጋር፣ ከከንፈር ወዳጅ፣ ከፍቅረኛ፣ ከሥራ ባልደረባ፣
ወዘተ በተለያዩ ወቅቶች የተደረጉ ምልልሶችን ወደኋላ በመመለስ ያገጣጥምና ለይስሙላ ለተቋቋሙት ፍርድ ቤቶች በማስረጃነት ያቀርባል፤ ንጹሃንም ይፈረድባቸዋል። በቅርቡ “አኬልዳማ” በሚል የተሰራው “የወንጀል ድራማ” የዚሁ መምሪያ “የሥራ ውጤት” ነው፡፡ በእነ ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ላይም የተፈጸመው እንዲህ ያለው የቆርጦ ቀጥል ክስና ቃለመጠይቅ ነው።
እንግዲህ የኔዋም ጦማር የቀድሞ ቀጣሪዎቼ እንደስጋት ቆጥረዋት ይመስላል ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች እንዳይጎበኟት እገዳ የጣሉባት። እንደው ልፉ ቢላቸው ነው እንጂ በዚህ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚው በተራቀቀበት ዘመን ህዝብ ለማወቅ የሚፈልገውን ዜናም ሆነ ሌላ ጠቃሚ መረጃ ለማግኘት የሚደረገውን አፈናና አምልጦ የፈለገውን ከማግኘት ወደኋላ እንደማይል በሊቢያ፡በሶሪያ፡ቱኒዚያ እና እንዲሁም በገንዘብ በቁሳቁስና በቴክኒክ በከፍተኛ ደረጃ ከሚያስታጥቃቸው እና በኢንተርኔት ስለላ በጣም በተራቀቀው ቻይና ውስጥ ከሚኖሩ ዜጎች ብዙ ሊማሩ ይገባ ነበር። ይሄ ሁሉ የግብር ከፋይ ገንዘብ፡የሰው ሃይልና ጊዜ የአደባባይ ምስጢር የሆኑ ምስጢሮችን ለመደባበቅ ከሚውሉ ይልቅ ድህነትን፡በሽታን፡ድቁርናን፡ረሃብን እና የመሳሰሉትን በዓለም ደረጃ በቁጥር አንድ ኢትዮጵያ የምትጠራባቸውን ህጸጾች ለማጥፋት ቢውሉ እኛም አንገታችንን ቀና አድርገን ከመራመድ ባሻገር መሪዎቻችን ለጉብኝት፡ ወይም ለሌላ ጉዳይ በስደት ወደምንኖርባቸው አገሮች ብቅ ሲሉ የተቋውሞ ሰልፍ ለማድረግ የምናውለውን ጉልበትና ጊዜ ሲሆን ሲሆን ከበሮ እየደለቅን ፈንዲሻ እየበተንን ጉንጉን አበባ ይዘን ለመቀበል ካልሆነም ለሌላ በጎ ተግባር መከወኛ እናውለው ነበር። በርግጥም ኢቺ የምትመሯት ሃገር ዲሞክራሲ የተትረፈረባት፡ዜጎች ያለምንም ፍርሃት ራሳቸውን የሚገልጹባትና የህግ የበላይነት የተከበረባት ከሆነች፦ይሄ ሁሉ መረጃን በነጻነት በማግኘት ላይ የሚደረግ የእገዳ ጋጋታ ለምን አስፈለገ? እስከ መቼ ህዝብና መንግስት እንደ አይጥና ድመት ተፈራርተን እንዘልቃለን? እኛም እንጦምራለን፡እናንተም አግዱን፡ አንባቢም በፈለገው መንገድ ያገኘናል።
*የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደዘገበው (http://www.ethpress.gov.et/ethpress/main/news.php?
newsLocation=home&newsInstruction=headline&newsId=7249) ከመጋቢት 27 ቀን 2004 ዓም ጀምሮ በኢንሳ ትብብር ኢህአዴግ የመረጃ ፍሰቱን ወደ አንድ ቋት ለማስገባት (www.eprdf.org.et) የተሰኘ አዲስ ድረገጽ በ 1ሚሊዮን ብር ወጪ አዘጋጅቶ ይፋ አድርጓል፡፡ ይህ በግልጽ የሚያሳየው ኢንሳ እንደ ፌዴራል መ/ቤትነቱ ለአንድ ፓርቲ ጥቅም ሳይሆን ለሕዝብ መቆም የሚገባው ሆኖ ሳለ በአንጻሩ ግን የህወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ለራሱ የሥልጣን ማስረዘሚያ ያለአንዳች ተቀናቃኝ የኢትዮጵያን ኃብት እየመዘበረ መሆኑን ነው፡፡ አንድ የፌደራል መ/ቤት በምን ስሌት ነው ለአንድ ፓርቲ ያውም ሥልጣን ላይ ለተቀመጠ እንዲህ ዓይነት አገልግሎት የሚሰጠው?
No comments:
Post a Comment