ሚያዚያ ፳፫/፳፻፬ ዓ/ም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው በስዊድን አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በየዓመቱ በሚከበረው የሜይዴይ በዓል ላይ በመገኘት የህውሃት መንግስት በኢትዮጵያ እያካሄደ ያለውን በኒዮኮሎኒያሊዝም እና በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ዜጎችን ከሚኖሩበት የማፈናቀል ዘመቻ፡የመሬት ቅርጫ፡ እንዲያቆም እንዲሁም ያለአግባብ የታሰሩ ጋዜጠኞችንና የፖለቲካ እስረኞችን ባስቸኳይ እንዲፈታ የተቋውሞ ሰልፍ በማድረግ ጠየቁ። ከዚህ በተጨማሪም የዓለም መንግስታት በከፍተኛ ሁኔታ በህውሃት መንግስት በጭቆና ቀምበር ለሚሰቃየው የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል አጋርነቱ እንዲያሳይና አምባገነን ለሆነው መለሰ ዜናዊ የሚሰጠውን ማንኛውንም እርዳታና ትብብር እንዲያቋርጥ በተቋውሞ ሰልፉ ላይ ጠይቀዋል።
No comments:
Post a Comment