ኧቤት የዚህን ተወዳጅ ፕሮግራም መግቢያ ሙዚቃና የታደሰ ሙሉነህ ማራኪ ድምጽ በስንት ዘመኔ ስሰማው የተሰማኝ የደስታና የሃዘን ቅልቅል ነው፦( ታደሰ ነፍስህ በሰላም ትረፍ። በኢትዮጵያ
ሬዲዮ፣ ቴሌቪዥንና ሌሎች ሚዲያዎች ከ40
ዓመታት
በላይ ያገለገለው ጋዜጠኛ ታደሰ ሙሉነህ ቀብር
ባለፈው ዓርብ ግንቦት 16 2004 ዓ᎐ም᎐ በገነተ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል፡፡ የ 64 ዓመቱ ጋዜጠኛ ታደሰ ሙሉነህ በኢትዮጵያ
ሬዲዮ ከዜና አንባቢነት እስከ ዜና ዋና
አዘጋጅነትና በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች
ከማገልገሉም በላይ፣ ከ1970ዎቹ
መጀመርያ ጀምሮ ተወዳጅ የነበረው ‹‹የእሑድ
ጧት ፕሮግራም›› መሥራችና ዋና አዘጋጅ
ነበረ፡፡
አቶ
ታደሰ ጡረታ ከወጣም በኋላ ከሙያው ሳይለይ
የራሱን ማስታወቂያ ድርጅት በማቋቋም የማስታወቂያ
ሥራዎችን ከማከናወኑ ባሻገር፣ በሸገር ኤፍኤም
የ‹‹እሑድ እንደገና›› ፕሮግራም አዘጋጅና
የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት የራዲዮ ፕሮግራም
ይመራ ነበር፡፡ በሙያው ካገኛቸው በርካታ
ሽልማቶች መካከል ከኢትዮጵያ የሥነ ጥበባትና
መገናኛ ብዙኀን ሽልማት ድርጅት ያገኘው
በዋናነት ይጠቀሳል፡፡
ታደሰ ሙሉነህ እና ባልደረቦቹ (ባልሳሳት የአሜሪካን ድምጽ አማርኛ ክፍል ባልደረባ አዲሱ አበበ አንዱ ነበር) በኢትዮጵያ የመዝናኛ ሬዲዮ ፕሮግራም ዘርፍ