Tuesday, February 11, 2014

ሰው ለሆኑ ሰዎች በሙሉ! በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፤ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት

የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡
‹‹ይህንን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መወያየት ክልክል ነው፡፡›› በማለት በተንጎላጀጀ ድምፅ ጠባቂው ተናገረ፡፡ ቀጠል አደረገናም ‹‹መነጋገር የምትችሉት ስለቤተሰብ ጉዳዮች ብቻ ነው›› በማለት ተናገረ፡፡ ይህን ከላይ ያለውን ሐሳብ የሚመለከት ማንኛውም አንባቢ፣ ጉዳይ የተፈፀመው እዚህችው እማማ ኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ አጃኢበኛ እስር ቤቶች፣ ቤተሰብ መጠየቂያው እንደሆነ መጣራቱ አይቀርም፡፡

ይሁንና በመግቢያው ላይ ያለው ጽሑፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ‹እናት› ከተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1906 ከታተመው የስመ ጥሩው ሩስያዊ ደራሲ ማክሲም ጎርኪይ ታሪካዊ ልቦለድ ገፅ 102 ላይ ነው፡፡ የዛሬ 108 ዓመት አካባቢ ማለት ነው፡፡ አቤት ርቀቱ!... ይህ ርቀት ግን ለእኛ ምንም ማለት ያልሆነ ይመስላል፤ ለምን? ቢሉ ዛሬም ይህንንና ይህን የመሳሰለውን አስፍተን እየሠራን እንገኛለን፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ሁኔታዎች እየተጓዝን ያለነው የቁልቁለት ሩጫ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል፡፡

የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡

Thursday, February 6, 2014

አቶ በቀለ ገርባ የአመክሮ መብታቸውን ተከለከሉ

በእስር ላይ የሚገኙት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ የእስር ጊዜያቸውን ቢጨርሱም መክሮ መከልከላቸው ተሰማ። ህክምናም እያገኙ ኣይደለም ተብሏል። የኮንግረሱ ዋ/ጸኃፊ ለዶቸቬሌ እንደ ነገሩት ከሆነ አቶ በቀለ ገርባ የ 3 ዓመት ከ 7 ወር የእስር ጊዜያቸውን ጠናቀው መለቀቅ የነበረባቸው ባለፈው ጥር 11 ቀን ነበር
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሺን በበኩሉ የዚህ ኣይነት ቅሬታ እስከኣሁን እንዳልደረሰው ስታውቋል።
ቀድሞ በዶ/ር መረራ ጉዲና ይመራ የነበረው የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ (ኦህኮ) እና ያኔ በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ይመራ የነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፈዲን) ተዋህደው የፈጠሩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር ነበሩ፤ አቶ በቀለ ገርባ። በያዙት ኃላፊነትም ያለ ግባብ የታሰሩ ኦሮሞዎችን ጉዳይ እየተከታተሉ ለዓለም ዓቀፍ የመብት ተሟጋቾች እና ለሚመለከታቸው ሁሉ ያሳውቁም ነበር። ይኸው ተግባራቸው ያላስደሰተው የኢትዮጵያ መንግስት ታዲያ የኮንግረሱ ዋ/ጸኃፊ አቶ በቀለ ነጋ እንደሚሉት ሸባሪ በሚለው ድርጅት ስም ወንጅሎ ስፈረደባቸው። የተፈረደባቸው ስምንት ዓመት ሲሆን በይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ወደ 3 ዓመት ከ 7 ወር ተሻሽሎላቸው ነበር ዝዋይ እስር ቤት የከረሙት።
አቶ በቀለ ገርባ ከዝዋይ እስር ቤት ጀምሮ ሁን በሚገኙበት የቃሊቲ ወህኒቤትም ታመው ህክምና እንዳላገኙም ነው እየተነገረ ያለው። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሺን ሊቀመንበር የሆኑት አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ግን የዚህ ኣይነት አቤቱታ እስከ     አሁን አልደረሰንም ባይ ናቸው።
ከኢትዮጵያ መንግስት ወከባና እስራት ሸሽተን በጎረቤት ገር እንገኛለን ከሚሉት የኦሮሞ ተወላጆች መካከል ንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ ስደተኛ በበኩላቸው ከአቶ በቀለ ገርባ በባሰ ሁኔታ ህክምና ተነፍገው የሞቱ የኦሮሞ እስረኞችም ሉ ሲሉ ንዳንዶቹን ጠቃቅሷል። ከዚሁ በመነሳት የኢትዮጵያ እስር ቤቶች የስራ ቋንቋ ኦሮምኛ ሆኗል እስከማለትም ተደርሷል። የሰብዓዊ መብት ኮሚሺን ሊቀመንበሩ አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ግን ሊደንቀን ኣይገባም ይላሉ።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ም/ሊቀመንበሩ፤ አቶ በቀለ ገርባ፤ በተፈረደባቸው ዕለት የፍርድ ማቅለያ ስተያየት ይሰጡ ዘንድ እድል ቢሰጣቸውም «ሳላጠፋ የፈረደብኝን ፍ/ቤት ይቅርታ ኣልጠይቅም። ይቅርታ መጠየቅ ካለብኝ የሚጠበቅብኝን ያህል ካልሰራሁለት የኦሮሞን ህዝብ ነው ይቅርታ እምጠይቀው» ሲሉ ችሎቱ ፊት ቆመው መናገራቸው አይዘነጋም።
ምንጭ፡ ዶቸቬሌ

Saturday, February 1, 2014

በታማሚዎች መነገድ ያተርፋል!? ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ (ከማረሚያ ቤት)

የጉዳዩ ባለቤት ባልሰራው ወንጀል 14 ዓመት ከተፈረደበት በኋላ በኩላሊት ህመም በመሰቃየት ላይ የሚገኘው ወገናችን ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ሲሆን ህክምና እንዳያገኝ በቃሊቲ እስርቤት የህክምና ሃላፊዎች ወደው ይሁን ተገደው እየተፈጸመ ያለው የማሰቃያ ጨካኝ  ድርጊት እጅግ ህሊናን የሚነካ እና በማንኛውም መለኪያ እንኳን ዘጠና ሚሊዮን ህዝብ አስተዳድራለሁ ከሚል መንግስት ተብዪ ይቅር እና ከአንድ ተራ  የመንደር ዱርዬ የማይጠበቅ  ነው።  ጽሁፉን ያገኘሁት ከሌላዋ ኢትዮጵያዊ ዓምደኛ ታሳሪ ማለትም ርዕዮት ዓለሙ የፍቅር ጓደኛ ስለሺ ሃጎስ ሲሆን ላነበባችሁት እንደገና ደግማችሁ እንድታነቡት፡ ላላነበባችሁት ደግሞ የህውሃት መራሹ ጨካኝ መንግስት ምን ያህል ህገመንግስታዊም ሆነ ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን ዓለምዓቀፍ የሰብዓዊ እና ግለሰባዊ መብቶችን የሚያስከብሩ ድንጋጌዎችን
በመጣስ የዜጎችን መብት ከእለት ወደ እለት እየሸራረፈ በጥልቀት እንዳታዩት ይረዳችኋል ብዬ አምናለሁ። በጣም የሚገርመው ግን ውብሸት ይሄ ሁሉ ዘግናኝ ግፍ በህግ ጠለላ እያለ ቢፈጸምበትም በውስጡ በቀል ወይም ጥላቻ የለም። ዛሬም የሚሰብከው ፍቅርንና መቻቻል ነው። 
‹‹ጸሐይ በሞቀው-----›› የፍርድ ሂደት ራሴን ለመከላከል አቅርቤው ከነበረው የተከሳሽ የመከላከያ ቃል በኋላ ዳግም ድምጼን ለማሰማት የተመለስኩበት አጋጣሚ ለወራት ሲያሰቃየኝ ለቆየው የኩላሊት ሕመሜ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ‹‹የጤና ባለሞያዎች ››ምንም ሕክምና ሊሰጡኝ እንደማይችሉ በመግለጽ በተራቸው የሕክምና ፋይሌን መዝጋታቸው ቅር ያሰኘኛል፡፡ጥልቅ ፍቅር እና ክብር ላለኝ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከመልካም ዜና ጋር ብወጣ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር፡፡ግን አልሆነማ!ጉዳዮን የበለጠ ግልጽ ለማድረግ ፣በተደረገልኝ የኩላሊት የአልትራ-ሳውንድ ምርመራ ፣በተለይ በግራ ኩላሊቴ ላይ በአሳሳቢ ሁኔታ ፣እጅግ የተከማቸ አሸዋ መኖሩ ተረጋግጧል፡፡በግራም በቀኝም ያሉ ወገኖች ይህን በማንኛውም ጊዜ መመልከት ይችላሉ፡፡(ለጠላትም ለወዳጅም አላልኩም፣ምክንያቱም በግራ እና በቀኝ በተሰለፉት ውድ ኢትዮጵያዊያን መካከል እየከረረ የመጣው የሐሳብ እና የመስመር ልዮነት እንጂ፣ጠብታ የጠላትነት መሰረት እንደሌለው ታሪክ እና እውነት ይመሰክሩታልና፡፡)ለማንኛውም የቃሊቲዎቹ ሐኪሞች ስቃዬ ሊሰማቸው አልቻለም ወይም አልፈለጉም ፡፡ከቶ ለምን ይሆን!?ይህንን ከአስደማሚ የሰቆቃ ድራማ ፣ከጀርባ ሆኖ እየመራ ያለው ባለ ረዥም እጅ ማን ይሆን?ለመሆኑስ አማራጭ በሌላቸው ታማሚዎች ጤንነት መነገድስ ስንት ያተርፋል?ምን ይሉት እርካታንስ ያጎናጽፋል?ከእኛ ስር የበቀለው የነገይቱ ኢትዮጵያችን ተረካቢ ትውልድስ ይህን አስጸያፊ ድርጊት እንዴት ይመለከተዋል ትላላችሁ ?ሁላችንንም ቸር እና ፍጹም የሆነው እግዚአብሄር ይርዳን፡፡በተለይ እኔ ባለሁበት የእስር እና የጤንነት ሁኔታ ላይ የሚገለጽ ሐሳብ ፣ስሜታዊነት ሊንጸባረቅበት ቢችል እንኳ ትረዱኛላችሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ሌሎችን ለመውቀስም የጥላቻ ስሜትንም ለመግለጽ ተደርጎ እንዳይወሰድብኝም በትሕትና እጠይቃለሁ፡፡ክብር እና ፍቅር የሚገባችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን በግሌ የእስር ቆይታዬ በነፍሴ ውስጥ እንደውቅያኖስ የጠለቀ ፍቅር እና የእናንተን አጋርነት በማይነጥፍ አሳቢነት አገኘሁበት እንጂ ጥላቻን አልተማርኩበትም፡፡ ደግሞም እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን፡፡ የታሪክ ፣የእምነት፣የወግና የባህል በአጠቃላይም የማንነት ጽኑ መሰረት አለን፡፡ትናንት የመጣን ነገ የምንሄድ አይደለንም ፣እንኖራለን ቢያንስ ትውልድ ይኖራል፡፡ታዲያ እንዴት ሕክምና በመንፈግ ፣ከቤተሰብ አርቆ በማሰር (የሁለትዮሽ እንግልት ለመፍጠር በማሰብ)ይህንን ማንነት እንጣው?አይሆንም!እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክአክባሪ ወንድማችሁ ውብሸት ታዬ

Thursday, January 30, 2014

Jailed Ethiopian Dissident Blogger Eskinder Nega Honored Once Again

Eskinder Nega, an Ethiopian publisher, journalist and blogger who is serving an 18-year jail sentence under anti-terror legislation, has been awarded the 2014 Golden Pen of Freedom, the annual press freedom prize of the World Association of Newspapers and News Publishers (WAN-IFRA).
Mr Nega was arrested on September 14, 2011 after publishing an article criticising his government’s use of the 2009 Anti-Terror Proclamation to jail and silence critics, including Ethiopian actor and activist Debebe Eshetu.  He was sentenced on 23 January 2012 and denounced as belonging to a terrorist organization.

In making the award, the WAN-IFRA Board sent a message to the Ethiopian government that misusing anti-terror legislation to jail journalists and those critical of his government is unwarranted and against international protocols, including the Vienna Declaration on Terrorism, Media and the Law.

“This award recognizes the courage of Eskinder Nega to speak out despite the risks that saw him