Saturday, August 30, 2014

ክሶቼ የቅጣት ጣሪያቸው እስከ ሞት ድረስ ነው። በእስር ላይ የሚገኘው የህግ መምህሩ እና ጦማሪው ዘላለም ክብረት

ብርቅዬው የኢትዮጵያ ልጅ ዘላለም ክብረት እግር ተወርች እየማቀቀ ከሚገኝበት እስርቤት ስለእስሩ፡ስለአሳሪዎቹ እና በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የህግ አስፈጻሚዎች፡ ተርጓሚዎች (ለመሆኑ ግን ህግ የሚባለው ነገርስ አለ) እና  ሌሎች ባለጊዜዎች የህጎች ሁሉ የበላይ ህግ ነው የሚባለውን ህገመንግስት በመጣስ በእሱ እና በሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውን ወገኖች ላይ የሚፈጽሙትን ለህሊና የሚዘገንን ድርጊት ለሁለተኛ ጊዜ በከተበው ሃያል ብእሩ እነሆ  ብሎናል። ከዘላለም ደብዳቤ ምን ያህል የመንፈስ ጥንካሬ እና ለሰው ልጆች መብት መከበር ያለውን  ተጋድሎ እና  እስርቤት እንኳን ሆኖ  ገዢዎቻችን  የጤፍ ቅንጣት ያህል እንደማይፈራቸው ለመገንዘብ  ይቻላል። ሌላው በጣም  ዘላለምን ልዩ  የሚያደርገው እንደዚያ ባለ አሰቸጋሪ ሁኔታ ላይ ሆኖ የደረሱበትንና እየደረሱበት ያሉትን ኢሰብዓዊ በደሎች እያዋዛ በመጻፍ ለተደራሲ ማቅረብ መቻሉ ነው።   የዘላለም የህግ እና  የሰብዓዊ መብቶች እውቀት በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በዜጎቹ ላይ እየፈጸመ ያለውን ቅጥ ያጣ የሰብዓዊ መብት ረገጣ ርቃኑን አውጥቶታል። በዚህም የተነሳ ይህ በቀለኛ  መንግስት ዘላለምን ለወራት እንዲያም ሲል ለዓመታት እንደ እነ እስክንድር ነጋ፡ ርዕዮት ዓለሙ፡ በቀለ ገርባ እና ሌሎችም እንዲማቅቅ  እንደሚፈርድበት ሳይታለም የተፈታ ነው።

Friday, August 22, 2014

በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ብቻ አስር የግል ጋዜጠኞች አገር ጥለው ተሰደዱ ፡ ዶይቸ ቨሌ

የኢትዮጵያ መንግስት ያስረናል ወይም ሌላ ጠንካራ እርምጃ ይወስድብናል ብለው የሚሰጉ የግል ጋዜጠኞች ሃገሪቱን ጥለው Lomi magazine, Enque magazine, Fact magazine, Jano magazine, Lomi magazine, and Afro-Times newspaperመሰደዳቸውን እንደ ቀጠሉ ነው።ከሳምንት በፊት ለግል መገናኛ ዘዴዎች ይሰሩ የነበሩ ሶስት ጋዜጠኞች ከሃገር ተሰደዋል።በያዝንው ሳምንት ደግሞ ሌሎች ሰባት ጋዜጠኞች ወደ ውጭ ሃገር ተሰደዋል። የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች እንደሚሉት መንግስት ለትችት ትዕግስት አለመኖሩ፤የአገሪቱ የፍትህ ስርዓት ከፖለቲካ ጋር መደባለቁና ሚዲያን የማያበረታቱ አዋጆችንና ፖሊሲዎችን መኖራቸው ዋንኞቹ ምክንያቶች ናቸው። ለፉት ጥቂት ወራቶች እንኳ ከግሉ ሚዲያ ብዙ ጋዜጠኞች ሲታሰሩ ወይም ሲሰደዱ ሌሎች የህትመት ውጤቶቻቸውን እንዲዘጉ ተገደዋል። ላለፉት 119 ቀናት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት ጦማሪዎችና ጋዜጠኞች የተከሰሱበት ምክንያት እንኳ ፤ተሟጋቾቹ እንደሚሉት፤ከታሰሩበት ቀን ጀምሮ ለ8ኛ ጊዜ እስከ ተቀጠሩበት ድረስ ያለው የፍርድ ሂደት ለብዙ ሚዲያዎች፤የህግ ተንታኞችና ጉዳዩን ለሚከታተሉ አካላት አነጋጋሪ ሆኖ ዘልቋል።የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስቴር በቅርብ ጊዜ ሎሚ፤እንቁ፤ጃኖ፤ፋክት መጽሄቶችና አፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሃይል ለመናድ የሃሰት ወሬ ነዝተዋል በሚል ከሷቸዋል።ይህንንም ተከትሎ ከሁለቱ መጽሄቶች ውጭ ቁጥራቸው 10 የሚሆኑ የተቀሩት መጽሄቶችና ጋዜጣ ዋና አዘጋጆች አገር ጥለው ተሰደዋል።
የሎሚ መጽሄትና የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ጠበቃ አቶ ተማም አባ ቡልጉ የክስ ሂደቱን ሲያስረዱ የተከሰሱበት ጭብጥ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ነው የሚል ነው። ይህም ከጸረ-ሽብር ህጉ ጋር የተያያዘ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ጋር የተያያዘ ነው።
እነዚህ የሚዲያ ውጤቶች የክስ ወረቀት የደረሳቸው ህትመታቸው ከተዘጋ ወይም እንዳይታተም ከተደረገ ሁለት ሳምንታት በኋላ ሲሆን ህትመቶቹ ላይ የወጡ ጽሁፎችን እንደ ክስ ነጥብ አድርጎ አቃቢ ህግ አንስቷል።እንደ አቶ ተማም አገላለጽ የተጠቀሱት ነጥቦች እውነት የሚያስከስስ አለመሆኑን ተናግረው ለምሳሌ ሎሚ መጽሄት በሰኔ 6/2006 ይዞ በወጣው "በአለም በጨቋኝነቱ አቻ የማይገኝለት የሚዲያ ምህዳር በኢትዮጵያ በሚል ጽሁፍ ነበር።
አቶ ተማም ከ1997 በኋላ የወጡት ህገ ወጥ ህጎች ለምሳሌ የጸረ-ሽብር ህጉ አላስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው እንደምክንያትም የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ያሉትን ወንጀሎች ለመቅጣት በቂ መሆኑን ይናገራሉ።
የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪው በምህፃሩ ሲፒጄ የምስራቅ አፍሪቃ ዳይሬክተር ሚስተር ቶም ሮድስ በኢትዮጵያ ሁኔታው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መምጣቱንና በእስር ቤት የሚገኙ ጋዜጠኞችም ቁጥር መጨመሩን ይናገራሉ።
ሲፒጄ ትናንት ባወጣው መግለጫ በርካታ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ከመንግስት የሚደርስባቸውን ጫና በመሸሽ ከሃገር ለመሰደድ እየተገደዱ ነው።እዚያው ሃገር ውስጥ ለመቆየት የሞከሩት ደግሞ ለእስራት ይደረጋሉ።ጋዜጠኞቹ ለሚመሰረትባቸው ክስም ሆነ ለሚሰነዘርባቸው ጫና ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ምክንያት የለም እንደ ድርጅቱ መግለጫ።ቶም ሮድስ እንደሚሉት ከ2001 ጀምሮ በነበሩት አምስት አመታት ውስጥ ብቻ ከ 40 በላይ ጋዜጠኞች አገር ጥለው ተሰደዋል።
መርጋ ዮናስ
ነጋሽ መሐመድ
ምንጭ፡ ዶይቸ ቨሌ

መንግስቴ የ 15 እና የ14 ዓመት ልጆችን በአሸባሪነት ጠርጥሮ እንደሚያስርም ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ዘላለም ክብረት

‹‹ይድረስ ላንቺ››
ተፃፈ ከስድስተኛ ተከሳሽ
በዘላለም ክብረት

ወዳጄ ልቤ ከቶ እንደምንድን ነሽ? እውን እኔና አንቺ በአለም ስንኖር ሌላ የመገናኛ ዘዴ አጥተን ወደ snail mail እንመላለሳለን ብለሽ አስበሽ ታውቂያለሽ? ለማንኛውም እንዲህ ሆነ፡፡ ጥጋበኛ ሰው ያስቀናኝ ጀምሮልሻል፣ ጥጋበኛ እንዲህ የሚለው ትዝ አለኝ፡፡

‹‹ ….ደብዳቤ ቢጽፉት እንደ ቃል አይሆንም፣
እንገናኝ እና ልንገርሽ ሁሉንም….››

የደላው! ቢያሻው በደብዳቤ፣ ሲፈልግ በአካል እያማረጠ እኮ ነው፡፡ ለእኔ አሁን ባለሁበት ሁኔታ ሁለቱም ቅንጦት ነው (ወይ ደብዳቤው አይደርስሽም ወይም አንቺን ማየቴ ሊገደብ ይችላል)፡፡ ቆይ ትንሽ የጎን ወሬ ላዋራሽና ምክንያቱን እነግርሻለሁ፡፡ ‹‹አንቺ›› ተብለሽ በዚህ ደብዳቤ ስለተጠቀስሽው ‹‹አንቺ››ና ይሄን ደብዳቤ ለሚያነቡ ወዳጆች የዕምነት ክህደት ቃሌን በትንሹ ላስፍር፡፡

እመቤት ሲልቪያ ፓንክረስት የኢትዮጵያ ፍቅረኛ (Ethiopian by choice) ዱቼ ሞሶሎኒ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ፤ ወራሪው ሃይል በመላው ኢትዮጵያ ‹‹ የኢትዮጵያን ስም እያነሱ መፃፍ ክልክል ነው›› የሚል ያልተፃፈ አዋጅ አውጆ እንደነበር ይነግሩናል፡፡ በዚህም ምክንያት ፀሀፍቱና አዝማሪያኑ ስውር መጠሪያ መጠቀም ስላስፈለጋቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተወዳጁ ሕዝባዊ ዘፈን አንቺ ልጅ አንቺ ልጅ እንደ ስውር የፍቅር ዘፈን ተበርክቷል፡፡ በዘፈኑ ‹‹አንቺ ልጅ ›› የተባለችውም ኢትዮጵያ ናት፡፡ እኔስ በዚህ ዘመን ‹ይድረስ ለባለ ታሪኩ›፣ ‹ይድረስ ለባለ ንብረቱ›… እንደሱ የሀዘን ደብዳቤ ርእስ ‹ይድረስ ለኢትዮጵያ › በማለት ፋንታ ‹ይድረስ ለአንቺ› ለማለት ስውር መጠሪያ ተጠቅሜያለሁ? ፤ በፍፁም! ጌቶች እንደሚሉት ሕገ መንግስቱ የመናገር ነፃነቴን ሙሉ ለሙሉ አስከብሮልኛልናi
ቧልቱ ይቆየንና በዚህ ደብዳቤ ርዕስ ዙሪያ ያለማንም አስገዳጅነት የእምነት ክህደት ቃሌን ላስፍር አንቺ የተባለችው ኢትዮጵያ አይደለችም፡፡ ‹አንቺ› የኔዋ ሀቢቢ ግን ባለሽበት ይድረስሽ፡፡ ውዴ እንግዲህ በዚህ ደብዳቤ ያለፈውን

Thursday, August 21, 2014

Ethiopian Court Denies Bail to 3 Journalists & 6 #FreeZone9Bloggers: RSF

Reporters Sans Fronetiers (RSF), one of the International Freedom of Expression watchdogs disclosed this today following yesterday's orchestrated trial held in Ethiopia's capital Addis Ababa. Since the prosecutor couldn't corroborate the fabricated charges against these innocent citizens who did nothing but exercised birthrights, it repeats the two decades tradition by denying bail and adjourning the trial for the 8th times. Here's the details of RSF's reportage about the "hearing".   
Three journalists and six bloggers who have been held for the past five months were denied bail by a federal court in Addis Ababa yesterday after the prosecution argued that article 3 of the 2009 anti-terrorism law, under which they are detained, precludes release on bail.
The defence said article 3’s bail prohibition does not apply because none of them has been individually charged with a specific crime under the anti-terrorism law. The defence also argued that article 3 violates the constitutional guarantee of the right to release on bail.
The three journalists are

Monday, August 11, 2014

"We gave our Confession after being Brutally Treated" Leaked Letter by jailed Zone9 Blogger

Befeqadu Hailu, Zone9 Blogger
First of all I'd like to thank Mahilet Solomon, for her tremendous job in translating this leaked letter by one of the members of Zone 9 bloggers aka Befeqadu Hailu, just a day after it was published. It shows not only her translation skill but also her unparalleled devotion to the freedom of expression, and above all her care for thousands of fellow Ethiopians who are being incarcerated for the crimes they didn't commit. Befqadu also should be commended for penning this very troubling and obvious account under such brutal circumstances where he, other members of Zone 9 bloggers, journalists, opposition party leaders and their followers have to go through everyday and night in present day Ethiopia. What Befqadu wrote is not something new, however it helps to open our eyes about the alarming situation with regard to the human-rights abuses in Ethiopia especially against those under police custody. The Ethiopian government denied and is still denying all these allegations, even though firsthand experiences by the likes of Befqadu and research documents by other human-rights watchdogs reveal these broad-light gross abuses against innocent and unarmed Ethiopians who did nothing but exercised their constitutional and birthrights. I hope, one day all the culprits of these heinous crimes will be brought to justice and eventually innocent victims of this brutal system will be freed. Here's the full excerpt of the English version of Befqadu's leaked letter from one of Ethiopia's notorious prisons called Kilinto.       

"Dear Hyena no need for excuses just eat me” - Ethiopian Proverb By BefeQadu Hailu

Translated by Mahilet Solomon
"So what do you think is your crime?" I was asked by one of my interrogators while I was telling him about what I did as a blogger, an advocate and an activist. Later on, after I was allowed to meet with my "collaborators" according to my prisoners and asked each other, we found out we were all asked this same question “what do you think is your crime”? This describes the overall outcome of our interrogation. Since they couldn’t figure out what our supposed crime was or what law we were suspected of violating, we were asked

Sunday, August 10, 2014

‹‹አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ›› በጦማሪው በፍቃዱ ሃይሉ ተጽፎ ከቂሊንጦ እስርቤት ሾልኮ የወጣ ጽሁፍ

https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEi-hyrPO4gkHNuiOExpCsXIEOxn5AI_xWheB688HKzp0nyQwDFgtXfh6cbyS-dD3ghSMgidJJaKz0yITHwcTkxVUjDin2RQDc7-8RA7VbZRh67w-nLC01I1rUJBCZ9r9i55gvcfAI45dCA/s1600/BefeQaduZ.jpgይህ በቅርቡ በተለያዩ ድረገጾች እና የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ይፋ የሆነው የዞን ዘጠኝ ጦማር አባል የሆነው እና ከሌሎች አምስት ባልደረቦቹ እና ሶስት ጋዜጠኞች ጋር በህውሃት የጸጥታ ሰራተኞች  ታግቶ ላለፉት ሶስት ወራት ያለምንም ክስ እና ወንጀል በቂሊንጦ ምርመራ ክፍል ላይ ባለሰራው ወንጀል ፍዳውን የሚያየው የጦማሪ በፍቃዱ ሃይሉ አጭር ጽሁፍ፡ አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ኢፍትሃዊ ስርዓት እና አምባገነንት በመጠኑም ቢሆን ያሳያል። እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ግን፡ ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ተመሳሳይ ወይም ከዚህ የከፋ ወንጀል እየተፈጸመባቸው ሲሆን እነዚህን በደሎች እንደበፍቃዱ ለህዝብ የሚያደርሱባቸው መንገዶችም ሆነ ችሎታውም እንደሌላችው መገንዘብ ይገባል። ህውሃት፡ ይህን መሰሉን ኢሰብዓዊ ድርጊት ሲፈጽም የመጀመሪያው አይደለም የመጨረሻውም አይሆንም። የበፈቃዱ  ሃይሉ፡የአቤል ዋበላ ፡የአስማማው ሃይለጊዮርጊስ ፡የናትናኤል ፈለቀ፡የዘላለም ክብረት፡የኤዶም ካሳዬ፡የማህሌት ፋንታሁን፡የተስፋለም ወልደየስ፡የእስክንድር ነጋ ፡የርዕዮት ዓለሙ፡የውብሸት ታዬ፡የአንዷለም አራጌ፡ የበቀለ ገርባ እና የሌሎች በሺሆች የሚቆጠሩ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን ወንጀል፡ ለአገራቸው መቆርቆራቸው እና በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ህጸጾች ለማጋለጥ መድፈራቸው ብቻ ነው። 
‹‹ታዲያ ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?!››፣ ብሎኛል አንዱ መርማሪዬ ስለዞን ዘጠኝ እና እኔም እራሴ እንደጦማሪም እንደአራማጅ ተራማጅም ሠራሁ የምላቸውን ነገሮች ዝርዝር ነግሬው ሳበቃ፡፡ በኋላ ላይ በእስር ቤት ቋንቋ ከ‹‹አባሪዎቼ›› ጋር መገናኘት ከተፈቀደልን በኋላ ስንጠያየቅ ለካስ ሁላችንም ይቺኑ ጥያቄ ተጠይቀናል፡፡ ይኼ ነው እንግዲህ የምርመራችንን ሒደት የሚገልፀው ጥያቄ፡፡ ‹‹ተጠርጥረን›› የተያዝንበትን ጉዳይ የሚያረጋግጥ ሥራ ሠርተን ባለመገኘታችን

Wednesday, August 6, 2014

Ethiopia: 5 Popular Govt critic Magazines & a Newspaper facing criminal charges

Lomi magazine, Enque magazine, Fact magazine, Jano magazine, Lomi magazine, and Afro-Times newspaperThe Ethiopian Ministry of  Justice, in its vaguely worded statement released on a government owned TV channel on August 4, 2014 disclosed that it is filing criminal charges against top-selling and very popular privately owned government critic print media and their respective publishers for repeated acts of incitement and dissemination of false rumors intended to cause a violent overthrow of the constitutional order and to undermine the public trust on the government”. Meanwhile, the defendants revealed that they heard about their charges from the media like any ordinary citizens as opposed to receive a formal written charge which is supposed to be a normal procedure. The list of the accused privately owned press and their publishers are the following:
* Addis Guday Weekly Magazine,  by Rose publishing P.L.C.;
Lomi Weekly Magazine, by Dadimos Publishing P.L.C;
* Enque Bi-weekly  Magazine by Alemayehu Publishing P.L.C;
* Fact Weekly Magazine by Yofa Publishing P.L.C; 
* Jano Bi-weekly  Magazine by Asnake Publishing P.L.C;
The sixth one is a newly launched weekly newspaper called Afro-Times, which is affiliated to Lomi Magazine.
The statement claimed that the decision to lodge criminal charges was taken after several attempts to convince the magazines to change their practices. It also claimed that the public has been "demanding" for legal measures through various channels. Oh really? Fool me once, shame on you. Fool me twice, shame on me.
Not surprisingly, Ethiopia's Premier assured the US at the US-Africa summit yesterday ( August 5, 2014) that his government is working hard to fight "terrorism"; err since when unarmed bloggers, journalists, leaders of civil societies and opposition parties have become terrorists? 

Source: ERTA (Ethiopian Radio & Television Agency)

ፍትህ ምኒስቴር አምስት የግል መጽሄቶችን እና አንድ ጋዜጣን ህገመንግስቱን በሃይል ለመናድ ሞክረዋል በማለት ከሰሰ

Lomi magazine, Enque magazine, Fact magazine, Jano magazine, Lomi magazine, and Afro-Times newspaperምንስቴሩ ከትላንት በስትያ መንግስት በሚቆጣጠረው የቴሌቪዥን ማሰረጫ ባወጣው የተድበሰበሰ መግለጫ፡ እነዚህን የግል መጽሄቶችን፡ ጋዜጣውን እና አሳታሚዎቻቸውን «ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመጽ ለመናድ…» በሚል ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን ጋዜጠኞቹ እስካሁን የክስ መጥሪያ እንዳልደረሳቸውና መከሰሳቸውን እንደማንኛውም ሰው የሰሙት በቴሌቪዥን መሆኑን እየተናገሩ ነው፡፡ አቃቤ ህግ «ሕገመንግሥታዊ ሥርዓቱን በአመጽ ለመናድ፡ ህዝብን ለዓመጽ ለማነሳሳት እና በመንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ ያደርጋሉ» ብሎ የከሰሳቸው የግል መጽሄቶች እና ጋዜጣው የሚከተሉት ናቸው። 
1ኛ ሳምንታዊው አዲስ ጉዳይ መጽሄት፡ እና ሮዝ የግል አሳታሚ ድርጅት 
2ኛ ሳምንታዊው ሎሚ መጽሄት፡ እና ዳዲሞስ የግል አሳታሚ ድርጅት 
3ኛ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተመው እንቁ እና አለማየሁ የግል አሳታሚ ድርጅት 
4ኛ ሳምንታዊ ፋክት መጽሄት እና ዮፋ የግል አሳታሚ ድርጅት 
5ኛ በሳምንት ሁለት ጊዜ የሚታተመው ጃኖ መጽሄት እና አስናቀ የግል አሳታሚ ድርጅት ሲሆኑ 
ስደስተኛው እና በቅርብ ጊዜ መታተም የጀመረው አፍሮ ታይምስ የተባለው ሳምንታዊ ጋዜጣ የሎሚ መጽሄት አጋር እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል። 
ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ጠቅላይ ምኒስትራችን አሜሪካን አገር በተካሄደው የአፍሮ አሜሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ መንግስታቸው ከምንግዜውም በበለጠ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ቁርጠኝነቱን ለፕሬዚዳንት ኦባማ እና ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል። ሽብርተኞቹ የተባሉት እንግዲህ፡ በማእከላዊ፡በቃሊቲ፡በቂሊንጦ፡በዝዋይ እና በሌሎች እስርቤቶች ባልሰሩት ወንጀሎች ተይዘው ክስ ሳይመሰርትባቸው ወይም በሃሰት ተወንጅለው የሚሰቃዩት የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች፡ጋዜጠኞች፡የሲቪል ተቋማት መሪዎች፡የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና ተከታዮቻቸው፡ እና ሌሎች በሺህ የሚቆጠሩ መሳሪያ ያልጨበጡ ኢትዮጵያውያን የጸረሽብረተኛ ህጉ ሰለባዎች ናቸው።

ምንጭ ኢሬቴድ