ጋዜጠኛ
ጽዮን ግርማ በአራዳ
ምድብ ችሎት በአካል በመገኘት እንደዘገበችው እንደዘገበችው በዛሬው እለት የተከናወነው የፍርድ ቤት ድራማ ያው ህውሃት እንደለመደው በፍቃዱ ሃይሉ ማህሌት ፋንታሁን እና አቤል ዋበላ ላይ ፖሊስ ከትላንትናው ጋር ተመሳሳይ የሆነ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የጠየቀ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ 14 ቀን ፈቅዶለታል፡፡ፖሊስ
የጸረ ሽብር አዋጁን በመጥቀስ በሽብር ክስ ለማቅረብ ስላሰበ 28 ቀን እንዲሰጠው የጠየቀ ቢሆንም ዳኛው ያለምንም
የተለየ ተጨማሪ ነገር ከመነሻ ጥርጣሬ ለመቀየር ፖሊስ አሳማኝ ምክንያት ባለማቅረቡ 14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ
ብቻ ፈቅደዋል። የዛሬውን ውሎ ለየት የሚያደርገው፡ ፖሊስ የታሳሪዎቹ ቤተሰቦች እና ወዳጆችን እንዳያለቅሱ፡ለታሳሪዎቹ እጃቸውን
እንዳያውለበልቡ እና ምንም ዓይነት ምስል በፍርድቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳያነሱ/እንዳይቀርጹ መከልከሉ የአፈናውን
መጠነሰፊነት ያሳያል። ይህንን ጉዳይ በተመለከተ በትዊተር ላይ ዜጎች በሚከተለው መልኩ ቁጣቸው እና ሮሮአቸውን ሲገልጹ ነበር።
“እጅ ማውለብለብና ማልቀስ የተከለከለ ነው:: ይኽን የሚያደርግ ሰው ይዘን እንኼዳለን::” ፖሊስ
*መተንፈስ ክልክል ነው* pic.twitter.com/MooV7BOzIy
— Paliku Piluku (@PalikuPiluku) May 18, 2014
ህውሃት ኢትዮጵያውያንን መከልከል የቀረው መተንፈስ ብቻ ሳይሆን አይቀርም፡ ይሄንኑ በተመለከተ ደግሞ አንድ ፓሊኩ የተባሉ ግለሰብ በሚከተለው መልኩ ገልጸውታል