የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ እና ልዩ ክፍሉ
3'18'' "ጓደኛዬ የልዩ ፓሊስ አባላት በውሃ እና በኤሌክትሪክ ራሱን እስኪስት ካሰቃዩት በኋላ ህይወቱ አለፈች።"
3'28'' "የልዩ ፖሊስ አባላት ከ5 እስከ 10 የምንሆን እስረኞችን ነጥለው በመውሰድ ያሰቃዩን ነበር።"
ይህን በስዊድን አገር በሚገኘው ብሄራዊ የቴሌቪዥን ድርጅት ተቀናብሮ ባለፈው ሳምንት ይፋ የሆነውን ዘገባዊ ፊልም ለምን ያህ ግዜ ውስጤ እያረረ፡እየደበነ እና እየተሰቃየ እንዳየሁት በትክክል አላውቅም። ፊልሙ የተዘጋጀው ከሶማሌ ክልል በኢትዮጵያዊ አብዱላሂ ሁሴን በድብቅ ከአገር እንዲወጣ በተደረገው እና የአካባቢው ባለስልጣኖች እና የልዩ ፖሊስ አባላት በማናለብኝነት ኢሰብዓዊ በሆነ መንገድ ነዋሪውን ህዝብ ሲያሰቃዩ እንዲሁም በሶማሊያ ጠረፍ በኩል ወደ አካባቢው ከኦብነግ ታጣቂዎች ጋር በመግባት ዘገባ ለመስራት ሲሉ በተያዙት ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ላይ ህገወጥ ድርጊት ሲፈጽሙ በሚያሳየው ፊልም ተመስርቶ ሲሆን በዚህ ጽሁፍ መጀመሪያ ላይ እማኝነታቸውን የሰጡት እነዚህ የአካባቢው ነዋሪዎች አሁን በስደት