ሰላም ወገኖች ( the English version will follow for our friends who don't understand Amharic) ይሄንን አስደሳች ዜና ሳቀርብ ከፍተኛ የሆነ ክብርና ደስታ ይሰማኛል። ከመስፍን ነጋሽ የአዲስነገር ኦንላይን ዋና አዘጋጅ ጋር በመሆን ባሳለፍነው የፈረንጆቹ ዓመት ኢትዮጵያ ውስጥ ለ14 ወራት ባልሰሩት ወንጀል በቃሊቲ እስር ቤት እንዲሰቃዩ ከተደረጉ በኋላ የተፈቱትና አሁን አገራችው ገብተው በነጻነት ከሚንቀሳቀሱት ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ማለትም ዩዋን ፐርሹን እና ማርቲን ሺብዪ ጋር ያደረግነው ቃለምልልስ አምስተርዳም በሚገኙት የኢሳት ቲቪ ባልደረቦች ያላሰለሰ ትብብርና ጥረት እነሆ
በአማርኛ ተተርጉሞ ክፍል አንድ በኢትዮጵያ እና በውጭ አገር ለምንገኝ ወገኖች ቀርቧል። በዚህ አጋጣሚ ማርቲን እና ዩዋን በቃሊቲ እስርቤት ያሳለፉትን ሰቆቃ ለመርሳት ማረፍ ሲገባቸው የዚህን ቃለመጠይቅ ዓላማ በመገንዘብ ጊዜያቸውን በመሰዋት ቃለመጠየቁን በመስጠት ስለተባበሩን በኢሳት ቲቪ በመስፍን ነጋሽ እንዲሁም በመላው የኢሳት ተመልካች ስም ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ። ቀን ከሌት በመድከም ቃለምልልሱን ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ በመተርጎምና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህ ወቅታዊና ታሪካዊ ፋይዳ ያለው መልእክት እንዲዳረስ ጊዜያቸውን ጉልበታቸውና እውቀታቸውን ለሰውት አምስተርዳም በሚገኘው የኢሳት ቴሌቪዥን የስራ ባልደረቦች ታላቅ አክብሮቴንና ምስጋናዬን ሳቀርብ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል። በመጨረሻም ይህንን ቃለመጠይቅ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ የረዱንን አለማየሁ በቀለ እና ኤልያስ አየለ ከስዊድን እንዲሁም ግሎባልሪፖርቲንግ የተባለውን ስዊድናዊ የመገናኛ ብዙሃን አማካሪ ድርጅት ቃለምልልሱ በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ላደረገልን ሙያዊና ቁሳዊ እገዛ ሳላመሰገን ማለፍ አልፈልግም።

Hello everybody,
I'm glad to share with you this good news; the interview which Mesfin Negash, Managing editor of Addis-Neger online and I conducted last year with Johan Persson and Martin Schibbye (the duo Swedish journalist who were imprisoned for fourteen months and released) is now finally transcribed in Amharic and on air to all Ethiopians at home and abroad, thanks to hard-working staff members ESAT's Amsterdam bureau. On this occasion, I would like to thank on behalf of ESATtv, Mesfin Negash, all Ethiopians at home and abroad as well as myself; Martin and Johan for spending your time with us (when you needed was rest and to forget about Kality) to expose the 14 months atrocities you had been to go through in Ethiopia. I'd like to thank and commend staff members of Amsterdam's ESATtv for their unparalleled dedication and hard-work in transcribing the interview from English to Amharic so that all Ethiopians at home and abroad could have access to this historic and relevant interview with these two courageous journalists. Last but not least, I'm honored and glad to do this wonderful job with people like Mesfin Negash, Alemayhu Bekele, Elias Ayele and above all GlobalReporting (a Swedish Media consultancy firm) for its professional and logistical assistance to conduct this interview which otherwise would not have been possible. Thanks a lot Enjoy the clip and let's wait for the part II.
No comments:
Post a Comment