ሌሊሴ ወዳጆ የህሊና አስረኛ |
አገራችን
ከቅርብ አመታት ወዲህ እድሜ አሁን በህይወት
ለሌሉት ባለራዕዩ ልማታዊ መሪያችን እና
ፓርቲያቸው፡ በተለያዩ ምክንያቶች ታዋቂነቷ
እየገነነ መጥቷል።ሌላ ሌላውን ትትተን
በፈረንጆቹ የ2012
ዓመት
በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ጋዜጠኞችን በማሰር
ሁለተኛነትን
ስተቀዳጅ፡አንደኝነቱን ግን ጎረቤታችን
ኤሪትርያ ነጥቃናለች፡ወይ ነዶ፡እንዴት
ተድርጎ። ምስጋና ለታላቁ መሪያችን ነፍሳቸውን
ይማረውና (ይቅርታ
ተዳፈርኩ አይደል፡ለካ አልሞቱም የሚሉ አንዳንድ
ወገኖች እንዳሉ ዘንግቼው ነው)፡
አገራችን ባለፉት አስርተ ዓመታት ጋዜጠኞቿ
እንዲሰደዱ
በማድረግ በከፍተኛ ደረጃ ከሚጠቀሱት አገሮች
ተርታ ውስጥ ትገኛለች። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ
ደግሞ በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞቿ በማሸለም
ታዋቂ ሆናለች። የሩቁን ትተን በዚህ ዓመት
ብቻ ሁለት በሽብርተኝነት እና አገር በመካድ
ወንጀሎች ተፈርዶባቸው ቃሊቲ በእስር ላይ
የሚገኙት ጋዜጠኞቿ ማለትም እስክንድር
ነጋ እና ርዕዮት
ዓለሙ ከሁለት የተለያዩ የዓለም ዓቀፍ
ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ተሟጋች
ድርጅቶች ተሸላሚ ሆነዋል። አብዛኛውን ጊዜ
የመገናኛ ብዝሃንም ሆነ በመብት ተሟጋች
ድርጅቶች በግሉ የሚዲያ ዘርፍ የሚያገለግሉ
ጋዜጠኞች ሲታሰሩ በብዛት የሚያሰሙት ድምጽ